እስኪ እንነጋገር!
በሙስሊም መሪ ላይ አምፆ ስለመውጣት ያሉ ብዥታዎችና መልሶቻቸው
"...إلا أن تروا كفرا بواحا"
"...ግልፅ የሆነ ክህደት (ኩፍር) እስክታዩ ድረስ (ከትዕዛዝ አትውጡ)" የሚለው የዑባዳህ ሐዲስ ነው።
"مَنْ وَلِيَ عَلَيْهِ وَالٍ فَرَآهُ يَأْتِي شَيْئًا مِنْ مَعْصِيَةِ اللَّهِ فَلْيَكْرَهْ مَا يَأْتِي مِنْ مَعْصِيَةِ اللَّهِ ، وَلا يَنْزِعَنَّ يَدًا مِنْ طَاعَةِ اللَّهِ."
"አንድ መሪ የተሾመበት ሰው አላህ የሚታመፅበትን ወንጀል (መሪው) ሲሰራ ካየ ወንጀሉን ይጥላ፣ (መሪውን በማመፅ) አላህን ከመታዘዝ ግን እጁን እንዳያነሳ" ተብሏልና።
"يا أيها الذين آمنوا أطيعوا الله وأطيعوا الرسول وأولوا الأمر منكم" (القرآن)
"እናንተ ያመናችሁ ሆይ፣ አላህን ታዘዙ፣ መልዕክተኛውንም ታዘዙ፣ ከናንተ የጉዳዩ ባለቤት የሆኑትንም (መሪዎች ታዘዙ)" (ቁርአን)
"...فاصبروا حتى تلقوني على الحوض"
"(ከመሪዎች አድሎና ግፍ ቢደርስባችሁ) ሐውድ ላይ እስክታገኙኝ ድረስ #ታገሱ" ብለዋል።
"...أدوا الذي عليكم، وتسألون الله الذي لكم"
"እናንተ ላይ ያለባችሁን ሐቅ ተወጡ፣ የናንተን ደግሞ አሏህን ጠይቁ"
"... اسمعوا وأطيعوا وان تآمر عليكم عبد حبشي"
በዒርባድ ረዲየሏሁ ዓንሁ ሐዲስ፣
"(እናንተ ባትወዱትም) የሐበሻ ባሪያ መሪ ከሆነባችሁ ስሙት ታዘዙትም"
"يكون بعدي أئمة لا يهتدون بهداي ولا يستنون بسنتي فاسمع وأطع"
"ከእኔ በኋላ በኔ መንገድ የማይጓዙ፣ በሱንናዬም የማይመሩ መሪዎች ይመጣሉ። (እነኝህን መሪዎች) ስማ ታዘዝም"
(አቡ የሕያ ያሲን፣ ሚያዝያ 11,2010)

0 Comments