እናታችን ኡሙ ሰለማህ ባስተላለፈችው ሐዲሥ የአላህ መልእክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል:–
((إنما أنا بشر، وإنكم تختصمون إلي، ولعل بعضكم أن يكون ألحن بحجته من بعض، فأقضي له بنحو ما أسمع، فمن قضيت له بحق أخيه فإنما أقطع له قطعة من النار)).
"እኔ ሰው ነኝ። እናንተ ደግሞ ወደኔ ትካሰሳላችሁ። ምናልባትም ከፊላችሁ በሙግቱ ላይ ይበልጥ አዋቂ ይሆንና በሰማሁት መሰረት እፈርድለታለሁ። እናም የወንድሙን ሐቅ የፈረድኩለት ሰው የእሳትን ቁራጭ ነው የምቆርጥለት።" [ቡኻሪና ሙስሊም]
ከሐዲሡ የሚወሰዱ ቁም ነገሮች:–
① ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሰው እንደሆኑ። በዚህ ረገድ ብዙ የሚነዙ ውሸቶችን ያስተውሉት።
② ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ከሰዎች ልቦና ውስጥ ያለን እንደማያውቁ፣
③ ዳኛ የሆነ ሰው ከፍርድ በፊት ተካሳሾችን ሁለቱንም መስማት እንዳለበት፣
④ ፍትህን ለማስፈን የሚችለውን ጥሮ የተሳሳተ ሰው ወንጀለኛ እንደማይሆን፣
⑥ በክርክር በልጦ በዳኛ ማስወሰን ከወንጀል እንደማያተርፍ
⑤ የሰው ሐቅ በዚህ መልኩ የሚወስድ ሰው እሳት እንዳለበት።
0 Comments