Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ባ’ንድ ራስ ሁለት ምላስ

★ ባ’ንድ ራስ ሁለት ምላስ ★
"በኛና በክርስቲያኖች መከከል ያለው ልዩነት የዐቂዳ (የእምነት) ልዩነት አይደለም። ይልቁንም ዳይናሚካል ልዩነት ነው።"
·
·
·
·
·
·
·
·
·
·

·
✘ "ማነው ይህን ያለው? የትኛው ደንቆሮ ነው በስላሴና በተውሒድ መካከል ያለውን ልዩነት መለየት ያቃተው?
ኢብኑ ባዝ?!
ጃሚ?!
ፈውዛን?!
እነሱ ናቸው?!
ነው ወይስ ይሄ ሙሐመድ ቢን ሰልማን የሚባለው ሰውየ ነው?! ንገረኛ?!!"
 "ተረጋጋ እንጂ አጎቴ?"
✘ "እንዴት እረጋጋለሁ? ጭራሽ እስልምናና ክርስትናን አንድ ሊያደርጉ ነው?"
 "መረጋጋትህ ላይቀር ባንተዛዘብ አይሻልም?"
✘ "ምን ማለት ነው? ይሄ የሚያረጋጋ ነው?! ቅድሚያ ለተውሒድ የምትሉት ለዚህ ቅጣችሁ ነው?"
 "እየውልህ ‘በኛና በክርስቲያኖች መከከል ያለው ልዩነት የዐቂዳ ልዩነት አይደለም’ ያለው ማን መሰለህ?"
✘ "ተናገራ! ምን ትንቀጠቀጣለህ?! እህን ጊዜ የሌላ ሰው ቢሆን ለማራገብ አንደኛ ነበራችሁ"
 "ይህን ያለው የቀድሞው የግብፅ ፕሬዚደንት
#ኢኽዋኒው
#ሙሐመድ_ሙርሲ ነው።
እርግጠኛ ነኝ አሁን ትረጋጋለህ።"
✘ "እ…እ… እ አይ እሱኮ ማለት የፈለገው…"
 "ዝም በል! አታላይ! ነጋዴ!"
✘ "ደግሞ ነጋዴነት ስድብ ሆነ?"
 "ነጋዴነት ክብር ነው! በዲን መነገድ ነው ብልግናው!"
✘ "እኔኮ ማለት የፈለግኩት ስልጣን ላይ ሳለ የክርስቲያኖችን በተለይም የምእራባውያንን ተፅእኖ ለመቀነስ የተናገረው ይሆናል ለማለት ነው።"
 "የለም የለም! ይሄ አጭበርባሪ የሆነ ቡድናዊ መለኪያ እንዳላችሁ ነው የሚያሳየው። መጀመሪያ መገንፈልህ ለምን ነበር? የጥፋቱ ክብደት ሳይሆን የሰዎች ማንነት ነው የሚያስጨንቅህ። እንጂ ይሄ አደገኛ ጥፋት የንጉስ ሰልማን ወይም የልጁ ቢሆን እንኳን ለሙርሲ እንዳደረግከው በጥሩ ልትተረጉምለት ይቅርና ቀባብተህ፣ ጨማምረህ ከእርግማንና ከማክፈር ጋር ነበር የምታቀርበው። መቼ ነው ግን ማስተዋል የምትጀምሩት?!"

Post a Comment

0 Comments