Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

የምንፅፈውን የምንለውን እንምረጥ(እንወቅ)

#የምንፅፈውን የምንለውን እንምረጥ(እንወቅ)
💥በሶሻል ሚዲያ የተሰማንን ሁሉ መግለፅ አይጠበቀብንም! የተለያዩ የሰው ኣይነቶች በእድሜ፣ በፆታ፣ በእውቀት ደረጃ ያሉበት ነው ሶሻል ሚዲያ በተለይ ፌስቡክ ራሱን የቻለ ዓለም ነው ይህን አገኘሁትና ተመቸኝ ብለን መፃፍ አይገባም፣ሰውም ከፃፈ ኮሜንት መስጠት ሸርና ኮፒ ማድረግ ወይም ተመሳሳይ ነገር መፃፍ አይኖርብንም ቆም ብለን እናስተውል
★ሴቶች ጋ ያለው ድፍረት በዚህ ዘመን እጅጉን ያስደነግጣል ፣ ያስፈራል የት ነው ያለነው?ብለን እንድናስብም ያደርጋል ግን ምን ይጠቅመናል ? የሚያሳዝነው ይህን የምናደርገው ስማችን የሙስሊም፣ለኢስላምም ፍቅር አለኝ የምንል መሆናችን ነው ።
💥
እንኳን ኢስላም የሀገራችን ባህል የማይፈቅደውን ንፁህ ተፈጥሮ ያለው
የሚያፍርበትን ሁሉ ስለ ትዳር በሶሻል ሚዲያ ማወጅ ምን ይሉታል?
በአደባባይ! ይህ በፍፁም ስልጣኔ እንዳይመስለን ፣ አላዋቂነታችንን ነው አጉልቶ የሚያሳየው ነውር ነው ለብዙም ሰው የወንጀል በር እንሆናለን የምናውቀው፣ የማናውቀው ስለ እኛ እያወራ ሀሜት ውስጥ ይገባል፣ በፊትናች የተነሳ ፣ዱዓ እንጅ የሶሻል ሚዲያ አይጠቅምም የተሰማን ስሜት አውርቶ መፍትሄ ለማግኘት
★ንፅህት፣ጥብቅ (ዐፊፋ) ብንሆን ጥሩ ነው ለራሳችን ነው የሚጠቅመው
በንግግር ፣በተለያዩ እንቅስቃሴ ከአላህ አጅርን በመፈለግና በማሰብ ላይ ሆነሽ ትዳር ሳይኖርሽ ከጌታሽ ብትገናኝ ባለማግባትሽ ጌታሽ አይጠይቅሽም ነገር ግን አጉል ያወቅሽ(የሰለጠንሽ) እየመሰለሽ መድረክ አገኘሁ ብለሽየምትፅፊው ድንበር የምታልፊው እርባና ቢስ ተራ ወሬ ጌታሽ ፊት ነገ ያስጠይቅሻልና መጠንቀቁ ይሻላል ፣
★አይን አፋርነት ውበት ነው፣ጌጥ ነው እየተረሳ ያለ
ጥሩ የአላህ ስጦታ ነበር
★ታላቁ ነቢያችን ሐያእ (አይን አፋርነት) ከኢማን ነው ብለውናል ።
ሩቀያ ዐብደላህ

Post a Comment

0 Comments