Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

እኛስ ቁርኣን ስንቀራ ምን ይሰማናል?

እኛስ ቁርኣን ስንቀራ ምን ይሰማናል?
"የነብዩ ﷺ ሶሐቦች ቁርኣንን ሲሰሙ እንዴት ነበረ?" ተብላ የተጠየቀችው አስማእ ቢንት አቡበክር መልሷ እንዲህ የሚል ነበር:–
"تدمع أعينهم وتقشعر جلودهم، كما نعتهم الله".
"አይኖቻቸው ያነባሉ። ቆዳዎቻቸው ይኮማተራሉ። ልክ አላህ እንደገለፃቸው!" 📚أخرجه البيهقي ٢/٣٦٥.
እኛስ በምንድን ነው የምናለቅሰው? ለመሆኑ ቁርኣንን ስንቀራ በዛቻው እንርዳለን? በተስፋ ቃሉ እንቋምጣለን? ታሪኩን እናጣጥማለን? ኧረ ይህም ይቅር ለመሆኑ ቁርኣን እንቀራለን? መልሱ "አዎ" የሆነ ሰው ምንኛ የታደለ ነው? ግን መቼ ነው የምንቀራው?
★ በየቀኑ?
★ በሳምንት ጁሙዐ?
★ በአመት ረመዳን ወር? መቼ?
አላህ ይድረስልን።
ነገ አዋጅ አለ! እንዲህ የሚል ነብያዊ አዋጅ!
(وَقَالَ الرَّسُولُ يَا رَبِّ إِنَّ قَوْمِي اتَّخَذُوا هَٰذَا الْقُرْآنَ مَهْجُورًا)
[ الفرقان 30]
"መልክተኛውም ‘ጌታዬ ሆይ! ሕዝቦቼ ይህንን ቁርኣን የተተወ ነገር አድርገው ያዙት’ አለ፡፡" [አልፉርቃን: 30]
ያኔ ምን ይሆን መልሳችን?

Post a Comment

0 Comments