Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

የቱን እንምረጥ የእውነቱን ወይንስ የውሸቱን አንድነት?


የቱን እንምረጥ የእውነቱን ወይንስ የውሸቱን አንድነት?
አላህ የልብ መመልከቻችንን ያብራልን፡፡
አላህ ሐቁን ይምራን፡፡ የውስጥ መመልከቻ ሲታወር የላይኛው አይን ቢመለከትም አያይም፡፡
እስቲ የአላህ ባሪያዎች ሆይ! አላህ በሰጠን ንጹህ አእምሮ እንየው እንዴት ነው እውነተኛው ብቸኛ አንድ መንገድ አንድ ያደርጋል፣ እሷም ላይ እንሰብሰብ ማለት “ሙቡታተን” በተገላቢጦሹ ደግሞ አላህ ያወገዘውን የሰይጣን መንገዶች መከተል እና ልዩነት “አንድነት” ተብሎ የሚጠራው?
የአላህ ባሪያዎች ሆይ! እስቲ የሚከተሉትን ጥያቄዎች ነፍሳችንን እንጠይቅ
1) ሃቅ ስንት ናት?
መልሱም አንድ እና አንድ ብቻ ናት፡፡ ለዚህም ማስረጃው ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) አብደላህ ኢብን መስኡድ ባስተላለፉት ሀዲስ “መሬት ላይ ቀጥተኛ መስመር አሰመሩ ይህም የአላህ ቀጥተኛው መንገድ ነው አሉ”
“ከዛም በጎን እና በጎን ሌሎች መስመሮች አሰመሩ እነዚህም መንገዶች ናቸው እያንዳንዱ መንገድ ላይ የሰይጣን ተጣሪ አለበት” አሉ፡፡
እስቲ ሀቅ ፈላጊዎች ሆይ! ሰይጣን የሚጣራባቸው የጥመት መንገዶች ብዙ መሆናቸው እና ሃቅ ብቸኛ አንድ መንገድ መሆኗ በነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) አንደበት ተነገረን ወይንስ አልተነገረንም?
መልሱም ተነገረን ነው፡፡
2) የትኛው ነው የሃቅ መንገድ?
ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ቁጥር አንድ ላይ ባየነው ነጥብ መሰረት ሃቅ አንድ መሆኗን ገልጸዋል፡፡ ከዚህም በመቀጠል እቺን ብቸኛ የሀቅ ጎዳና እናውቃት ዘንድ የቷ ናት?
የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ ይላሉ “የሁዳዎች 71 ቦታ ይከፈላሉ፣ ነሷራዎች 72 ቦታ ይከፈላሉ፣ ይህም ኡመት 73 ቦታ ይከፈላል ሁሉም የእሳት ናቸው አንዷ ስትቀር”
የአላህ መልክተኛ አሁንም የሀቅ መንገድ አንድ ብቻ መሆኗን ጠቀሱ
የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) አንዷ የሀቅ መንገድ የትኛዋናት ተብለው ሲጠየቁ
“እኔ እና ሰሃባዎቼ ዛሬ ያለንባት መንገድ ናት” አሉ፡፡
በሌላ ሀዲስ ደግሞ
“ከሰዎች ሁሉ በላጭ እኔ ያለሁባቸው (ሰሃባዎች)፣ ከዛም ቀጥሎ ያሉት (ታቢኢን)፣ ከዛም ከጥሎ ያሉት (አትባኡ ታቢኢን)”
ይህ ነው እንግዲህ ብቸኛው የሁለት አገር ደህንነት እና ሰላም ዋስትና፣ የሰለፍያ ጎዳና፣ ብቸኛው ሃቅ፣ ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም)፣ ኹለፋኡ ራሺዲን፣ ሰሃባዎች፣ ታቢኢዬች፣ አትባኡታቢኢን የሄዱበት መንገድ፡፡
የአላህ ባሪያዎች ሆይ! ግልጽ ሆነልን ሀቅ አንድ ብቻ መሆኗ?
ባረከላሁ ፊኩም፡፡ ሰይጣን የሚጣራባቸው የእሳት፣ የጥመት እና የጥፋት መንገዶች የትኛዎቹ ናቸው የሚለውን በሚቀጥለው ነጥብ እንመልከት፡፡
3) የትኛዎቹ ናቸውስ የትፋት መንገዶች?
ማንኛውም የነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እና የሰሃባዎቻቸው፣ የሰለፉነ ሷሊሂንን መንገድ ያልተከተለ እና የተቃረነ እዚህ የጥፋት እና የጥመት መንገድ ውስጥ ይገባል፡፡ ይህ ተቃርኖ በእምነት ጉዳይም ይሁን በአካሄድ ብቸኛዋን የሃቅ መንገድ የተቃረን ሁሉ እዚህ ሰይጣን የሚጣራበት የጥፋት መንገድ ውስጥ ገብቷል፡፡
በአላህ ፍቃድ እዚህ ጋር የጥመት ቡድኖችን ስም እጠቅሳለሁ፡፡ ልክ የሀቋ ብቸኛ ሰለፊያ ጎዳናን እንደጠቀስኩት ሁሉ፡፡
- ቀደሪያ፣
- ኸዋሪጅ፣ ሀሩሪያ፣ ኡባዲያ፣
- ራፊዳ ሺኣ፣
- ሙእተዚላ፣
- ማትሩድያ፣
- ጀህሚያ፣
- አሽአሪያ፣
- ኩላቢያ፣
- ሱፊያ ቃዲርያ፣
- ሱፍያ ቲጃንያ፣
- ሱፍያ ነቅሸበንዲያ……፣
- ኢኽዋን፣ ቁጥቢያ፣ ሱሩሪያ፣ ተብሊግ፣ አህባሽ፣ …….. እና ሌሎችም
እዚህ የተዘረዘሩት ሁላ ብቸኛዋን የሃቅ ጎዳና ሰለፊያ የተቃረኑ ናቸው፡፡ መንገድ የሳቱ ቡድኖች ለመሆናቸው ይሄ ማስረጃ ነው፡፡
4) ከላይ ቁጥር 3 ላይ የተዘረዘሩት ስንት ናቸው?
እንደሚታወቀው ቁጥር ሶስት ላይ የተዘረዘሩት ከአንድ በላይ ናቸው፡፡ ከዛም አልፎ ከብቸኛው የሰለፎች ጎዳና የተቃረኑ የጥመት ጎዳናዎች ናቸው፡፡
5) የመጀመሪያ ነጥብ ላይ ሃቅ ስንት እንደሆነች ነበር ያየነው?
መልሱም አንድ ብቻ ናት፡፡
6) ታድያ ለምን የውሸት አንድነት አስፈለገ?
ኢናሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂኡን፡፡ በዚህ ዘመን ሙስሊሙ በአንድ ሀቅ ላይ እንዳይሰባሰብ “ሁሉም ጀመኣ የራሱ ድክመት አለው”፣ “ሰው ሆኖ የማይሳሳት የለም” እና የመሳሰለውን እያሉ የሚበታትኑት እና ተለያይቶ “አንድ ነን” እያለ እንዲዋሽ የሚያደርጉት የጥመት ቡድን የሆኑት ኢኽዋነል ሙስሊሚን ፍልስፍናን ተከታዬች ናቸው፡፡
ለምሳሌ፡-
ሀሰን አል በና የተባለው የዚህ ጥመት ፖለቲካዊ ቡድን መስራች እንዲህ ይላል
اعلموا أنَّ أهل السنة والشيعة مسلمون تجمعهم كلمة لا إله إلاَّ الله وأنَّ محمداً رسول الله وهذا أصل العقيدة ,والسنة والشيعة فيه سواء وعلى التقاء ,أما الخلاف بينهما فهو في أمور من الممكن التقريب فيها بينهما
(ذكريات لا مذكرات)ط1- دار الاعتصام 1985 يقول الأستاذ عمر التلمساني ص249 و250
“እወቅ አህለሱና እና ሺአ ሙስሊሞች ናቸው፡፡ ላኢላሃ ኢለላህ ሙሐመዱ ረሱሉላህ የምትለው ቃል አንድ ታደርጋቸዋለች፡፡ ይህችም የአቂዳ መሰረት ናት፡፡ ሱና እና ሺኣ በዚህ ጉዳይ አንድ ናቸው፣ እኩል (የሚገናኙ፣ የሚጣጣሙ) ናቸው፡፡ በመካከላቸው ያለው ልዩነት እማ ሁለቱንም ማቀራረብ የሚቻል ነው (እንደ ልዩነት አይቆጠርም፡፡ ብዙ የሚያስቆጣ አይደለም፡፡)”
እውነታው ግን ሀሰን አል በና እንዳለው ሳይሆን ከሺአ ራፊዳዎች ጋር አንድ መሆን በፍጹም አንችልም፡፡ ልዩነታችንም የእምነት እና የክህደት ጉዳይ ነው፡፡
ምክንያቱን እነሱ ማለት እምነታቸው እና ተግባራቸው እንደሚከተለው በክህደት የተጨማለቀ ነው
- 12ቱ ኢማም ብለው የሚያምኑባቸውን ‹‹ከነብያት በላይ ናቸው፡፡ ከነብያት ይበልጣሉ›› ይላሉ፡፡ ይህ አባባላቸው ክህደት ነው፡፡
- ከአላህ ውጭ ‹‹ያ ሁሴን፣ ያ አልይ፣ ያ ፋጢማ፣ ያ ዘይነብ………›› እያሉ ይጣራሉ፡፡ ይሄም ሽርክ ነው፡፡ ጥሪ የሚገባው ለአላህ ብቻ ነው፡፡
- “ቁርዐን ተቀንሷል፤ ሱረቱል ዊላያ የሚባል ሱራ አለ ያላሉ” ይህ የክህደት እምነት ነው ምክንያቱም አላህ “ቁርዐንን እኛ ነን ያወረድነው እኛው እንጠብቀዋለን” ስለሚል ነው፤
- ሀዲስንም አይቀበሉም ቡኻሪ፤ ሙስሊም፤ አህመድ የመሳሰሉትን፡፡ በሱና የሚክድ ካፊር ነው፡፡
- እንዲህ ብለው ነሺዳ ሲያነሽዱም ተሰምተዋል “አንተ ሁሴን ከአላህ በላይ ትልቅ ነህ” ይሄም ኩፍር ነው፡፡
- የሺዐ መሪ ከነበሩት አንዱ ሃያቶላ ኹመይኒ እንዲህ ይላል “አነዚህ ሙሽሪኮች መዲናን መውረርና እነዛን ሁለት ጣዖቶች (አቡበክር እና ኡመርን) ማስወገድ ፈለጉ” ተመልከት ሱንዬ ወንድሜ ሆይ! ኢኽዋኖች ለማን አሳልፈው እየሰጡህ እንደሆነ? አቡበክርና ኡመርን (ረድየላሁ አንሁማ) ጣኦት ብሎ የሚጠራ ሸይጧን፡፡
- ከሺዐዎች መሪ አንዱም ስለ ምዕመናን እናት አኢሻ እንዲህ አለ “አኢሻ በእርግጥ ካሃዲ(ካፊር) ናት” የአላህ እና የረጋሚዎች እርግማን ሁሉ በርሱ ላይ ይሁን፡፡ ይህም ኩፍር ነው፡፡
- ከሺዐዎች አንዱም ተጠየቀ “ሱንዩ አለም ሙስሊም ይባላል ወይ?” እሱም “አይባሉም፤ ምክንያቱም ሙስሊም የሆነ ሰው አቡበክርን እና ኡመርን አይወድም” በማለት መለሰ፡፡ የአላህ ቁጣ በሱ ላይ ይሁንና፡፡ አቡበክርና ኡመርን በመውደድ ወደ አላህ እንቃረባለን፡፡
- የኡመር ኢብነል ኸጣብን ገዳይ አቡ አላ አልመጁሲን የዲን ጀግና ነው ብለው አላህን ከዚህ የተረገመ ሰው ጋር እንዲቀሰቅሳቸው ዱዐ ያደርጋሉ፤
- ኡመር የተገደለበትን ቀን የኢድ ቀን አድርገው ይዘዋል፤
- አቡበክርና ኡመር ከሸይጧን በታች ጀሀነም ውስጥ እየተቀጡ ነው ይላሉ፤
- ኢራን ላይ ሱንዬችን በክሪን ላይ ሰቅላ ትገድላለች፡፡ አላህ ያዋርዳቸውና
- እንደዚሁም ከነሱ ሸሆች አንዱ በVCD እየታየ ነብያችን አስሩን ጀነት ያበሰሩዋቸውን ሰሃባዎች አላህ ይርገማቸው ብሎ ዱዐ ያደርጋል፤
- ሌላው ሀሰን ነስረላህ በመባል የሚታወቀው የሂዝቦላህ መሪ ታላቁን ሰሃባ አቡሱፍያንን ሲያከፍር በቴሌቭዥን ታይቷል፤
- ኢብነል ቀይም እንደገለፃቸው “አንድም የውጭ ጠላት እስላምን ለማጥቃት አይመጣም ሺዐዎች እየመሩ ቢያመጡት እንጂ”፤ የሺዐዎች ጉድ ተነግሮ አያልቅም፡፡
አገራችንም ላይ የዚሁ የጥመት አስተምህሮት የኢኽዋን ተከታዬች የሽርክ መነሃሪያ የሆነውን መውሊድ የሚያከብሩ ሱፍዬችን፣ የሽርክ መንዙማ የሚያቀነቅኑ ሰዎችን፣ በቢድአ የታጨቁትን ተብሊጎች ቀን ከለሊት ከዚህ ሽርክ እና ቢድአቸው እንዲወጡ ከማስተማር ይልቅ “አንድ ነን እኛ ምንም አይለየን”፣ “መውሊድ አይለያየንም”፣ “መውሊድ ቅርንጫፍ ነው”፣ “ሱፊዬች ወንድሞቻችን ናቸው”፣ “መውሊድ አቂዳ አይደለም” ከዚህም አልፈው አለቃቸው አንዱ ኢኽዋኒ “መውሊድ” የሚል መጸሀፍ ጻፈ፡፡
7) የቱን እንምረጥ የእውነቱን ወይንስ የውሸቱን አንድነት?
አላህ ያዘዘን የሀቅ አንድነት ላይ እንድንሰባሰብ ነው፡፡ ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለምም) ሆነ ሰሃባዎቻቸው በሃቅ ላይ ተሰበሰቡ ቀጥተኛዋን መንገድ ከተቃረኑ ሰዎች ራቁ፡፡
ለዚህም ታላቁ ምሳሌ ታላቁ ሰሃባ አብደላህ ኢብን ኡመር ነው፡፡ ኢራቅ በስራ አካባቢ ቀደርያዎች ሲከሰቱ የእሱ መልስ የነበረው የሚከተለው ነው፡፡
“ንገሯቸው እኔም ከነሱ አይደለሁም እነሱም ከእኔ አይደሉም”፡፡
የአላህ ባሪያዎች ሆይ! ግልጽ ሆነላችሁ?
እኛ አላህ ያዘዘን በሀቁ አንድነት ላይ እንድንሰባሰብ ነው፡፡ ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ኡማው እንደሚለያይ እና ያ ልዩነት በተፈጠረ ሰኣት ሃቋ ላይ እንድንጸና ነው የነገሩን፡፡
ነፍሴንም እናንተንም የጥንት የጠዋቷን መንገድ አጥብቆ በመያዝ ላይ አደራ አደራ አደራ፡፡
ብቸኛዋ የመዳኛ መንገድ ዳእዋ ሰለፊያ ከነተከታዬቿ
- ከምንም በፊት ነብያት ሁሉ ቅድሚያ ለተውሒድ እና ሱና እንደሰጡት ትሰጣለች፣
- ቁርኣን እና ሀዲስን በሰለፉነ ሷሊሂን አረዳድ ትረዳለች፣
- ተስፊያ እና ተርቢያ ላይ ታተኩራለች፣
- ከማንኛውም የጥመት ቡድን ያስጠነቅቃሉ፣
- ሀቅ አንድ ብቻ መሆኑን ያጸድቃሉ……….
የአላህ ባሪያዎች ሆይ! ለነፍሳችን እንዘንላት ሁሉንም የጥመት ቡድኖች ትተን ብቸኛዋን ቃል የተገባላትን የሃቅ መንገድ እንከተል፡፡ ይህን ማድረግ አንድነትን መጠበቅ ሲባል፣ ከዚህ ውጭ ያለው አንድነትን ማፍረስ ይባላል፡፡ ምክንያቱም የሙስሊሞችን አንድነት ኸዋሪጆች፣ ራፊዳዎች፣ ቀደሪያዎች፣ ጀበሪያዎች፣ ሙእተዚላዎች፣ ማትሩድያዎች… ሱፍዬች፣ ኢኽዋኖች፣ ተብሊጎች፣ አህባሾች መጥተው በትነውታልና፡፡ የአላህ ባሪያዎች ሆይ! በጥመት ቡድኖች መሃል ያለው የጥመት ደረጃ ቢለያይም ሁሉም ግን ጥመት ነው፡፡ ከአህባሽ ጋር አንድ ነን እንደማንለው ሁሉ ለምን ከሁሉም የጥመት ቡድኖች ወይንም ለነዚህ የጥመት ቡድኖች ከለላ ከሚሰጡ ግለሰቦች ርቀን የሃቁ አንድነት ላይ አንሰባሰብም? ይህ መንገድ የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እና ሰሃባዎቻቸው የነበሩበት ብቸኛ የዋስትና መንገድ ነውና፡፡
አላህ ሆይ! የእውነተኛ አንድነት ስጠን ከውሸት አንድነት ጠብቀን፡፡ የአላህ ሰላት እና ሰላም በመልክተኛው፣ በቤተሰቦቻቸው፣ በባልደረባዎቻቸው እና ሃቅን በተከተለ ላይ ሁሉ ይሁን፡፡ አሚን