Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ሺኣዎች አያፍሩም ድብን ያለ ክህደት ላይ ተቀምጠው “በምድር ላይ ጥርት ያለችው ተውሒድ አለችን” ይላሉ፡፡

 
 

ሺኣዎች አያፍሩም ድብን ያለ ክህደት ላይ ተቀምጠው “በምድር ላይ ጥርት ያለችው ተውሒድ አለችን” ይላሉ፡፡
ሙሉ ማብራሪያው በማስረጃ
ሺአዎች ዘንድ “ጥርት ያለ ተውሒድ” የሚሏት ምን እንደሆነች በዚህ ክህደት ከተሞላበት ቪድዬዋቸው ይመልከቱ፡፡
መግቢያ ላይ የሚናገረው ራፊዳ ሺኣ እንዲህ ይላል
- “እኛ ሺአዎች በዚህ ወቅት፣ እዚህ ምድር ላይ ጥርት ያለችው ተውሒድ አለችን፡፡”
ከዛም በመቀጠል የሺአ ጠሞ አጥማሚ ሸሆች እንዲህ ይላሉ
- “ይህ ነው የተውሒድ ትርጉም፡፡ በፋጢመቱ ዛህራ ለመጠበቅ ሰላተል እስቲጋሳ (የጭንቅ ጊዜ ሰላት) ልትሰግድ ነው፡፡ ሱጁድም ልታደርግ ነው፡፡ ከዛም ጠባቂዬ አንቺ ፋጢማ ሆይ! ከጭንቅ አውጭኝ (ድረሽልኝ) ብለህ 100 ጊዜ ልትል ነው፡፡ ይሄ ነው ተውሒድ፡፡ አንቺ ፋጢማ ሆይ! እርጂኝ ካላልክ ተውሒድ የለህም፡፡ የተውሒድንም ትርጉም አታውቀውም፡፡”
**********************
እንግዲህ ይሄ ሽርክ ነው፡፡ ከአላህ ውጭ ረዳት የለንም፡፡ ሌላኛው ጠሞ አጥማሚ እንዲህ ሲል ይቀጥላል
**********************
- “አንተ አሊ ሆይ! ስል፣ አንተ ሁሴን ሆይ! ስል፣ አንቺ ዘሃራ ሆይ! ስል ይሄ የተውሒድ ጫፉ (ጣራው) ነው፡፡ የተውሒድ ጋሻው ነው፡፡ የተውሒድ ውስጡ (መሰረቱ) ነው፡፡…..”
**********************
እውነታው ግን ከአላህ ውጭ ምንንም ይሁን ማን የለመነ ከሳሪ ነው፡፡ አላህ ስለራሱ እንዲህ ይለናል
يُولِجُ ٱلَّيْلَ فِى ٱلنَّهَارِ وَيُولِجُ ٱلنَّهَارَ فِى ٱلَّيْلِ وَسَخَّرَ ٱلشَّمْسَ وَٱلْقَمَرَ كُلٌّ يَجْرِى لِأَجَلٍ مُّسَمًّى ۚ ذَٰلِكُمُ ٱللَّهُ رَبُّكُمْ لَهُ ٱلْمُلْكُ ۚ وَٱلَّذِينَ تَدْعُونَ مِن دُونِهِۦ مَا يَمْلِكُونَ مِن قِطْمِيرٍ
ሌሊትን በቀን ውስጥ ያስገባል፡፡ ቀንንም በሌሊት ውሰጥ ያስገባል፤ ፀሐይንና ጨረቃንም ገራ፡፡ ሁሉም እተወሰነ ጊዜ ድረስ ይሮጣሉ፡፡ ይህ ጌታችሁ አላህ ነው፡፡ ንግሥናው የእርሱ ብቻ ነው፡፡ እነዚያም ከእርሱ ሌላ የምትግገዟቸው የተምር ፍሬ ሽፋን እንኳ አይኖራቸውም፡፡
ከአላህ ውጭ ስለሚመለኩት ደግሞ ምንም ማድረግ እንደማይችሉ እንዲህ ይለናል
إِن تَدْعُوهُمْ لَا يَسْمَعُوا۟ دُعَآءَكُمْ وَلَوْ سَمِعُوا۟ مَا ٱسْتَجَابُوا۟ لَكُمْ ۖ وَيَوْمَ ٱلْقِيَٰمَةِ يَكْفُرُونَ بِشِرْكِكُمْ ۚ وَلَا يُنَبِّئُكَ مِثْلُ خَبِيرٍ
ብትጠሩዋቸው ጥሪያችሁን አይሰሙም፡፡ ቢሰሙም ኖሮ ለእናንተ አይመልሱላችሁም፡፡ በትንሣኤም ቀን (እነርሱን በአላህ) ማጋራታችሁን ይክዳሉ፡፡ እንደ ውስጠ ዐዋቂው ማንም አይነግርህም፡፡
ይሄ ነው እንግዲህ በአላህ እና ከአላህ ውጭ የሚመለኩት መሃል ያለው ታላቅ ልዩነት፡፡
**********************
እስቲ ሌላ ጥያቄ እንጠይቅ አለምን የሚያስተዳድራት አላህ ወይንስ 12 የሺኣ ኢማሚች?
የሺአ ጠሞ አጥማሚ ኢማሞች እንደሚከተለው ኩፍራቸውን በአደባባይ ይነዛሉ
- “ሰዎች ወደዱትም ጠሉትም እናገረዋለሁ…… በአላህ እና በፋጢማ እምላለሁ….. ዛሬ የአላህ መልክተኛ ምንም ማድረግ አይችሉም፡፡ ስለማይችሉ ግን አይደለም፡፡ መብት ስለሌላቸው እንጂ፡፡ አሚረል ሙእሚኒንም ይህን ማድረግ አይችልም፡፡ የአለማቱ ጌታ አላህም አይችልም፡፡ መላእክቶችም አይችሉም፡፡ የሚችለው ታድያ ማን ነው? በእጁ ሁሉ ውሳኔ እና ማስተናበር ያለው “ሳሂበ ዘማን” (የዘመኑ አስተዳዳሪ 12 የሺአ ኢማሞች) ነው፡፡ ታድያ ወደ ማን ነው የምትዞሩት?”
**********************
ልብ እንበል መሃል በአላህ ብቻ ነው የሚማለው፡፡ አላህ ሁሉን በማድረግ ላይ ቻይ ነው፡፡ ይህን የማያምን ከሃዲ ነው፡፡ ሺአዎች እና ከፊል ሱፍዬች እንደሚሉት “ሳሂበ ዘማን” የሚባል የለም፡፡ አላህ ይህንን ፍጥረተ አለም በመፍጠር፣ በማስተናበር፣ ድካምም አልያዘውም፣ አያንቀላፋምም፣ አያንጎላጅምም፡፡ አንድን ነገር ሲወስን ሁን ይለዋል ይሆናል፡፡
**********************
- “አላሁ (ሱብሃነሁ ወተኣላ) የዚህን አለም የማስተዳደር ስራ ለአውልያዎቹ (12 የሺአ ኢማሞች) ሰጥቷቸዋል፡፡ የግል እና የማህበረሰቡን ጉዳይ በምንጠይቅበት ጊዜ አገባባችን በዚህ ሁኔታ ከሆነ (ማለትም) አለሙ በእጃቸው የሆነ፣ እና ሁሉን በእጃቸው የሆነ ኢማሞች ዘንድ….. እናም እሱ (ኢማም) አንድ ነገር ካለ ይሆናል፡፡”
**********************
አንድን ነገር ሲወስን ሁን ሲለው የሚሆነው ለአላህ ብቻ ነው፡፡ ነገሩ በእጁ የሆነ፣ የንግስና ባለቤት የሆነው ብቸኛው ፈጣሪ ጌታ አላሁ ሱብሃነሁ ወተኣላ ብቻ ነው፡፡ ከዚህ ውጭ ያሉትን ጥቅምንም ለራሳቸው ማምጣት አይችሉም፡፡ ጉዳትን ከራሳቸው ላይ ማስወገድ አይችሉም፡፡
**********************
- “ካንተ ውጭ እኮ ማንም የለንም (ጸሎታችንን ስማን)፡፡ አንተ የአብደላህ አባት (ሁሴን) ሆይ! ዱንያችን እና አኸይራችን ነህ ፡፡ ችግር ባጋጠመህ ጊዜ ወደ ሁሴን ተመልከት (ለምነው)፡፡ ሁሴን ወዳንተ በእርግጥ መጥቶ ጉዳይህን (የፈለግከውን) ይፈፅምልሃል፡፡ ሁሴን ያንተን ጥሪ ለመስማት አማላጅም (አገናኝም) አይፈልግም፡፡”
**********************
ተመልከቱ የአላህን መብት፣ አላህ ብቻውን የተነጠለበትን አምልኮ ሙሉ ለሙሉ አሳልፈው ፍጡር ለሆነው ሁሴን አሳልፈው ሰጡት፡፡ ይህ ነው ሽርክ እና ኩፍር ማለት፡፡
**********************
- “(ሱንዬች ይላሉ) አላህ አንድ ነው፡፡ አላህ ፈጣሪ ነው፡፡ በፍጹም፡፡ አላህ በእርሱ እና በሰዎች መካከል ቀጥተኛ መንገድ እንዲኖር አልፈለገም፡፡ አላህ ይህን ፈልጓል (ሰዎች በቀጥታ እንዳያገኙት እያለ ነው)፡፡”
**********************
ይህ ጠሞ አጥማሚ በሚከተለው የአላህ ቃል እያስተባበል ነው
وَقَالَ رَبُّكُمُ ٱدْعُونِىٓ أَسْتَجِبْ لَكُمْ ۚ إِنَّ ٱلَّذِينَ يَسْتَكْبِرُونَ عَنْ عِبَادَتِى سَيَدْخُلُونَ جَهَنَّمَ دَاخِرِينَ
ጌታችሁም አለ “ለምኑኝ፤ እቀበላችኋለሁና፡፡ እነዚያ እኔን ከመግገዛት የሚኮሩት ተዋራጆች ኾነው ገሀነምን በእርግጥ ይገባሉ፡፡”
**********************
- “አላህ አያድረገውና ችግር ውስጥ ብትወድቅ፣ በሩ ላይ ቁምና “ፋጢማ ሆይ! እርጂኝ” ብለህ አልቅስ፡፡ በእርግጥ ትረዳሃለች፡፡ ”
**********************
أَمَّن يُجِيبُ ٱلْمُضْطَرَّ إِذَا دَعَاهُ وَيَكْشِفُ ٱلسُّوٓءَ وَيَجْعَلُكُمْ خُلَفَآءَ ٱلْأَرْضِ ۗ أَءِلَٰهٌ مَّعَ ٱللَّهِ ۚ قَلِيلًا مَّا تَذَكَّرُونَ
ወይም ያ ችግረኛን በለመነው ጊዜ የሚቀበል፣ መከራንም የሚያስወግድ፣ በምድርም ላይ ምትኮች የሚያደረጋችሁ፤ (ይበልጣልን? ወይስ የሚያጋሩት?) ከአላህ ጋር ሌላ አምላክ አለን? ጥቂትንም አትገሠጹም፡፡
**********************
- (ሙስሊሞች ላይ እንደማሾፍ እያለ እንዲህ ይላል) “አላህ ከደም ስራችን የቀረበ ነው፡፡ ስለዚህ ከአላህ በቀጥታ ጉዳዬቻችንን እንጠይቅ፡፡ አላህ አይሆንም ብሏል (በቀጥታ አትለምኑኝ ብሏል)፡፡ (ሙስሊሙ) ሄዶ እንዲህ ማለት ፈልጓል “አላህ ከደም ስሬ የቀረበ ነው፡፡ መልክተኛ አያስፈልገኝም፡፡ አላህን በቀጥታ እጠይቀዋለሁ፡፡” ይሄ ነስ (ግልጽ) የቁርኣንን ህግ የሚጋጭ ነው፡፡ ያ አላህ ማለት ስህተት ነው (እላለሁ)፡፡ አላህ በቀጥታ አትጠይቁኝ ብሏል፡፡”
**********************
አላህ ግን ስለራሱ “እኔ ቅርብ ነኝ፡፡ የለማኝን ጸሎት በለመነኝ ጊዜ እቀበለዋለሁ፡፡” ሲል ይነግረናል አንደሚከተለው
وَإِذَا سَأَلَكَ عِبَادِى عَنِّى فَإِنِّى قَرِيبٌ ۖ أُجِيبُ دَعْوَةَ ٱلدَّاعِ إِذَا دَعَانِ ۖ فَلْيَسْتَجِيبُوا۟ لِى وَلْيُؤْمِنُوا۟ بِى لَعَلَّهُمْ يَرْشُدُونَ
ባሮቼም ከእኔ በጠየቁህ ጊዜ (እንዲህ በላቸው)፡- እኔ ቅርብ ነኝ፡፡ የለማኝን ጸሎት በለመነኝ ጊዜ እቀበለዋለሁ፡፡ ስለዚህ ለኔ ይታዘዙ፤ በኔም ይመኑ፤ እነሱ ሊመሩ ይከጀላልና፡፡
**********************
እንግዲህ ከላይ እንዳያችሁት የአላህ ባሪያዎች ሺአዎች ማለት እንዲህ አይነት እርኩሶች ናቸው፡፡ አላህ ላይ የሚዋሹ፣ ከአላህ ውጭ የሚለምኑ፣ አለምን የሚያስተዳድሩት ከአላህ ውጭ ኢማሞች አሉ የሚሉ ክህደትን የሚያስተጋቡ ናቸው፡፡ ታድያ እንዴት ይሆን ሀሰን አል በና የኢኽዋኑ መሪ ከነዚህ ሰዎች ጋር ሙስሊሙን አለም አንድ ለማድረግ ሲጥር የነበረው? አሁንም ድረስ በሱንዩ እና በሺአው መካከል መቀራረብ እና አንድ ሆነው ጠላትን መመከት አለባቸው የሚባለው? ሺአዎች ለሱንዩ አለም ክፋ ጠላቶቹ ናቸው፡፡
“ላኢላሃ ኢለላህ ሙሐመዱ ረሱሉላህ የምትለዋ ቃል አህለሱና እና ሺኣን አንድ ታደርጋቸዋለች” ያለው የኢኽዋኑ መስራች ሀሰን አል በና ንግግር ውድቅ እና ቅጥፈት ለመሆኑ ይህ አጭር ቪድዬ የሺአዎችን እውነታ በደምብ ያሳያል፡፡
አላህ በሃቅ ላይ ተሰባሰቡ፡፡ በሃቅ ላይ የተሰባሰባችሁ አንድ ህዝብ ሁኑ ነው ያለን፡፡ እንጂ ኢኽዋኖች እንደሚሉት እንዲህ አይነት ኩፍር ላይ የተጨማለቁ ሰዎችን “አንድ ነን” እንድንል አይደለም፡፡
ሙስሊሞች ሆይ ንቁ፡፡ ቪድዬውን ከዬቱዩብ ሊንክ ለማግኘት የሚከተለውን ሊንክ ይጫኑት
https://www.youtube.com/watch?v=IXRzOVjwwNo&feature=youtu.be
አላህ ሆይ! ሃቅን በሃቅነቱ አሳየን የምንቀበለውም አድርገን፡፡ ባጢልን በባጢልነቱ አሳየን የምንርቀውም አድርገን፡፡

Sadat Kemal Abu Meryem