አላህ እና መልክተኛው (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) የተራገሙበትን
- ቅንድብ መቀንደብ እና ቅንድብ ማስቀንደብ፣
- ዊግ (አርቴፊሻል) ጸጉር መቀጠል እና ማስቀጠል፣
- መንቀስ እና ማስነቀስን
ለምን ይሆን አቅልላችሁ የምታዩት?
አረ አላህ እና መልክተኛው (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) የተራገሙበት ከባድ ጉዳይ ነው፡፡ እህቴ ሆይ! አላህን ፍሪ፡፡ የሰርግ ቀን ነው፣ የደስታ ቀን ነው እየተባለ አላህን ማመጽ መጨረሻው የከፋ ነው፡፡
ከአርሽ እስከ ፈርሽ የአላህ ግዛት ነው፡፡ እንዴት በአላህ ግዛት ላይ አላህ ይታመጻል?
ኢናሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂኡን፡፡ እናንተንም እኛንም አላህ ያስተካክለን፡፡
አሳዛኙ ሸይጧን እንዲህ (ቅንድብ በመቀንደብ፣ ዊግ በመቀጠል …… ) ካልሆነ አታምሩም ብሎ የበታችነትን ስሜት ውስጣችሁ ላይ ፈጥሮ ከአላህ ያጣላችኋላ፡፡ ግን ማወቅ ያለባችሁ አላህ አሳምሮ ነው የፈጠረን፡፡ አላህ እንዲህ ይላል
لَقَدْ خَلَقْنَا ٱلْإِنسَٰنَ فِىٓ أَحْسَنِ تَقْوِيمٍ
ሰውን በጣም በአማረ አቋም ላይ ፈጠርነው፡፡
አላህ ውስጥ እላያቸው እሱን በመታዘዝ ካማሩት ያድርገን፡፡ ከሰይጣንም ጉትጎታና ተንኮል ይጠብቀን፡፡
