ጥያቄ፦ የአልፊርቀቱ አልናጂያ ዋና ዋና ባህሪያት ምንድን ናቸው? የነዚህ ባህሪያት መጓደል ሰውን ከአልፊርቀቱ አልናጂያ ያስወጣልን?
መልስ፦ የአልፊርቀቱ አልናጂያ ዋና ዋና መለያዎች ወይም ባህሪያት በዐቂዳም ሆነ በዒባዳ በስነ ምግባርም ሆነ ከሰው ጋር በመስራት (በሙአመላ) ነቢዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) የነበሩበትን ፈለግ መያዛቸው ነው። በነዚህ አራት ነገሮች ነቢዩን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) አጥብቀው መከተላቸው የአልፊርቀቱ አልናጂያ መለያ ባህሪያት ናቸው።
በዐቂዳ የአላህ ኪታብና የመልክተኛው (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ሱና የሚያመላክቱትን ነው የሚይዙት። በአላህ
አምላክነት (ኡሉሂያ) ፣ በጌትነቱ (ሩቡቢያ) ፣ እና በስሞቹና በባህሪያቱ የጠራ ተውሂድ ይይዛሉ።
ዒባዳንም ነቢዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ይተገብሩ በነበሩበት መልኩ (በሳቸው ፈለግ ) ሙሉ በሙሉ ይተገብራሉ። ዒባዳን በአይነቶቹም ሆነ በባህሪያቱ፣ በወቅቶቹም ሆነ በቦታዎቹ፣ በመጠኖቹም ሆነ በሰበቦቹ (ምክንያቶች) ምንም አዲስ ነገር ዲን ውስጥ አይጨምሩም። ለአላህና ለመልክተኛው ታዛዦችና የአላህንና የረሱልን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ሥርዓት የሚጠብቁ ናቸው። አላህ ያልፈቀደውን ነገር ዲን ውሰጥ በመጨመር ከአላህና ከመልክተኛው ፊት አይቀድሙም።
በስነ ምግባርም (በአኽላቅ) እንዲሁ ከሌሎች ይለያሉ። ጥሩ ስነምግባር አላቸው። ለምሳሌ፦ ለሙስሊሞች በጎ ነገር መውደድ፣ ሆደ ሰፊና ቻይ መሆን፣ ለሰዎች ጥሩ ፊት ማሳየት፣ ጥሩ ንግግር መለገስ፣ ጀግንነትና ሌሎችም ጥሩ ሥነምግባራት መለያ ባህሪያታቸው ናቸው።
ከሰው ጋር በመስራት (በሙዓመላ) ረገድም ከሌሎች ይለያሉ። ግብይታቸው በእውነት (ሲድቅ) እና ግልጽነት (አልበያን) ላይ የተመሠረተ ነው። ነቢዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ለግብይት መሰረታዊ የሆኑትን እነዚህ ሁለቱን ነገሮች አስመልክቶ ሲናገሩ እንዲህ ብለዋል፦ << ተገበያዮች (ሻጭና ገዥ) ሽያጩ ተፈፅሞ እስካልተለያዩ ድረሰ (ሽያጩን ወይም ግዢውን የመተው) ምርጫ አላቸው። (በዚያ ግብይታቸው ላይ) እውነት ከተናገሩና ያለውን ነገር ግልፅ ካወጡ ግብይታቸው የተባረከ ይሆናል። ከዋሹና ያለውን ነገር ከደበቁ ግን ግብይታቸው በረከት ያጣል።>>(ቡኻሪና ሙስሊም)። ሰውየው ከነዚህ ባህሪያት የተወሰነውን ማጓደሉ ከፊርቀቱልናጂያ አያስወጣውም። ይሁን እንጂ ሁሉም በስራው ልክ ነው ደረጃው የሚወሰነው። በተውሂድ ላይ ጉድለት ካሳየ ምናልባትም ከፊርቀቱልናጂያ ሊወጣ ይችላል፥፥ ለምሳሌ፦ ኢኽላስን ማጓደል የመሠለ። ቢድአም እንደዚሁ ነው። ሰውየው ከፊርቀቱልናጂያ ሊያስወጣው የሚችል ቢድዓ ሊሰራ ይችላል።
በአኽላቅና በሙአመላ ረገድ ግን ሰውየው የተወሰነውን ማጓደሉ ደረጃውን ይቀንሳል እንጂ ከፊርቀቱልናጂያ አያስወጣውም።
የአኽላቅን (የስነ ምግባርን)ጉዳይ ዘርዘር አድርጎ መመልከት ያሻል። ከአኽላቅ ውስጥ በዋናነት ሊጠቀስ የሚገባው ከሙስሊሞች ጋር በእውነት (ሐቅ)ላይ አንድነት መፍጠር ነው። አንድ መሆን እንዳለብን ሲያዝ አላህ እንዲህ ይላል፦
۞ شَرَعَ لَكُم مِّنَ ٱلدِّينِ مَا وَصَّىٰ بِهِۦ نُوحًۭا وَٱلَّذِىٓ أَوْحَيْنَآ إِلَيْكَ وَمَا وَصَّيْنَا بِهِۦٓ إِبْرَٰهِيمَ وَمُوسَىٰ وَعِيسَىٰٓ ۖ أَنْ أَقِيمُوا۟ ٱلدِّينَ وَلَا تَتَفَرَّقُوا۟ فِيهِ
ُ
<<ለእናንተ ከሃይማኖት ያንን በእርሱ ኑሕን ያዘዘበትን ደነገገላችሁ፡፡ ያንንም ወዳንተ ያወረድነውን ያንንም በእርሱ ኢብራሂምን ሙሳንና ዒሳንም ያዘዝንበትን ሃይማኖትን በትክክል አቋቁሙ በእርሱም አትለያዩ ማለትን (ደነገግን)፤...>> (አል-ሹራ 42፥13)
እነዚያን ሃይማኖታቸውን የለያዩና አንጃዎች የሆኑትን ነቢዩ መሐመድ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ከነሱ እንዳልሆኑና ከነሱ ንፁህ እንደሆኑ አላህ (ሱብሐነሁ ወተአላ) ተናግሯል። አላህ እንዲህ ይላል፦
إِنَّ ٱلَّذِينَ فَرَّقُوا۟ دِينَهُمْ وَكَانُوا۟ شِيَعًۭا لَّسْتَ مِنْهُمْ فِى شَىْءٍ ۚ
َ
<<እነዚያ ሃይማኖታቸውን የለያዩና አሕዛብም የኾኑ አንተ በምንም ከእነሱ አይደለህም፡፡>> (አል-አንዓም 6፥159)
ሰለዚህ የቃል አንድ መሆንና የልቦች መቀራረብና አንድነት ከፊርቀቱልናጂያ (አህሉሱና ወልጀማዐ) ባህሪያት ዋነኛው ነው። በኢጅትሃድ ጉዳዮች በመካከላቸው ልዩነት ቢታይ እንኳ ይህ ልዩነታቸው ለእርስ በርስ ጥላቻና ጠላትነት አይዳርጋቸውም። በመካከላቸው የኢጅቲሃድ ልዩነት ቢከሰትም እንኳ ወንድማማቾች መሆናቸውን ያምናሉ። ሌላው ቀርቶ ውዱእ የለውም ብለው የሚያስቡትን ኢማም ተከትለው ይሰግዳሉ። ኢማሙ ውዱእ አንዳለው ያምናል። ለምሳሌ አንድ ሰው የግመልን ስጋ የበላ ኢማም ተከትሎ ይሰግዳል። በዚህ ኢማም እምነት የግመል ስጋ መብላት ውዱእ አያፈርስም። ተከትሎት የሚሰግደው (ማእሙም) ግን የግመል ስጋ መብላት ውዱእ እንጀሚያበላሽ ያምናል። ከመሆኑም ጋር ከዚህ ኢማም ተከትሎ መስገድ እንደሚቻል ያምናል። ኢማሙን ትቶ ለብቻው ቢሰግድ ሰላቱ ትክክል እንዳልሆነም ያምናል። ይህ ሁሉ የሚሆነው በኢጅቲሃድ ጉዳይ መለያየት እውነተኛ መለያየት እንዳልሆነ ስለሚያምኑ ነው። በኢጅቲሃድ ጉዳይ የተለያዩ ሰዎች እያንዳንዳቸው መከተል ግዴታ የሚሆንባቸውንና ሊተዉት የማይችሉትን ማስረጃ (ደሊል) ነው የተከተሉት። አንድ ወንድማቸው በያዘው ማስረጃ ምክንያት በአንድ ተግባር ላይ ከነሱ የተለየ አቋም ቢይዝ ይህ ሰው በእውነቱ ከነሱ ጋር አንድ ሆነ እንጂ ተለየ ብለው አያምኑም። ምክንያቱም እነሱም ሰው በማንኛውም መልኩ በማስረጃ እንዲሰራ ጥሪ ስለሚያደርጉ ነው። ስለዚህ በራሱ ባለው ማስረጃ መሠረት ከነሱ ልዩነት ቢያሳይ ከነሱ ጋር አንድ ሆነ እንጂ አልተለየም። ምክንያቱም እሱም የተከተለው እነርሱ ወደ ሚጣሩትና ወደ ሚያመላክቱት በቁርአን በሐዲስ ማስረጃ መስራትን ነው። በእንደዚህ አይነት ጉዳዮች በሰሃቦች መካከልም ልዩነቶች ተፈጥረው እንደነበር ለእውቀት ባለቤቶች ግልፅ ነው። በነቢዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ዘመን እንኳ ሳይቀር፥፥ ነቢዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) አንዳቸውንም አልተቆጧቸውም።
ነቢዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ከአህዛብ ዘመቻ ሲመለሱ ጅብሪል መጣቸውና ቃልኪዳንን ወዳፈረሱ ወደ በኒ ቁረይዟ እንዲዘምቱ ሲያዛቸው ነቢዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ለሰሃቦቻቸው ጥሪ አደረጊላቸው። << በኒ ቁረይዛ ሳትደርሱ ማናችሁም የዐስር ሰላትን እንዳትሰግዱ>> በማለት። ሰሃቦች ከመዲና ወደ በኒ ቁርይዛ ተንቀሳቀሱ። የዐስር ሰላት መንገድ ላይ እያሉ ደረሰባቸው። ከፊሎቹ በኒ ቁርይዛ እስከሚደርሱ ድረስ የሰላት ወቅቱ ቢያልፍባቸውም። ሰላቱን አዘገዩት። ምክንያቱም ነቢዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) << አንዳችሁም በበኒ ቁረይዛ እንጂ ዐስርን እንታስግዱ>> ብለዋልና። ከፊሉ ደግሞ ሰላቱን በወቅቱ ሰገደ። ነቢዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ከኛ የፈለጉት ቶሎ ብለን ለዘመቻው እንድንወጣ ነው እንጂ ሰላትን ከወቅቱ እንድናዘገየው አይደለም በማለት። ትክለኞቹ እነዚህ ናቸው። ነገር ግን ነቢዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) አንዱንም ወገን አልተቆጡም። በዚህ የግንዛቤ ልዩነት ምክንያት አንዱ በሌላው ላይ ጥላቻ አላሳደረም። ስለዚህም አህሉሱና ነን የሚሉ ሙስሊሞች አንድ ህዘብ የመሆን ግዴታ አለባቸው። በአንጃዎች መከፋፈል የለባቸውም። አንዱ ወደ አንደኛው አንጃ ሌላው ወደ ሌላኛው አንጃ ራሱን መፈረጅ የለበትም። እርስ በርሳቸውም በምላስ ጦር መወጋጋት የለባቸውም። በኢጅቲሃድ ምክንያት በተፈጠረ ልዩነት መጠላላት የለባቸውም። ሁሉንም አንጃዎች ስማቸውን ማውሳት አስፈላጊ አይደለም። አእምሮ ያለው ሰው ጉዳዩ ይገባዋልና።
አህሉሱና ወልጀመዐ የሆኑ ሙስሊሞች በቁርአናዊና ሐዲሳዊ አንቀፆች (ኑሱስ) ግንዘቤ ምክንያት በመካከላቸው ልዩነት ቢፈጠርም አንድነታቸውን የመጠበቅ ግዴታ አለባቸው። ለአላህ ምስጋና ይግባውና ይህ ነገር (የሚያጨናንቅ ሳይሆን) ስፋት ያለው ነው። ዋናው ነገር የልብና የቃል አንድ መሆን። የሙስሊሞች ጠላቶች የሙስሊሞችን መከፋፈል እንደሚፈልጉ ግልፅ ነው። ጠላትነታቸውን በግልፅ ያወጁትም ሆኑ ላይ ላዩን ለኢስላምና ለሙስሊሞች ወዳጅ መስለው ውስጡን ግን ቀንደኛ ጠላት የሆኑትም ጭምር። ይህን ባህሪ መላበስ አለብን። የፊርቀቱልናጂያ ባህሪ የሆነችውን በአንድ ቃል ላይ አንድነትን የመፍጠር ባህሪ።
【ሸኽ መሐመድ ኢብኑ ሷሊህ አል-ኡሰይሚን ረሒመሁላህ】
posted by Taju Nasir in facebook