Daniya M. umu Abdullah
بسم الله والصلاةُ والسلامُ على رسول الله
سبحان الذي زين الرجال باللحى والنساء بالذوائب
أما بعد فسلام الله عليكم ورحمة وبركاته
//ለሙስሊም እህቶቸ አጠር ያለች ምክር//
ሴቶች አላህ አክብሮናል አልቆናል የሰዉ ልጅ መሆናችንንም አረጋግጦልናል መብታችንን አስከብሮልናል ከጨለማዉ አለም ወደ ብርሀን በኢስላም ገብተናል በቁማችን መገደሉ መደፈሩ መቀበሩ መንቋሸሹ ቀርቶልናል ከአንድ ሀገር ገዥ ባለ ስልጣን የበለጠን መብት የበለጠን ክብርን በኢስላም ተጎናፅፈናል አላህም በስማችን እራሱን የቻለ የቁርአን ሱራ አዉርዶልናል ለኛ ትልቅ ሸረፍ ነዉ ለጌታችን አላሁ ሱበሀነሁ ወተአለ ላቅ ያለ ክብር እና ምስጋና ይገባዉ!
ሙስሊም ሴት በዲናችን የተለየ ቦታ እንደተሰጣት ሁሉ ትልቅ ሃላፊነትም አለባት። እሱም የትውልድ አስተማሪ ለልጆቿ የመጀመሪያ ትምህርት ቤት በመሇኗ። ስለዚህ ያላት ሚና እራሷን በ ኢልም (እውቀት) አንጻ ከዛም ለትውልድ መትረፍ ነው። ይህን ማድረግ የምትችለው ዲኗን በሚገባ ስታውቅ ነው። ያለ እውቀት የሚሰሩ ነገሮች ሁሉ ስህተታቸው የበዛና ትክክል ያልሆኑ ነገሮችንም ሊያካትቱ ይችላሉና ከምንም በላይ የምታስቀድመው እውቀትን ነው።
[العلم قبل القول والعمل]
[እውቀት ከንግግርም ከተግባርም ይቀድማል] ሙስሊም ሴቶች ምንም ወደኃላ ሳይሉ ዲናቸውን አጥብቀው መማርና ንግግራቸውም ሆነ ተግባራቸውም በእውቀት የታነጸ መሆን አለበት። አወ! ሸሪዓዊ እውቀትን በመለግ ላይ ጥረት ማድረግ በማንኛውም ሙስሊም ግዴታ ነው።
ረሱላችን (አለሂ ወሰላቱ ወሰላም) እንዲህ ብለዋል "ሸሪዐዊይ እውቀትን መፈለግ በማንኛውም ሙስሊም ላይ ግደታ ነው።"
እንዲሁም ከታላቁ ሶሀብይ ሙአውያ ኢብኑ አቢ ሱፍያን እንደተወራው የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል "አላህ መልካም የሻለትን ሰው እውቀትን ይሰጠዋል ወይም የድን ግንዛቤ ይሰጠዋል።"
ስለዚህም ውድ አህቶቼ ዲናችንን በማወቅ ላይ ልትሽቀዳደሙ ይገባል አላህ መልካም ከሻተለት ባሪያው ለመሆን ኢልምን በመፈለግ መድከም ይኖርባችኃልና። ሸሪዓው እውቀት ቀዳሚ ነገር ሲሆን ግንዛቤው ሲኖር ደግሞ ጥቅሙ የጎላ ነው። ኢብኑ ተይሚያህ (ረሂመሁላህ )እንዲህ ብለዋል [ሸሪዐዊ እውቀት ፣ሪፍቅ(ልስላሴ) ፣ሶብር/ ትዕግስት ፣በጥሩ ማዘዝና ከመትፎ መከልከል እውቀት ቀዳሚ ነው ። ሊሎቹ ከ እውቀት በኃላ የሚመጡ ናቸው።
ረሱል አልሂ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም] ከምንም በላይ አል
እውቀትን እንዲጨምርላቸው ዱአ ያደርጉ ነበር ። አላህም አዟቸዋል ለዚህም ማስረጃው፦
《 وقل رب زدني علما 》
《ጌታዬ ሆይ!እውቀትንም ጨምርልኝ።በል(20:114)
እዉቀትን በመፈለግ ላይ መበረታታት እዉቀት ስትፈልግ ከኩራት ከሪያእ ከአይናፋርነት በሪእ የጠራች መሆን ይኖርባታል።
አላህ ከሀቅ አያፍርም እና እሷም በዲኗ ላይ ተፈቁህ እንዲኖራት ልታፍር አይገባትም የሙእሚኖች እናት የሆነችዉ አዒሻ ቢንቱ ሲዲቃ (ረድየሏሁ አንሃ)እንዲህ ትላለች፦
"የአንሷር ሴቶችን አላህ ይዘንላቸዉ ኢልምን ለመማር ለተፈቁህ እፍረት አይዛቸዉም ነበር!"
ዲኗን ስትማር የአላህን ፊት ፈልጋበት እስከሆነ ድረስ ብዙ ቱርፋቶችም እንዳሏት ልትዘነጋ አይገባትም!የአላህ መልዕክተኛም (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም)እንዲህብለዋል፦
من سلك طريقاً يلتمس فيه علما سهل الله له به طريقاًإلى الجنة
እዉቀትን በመፈለግ ላይ የተጓዘ የተንቀሳቀሰ ሰዉ አላህ ለሱ የጀነትን መንገድ ያገራለታል!
{እህቴ አስታዉሺ ግብሽ ጀነት መሆኑን}
ከእውቀት በመቀጠል፦ እዉቀቱን ከያዘች ቡኃላ ወደ ተግባሩ ትመጣለች ለሁሉም ነገረ መርሀላ እንዳለዉ ሁሉ ለዚህም ጉዞዋ ያወቀችዉን ወደ ተግባር መቀየር ይኖርባታል! አዉቀሽም ሳትሰሪይ አስተላላፊ ከሆንሽ የአላሁ ሱበሀነሁ ወተአለ ንግግር አስታዉሺ ተቆጠቢ!
[يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا لِمَ تَقُولُونَ مَا لَا تَفْعَلُونَ]
[እናንተ ያመናችሁ ሆይ! የማትሠሩትን ነገር ለምን ትናገራላችሁ?]
እናም ያወቀችውን ከመናገሯ በፊት በተግባር ማሳየት ይጠበቅባታል። እውቀት ያለ ተግባር ከንቱ ነውና።
ሌሎችን ከማስተማር ይልቅ የራስዋን ተግባር ባሳመረች ጊዜ የሚመለከቷትም የሷን ተግባር ይከተላሉ። ከሁሉም አስቀድማ ነፍሷን ለጌታዋ ታዛዥ ማድረግ ግዴታ ይሆንባታል እሷ ያውቀችውን በተግባር ካሳየች ሌሎችን ማስታወስ ይኖርባታል።ከመጥፎ መከልከል በጥሩ ማዘዝ እና መሰል ኢስላም የሚያዛቸውን ተግባሮች ማስተማር ይጠበቅባታል።
ከእውቀት ከተግባር በመቀጠል፦ ከተማረችም ከሰራችበትም ወደ ቀጣዪ መርሀላ ትገባለች እሱም ወደ ማስተማሩ የተማረችዉን ለሌሎች ማስተላለፍ እንዳለባት ግልፅ ነብያዉይ ሀዲስ አለ ~:
بلغوا عني ولو آية
ከእኔ የሰማችሁት አንድ አያ/አንቀፅ/ቢሆንም አስተላልፉ!
ይሄን ሁሉ አካሄድ ስትጓዝ የሚቀራት ትንሽ ነገር ብቻ ቢሆንም የተማረችበት ሰዉ በታማኝነቱ በአቂዳዉ የተጣራ ታማኝ ሰዉ ሊሆን ይገባዋል! ኢብኑ ኡመር አላህ መልካም ስራቸዉን ይዉደድላቸዉ እና እንዲህ ይላሉ
ان ابن عمر قال دينك دِينك إنه لحمك ودمك خذ عن الذين استقاموا ولا تأخذ عن الذين مالوا
ዲንህ ስጋህም ደምህም ነዉ እስቲቃማህ/ፅናት ካላቸዉ ሰወች ዉሰዱ በዲን ላይ መገለባበጥን ከሚያበዙ ሰዎች አትማሩ!
{እህት በተለይ አሁን ባለሽበት ጊዜ እስተንትኚ! ዲንሽን ከማን መማር እንዳለብሽ ጠንቅቀሽ እወቂ!}
ተጨማሪ ነጥቦች፦ ከዛም በመቀጠል አደቧን ስነ_ስርአቷን፤ ሀያእዋን እሷን ከሚበልጡ ሰዎች ከኡመሀተል ሙእሚኒን መውረስ ይገባታል።
የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ አለሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፦"?ለሁሉም ሀይማኖት ለየት የሚያደርገው ስነ ምግባር አለው ኢስላምን ለየት የሚያደርገው አኽላቅ (ሀያዕ)ነው ብለዋል።
[ ኢብኑ ማጃዕ ዘግበውታል]
ሁሌም በሀያእ የተዋበች ልትሆን ይገባታል ! የአላህ መልእክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፦
الحياء لا يأتي إلا بخير
"አይናፋርነት መልካም ነገርን እንጂ አያመጣም!"
{እህቴ ሆይ! ከእኩይ ተግባር ለመላቀቅ ሀያእ ቢስ ከመሆን ተቆጠቢ}
ወደ ማይመለከታት ነገር አለመቀልበስ
ይሄንም ተመልክቶ የአላህ መልእክተኛ እንዲህ በማለት ተናግረዋል፦
عن النبي صلى الله عليه وسلم قال፦ من حسن إسلام المرء تركه ما لا يعنيه
"የአንድ ሰዉ የኢስላሙ ማማር የማይመለከተዉን ነገር መተዉ ነዉ!"
{የማይመለከትሽ ዉስጥ አትግቢ የሚመለከትሽ ሆኖ ግን የተውሽው(የረሳሽው)ብዙ ነዉና}
ወሳኝ ነጥቦች፦ ፊትና በበዛት ሰዓት ወደ ቁርአን እና ሀዲስ መመለስ አለባት በዘመናችን ያሉ ታላቁ ሸይኽ ፈዉዛን ኢብንፈዉዛን እንዲህ ይላሉ፦
قال شيخ صالح الفوزان حفظه الله "لا نجاة من الفتن إلا بطلب العلم
ከፊትና ፈላህ ነጃ መዉጫ መንገድ የለም እወቀትን ኢልም በመፈለግ ቢሆን እንጂ!
{አሁንም አስታውሺ! የነገራቶች መሰረቱ ኢልም መሆኑን ደጋግመሽ ለራስሽ ንገሪ}
ሀቅ ላይ እስካለች ድረስ በሀቅ ላይ መፅናትን አላሁ ሱበሀነሁ ወተአላ ፅናቱን እንዲሰጣት ልትማፀነዉ ይገባታል። እንዲሁም እራሷን አሳንሳ ለማይ አለመሞከር። ሴት ነኝ በማለት በኢስላም ሴት ልጅ ለውጥ እዳላመጣች አድርጎ ማሰብ ይህ ትልቅ ስህተት ሲሆን ይህን ችግር ገፎ በመጣል የሰሀቦችን ፈለግ መከተል
አላሁ ሱብሀነሁወ ተአላ በተከበረው ቁርአኑ እንዲህ ይላል፦ ["ከወንድ ወይም ከሴት እርሡ አማኝ ኾኖ በጎን የሰራ መልካም ኑሮን በዕርግጥ እናኖረዋለን ይሰሩት ከነበረው ነገር በመልካሙ ምንዳቸውን እንመነዳቸዋለን።"]
(16፡97)
በሂጃቧ የተዋበች እና የታዘዘችበት ነገር መሆኑንም ልትዘነጋ አይገባትም! በሱም ልትደራደርበት አትሞክር። ከሰለፎቻችን የአንዲትን ድንቅ እንስት ጥንካሬዋን ብንመለከት ለሴቶች ጥንካሬን ይጨምርልናለል እናም አጠር ባለ መልኩ ታሪኩ እንዲህ ነዉ፦
ተመልከቱ፡- ሐፍሳ ቢንት ሲሪን(አላህ ይዘንላትና) ባልቴት ሆናም ፊቷ በሂጃብ ትሸፍን ስለነበር እንዲህ አሉዋት፡-"በዚህ እድሜ ለምን ፊትሽ ትሸፍኝያለሽ አላህ በቁርአኑ እነዛን ባልቴቶቹ ሴቶች ፊታቸውን በሂጃብ ባይሸፍኑ ምንም ችግር የለባቸውም ብሎ የለ?" አሏት
وَالْقَوَاعِدُ مِنَ النِّسَاءِ اللَّاتِي لَا يَرْجُونَ نِكَاحًا فَلَيْسَ عَلَيْهِنَّ جُنَاحٌ أَنْ يَضَعْنَ ثِيَابَهُنَّ غَيْرَ مُتَبَرِّجَاتٍ بِزِينَةٍ
"ከሴቶችም እነዚያ ጋብቻን የማይፈልጉት ተቀማጮች (ባልቴቶች)፤ በጌጥ የተገለፁ ሳይኾኑ
የላይ ልብሶቻቸውን ቢጥሉ በእነሱ ላይ ኀጢአት የለባቸውም፡፡" (እን-ኑር፡60)
ድንቋና እንቋ ሐፍሳም፡ "የቁርአኑ አንቀፅ ጨርሱት!" ትላቸው ነበር፡፡
የቁርአኑ መጨረሻ፡
وَأَنْ يَسْتَعْفِفْنَ خَيْرٌ لَهُنَّ وَاللَّهُ سَمِيعٌ عَلِيمٌ
" ግን መጠበቃቸው ለእነርሱ የተሻለ ነው፡፡ አላህም ሰሚ ዐዋቂ ነው፡፡"
{እህቴ አስታዉሺ የዚህችን አዛዉንት መልስ ጥቡቅነትን ንፁህነትን የጌታዋን አምር መጠበቅን ባልቴትም ሆና ፈላጊም እንደማይኖራት አዉቃ እንዲህ ነበረች እናንተ ቆነጃጂት ወጣት እህቶች የት ነዉ ያላችሁት!?}
መታለል አያስፈልግም!፦ዛሬ ተኩላዎች በበዙበት አለም አንቺ ከማን ታንሻለሽ ብለዉ እራቁቷን እንድትሄድ የሚገፋፏት ምእራባዉያን ሁሉ ለሷ ካበደ ዉሻ የበለጠ ጠላቶቿ መሆናቸዉን ልትዘነጋ አይገባትም!
ከሂጃባ አዉጥተዉ አላህ በሰጣት ፀጋ ኒዕማ መጫወቻ ሊያደርጓት እንጂ ለሌላ አይደለም እህቴ ልብ ልትይ የማይገባሽ ነገር ወደድንሽ ብለዉ አንቺን የ1 ብር ፌስታል ማስታዋወቂያ የርካሾች እርካሽ ያደርጉሻል! የሱበሀን አሏህ እስኪ አስቢዉ ከፌስታል ያነሰ ምን አለ ? ከገባሽ አንቺንም እንደዛዉ ሊያደርጉሽ ነዉ ጥረታቸዉ ሸረፍን ክብርን ከፈለግሽ ሳታመነትይ ወደ ሐይማኖትሽ ተመለሺ! ኡመር አላህ መልካም ስራቸዉን ይዉደድላቸዉ እና እንድህ ይላሉ፦
نحن قوم أعزنا الله بالإسلام فإذا ابتغينا العزة بغيره أذلنا الله
"እኛ በኢስላም ልቅናን ሸረፍን ክብርን የተጎናጸፍን ህዝቦች ነን ከኢስላም ዉጭ ልቅናን ከፈለግን አላህ ያዋርደናል!"
{ዉዷ እኛ ዛሬ ከንግግር እስካለባበስ በሙሉ ሂወታችን በባህታዉያን ስልጣኔ ቀይረነዋል ድናችን ሙሉ ሁኖ ሳለ አሁንም ካልተመለስን ተዋራጆች ነን እመኚኝ!}
በሌላ በኩል ደግሞ የሸይጧን መጫወቻ ልትሆኚ አይገባሽም አላህ የሰጠሽን ዉበት በመቀያየር ከጌታሽ ጋር መጣላት የለብሽም ሸይጧን ጠላትሽ ነዉ ጠላት አድርገሽ ያዥዉ! ይሄንንም የአላህን ቃል አስታዉሺ!
إِنَّ الشَّيْطَانَ لَكُمْ عَدُوٌّ فَاتَّخِذُوهُ عَدُوًّا ۚ إِنَّمَا يَدْعُو حِزْبَهُ لِيَكُونُوا مِنْ أَصْحَابِ السَّعِيرِ
"ሰይጣን ለእናንተ ጠላት ነው፡፡ ስለዚህ ጠላት አድርጋችሁ ያዙት፡፡ ተከታዮቹን የሚጠራው ከእሳት ጓዶች እንዲኾኑ ብቻ ነው፡፡"
በተመሳይ! ኢኽቲላጥ ባለሽበት ቦታ ሁነሽ ላንች መህረምሽ ያልሆነ ሰዉ ጋር ለብቻሽ ከመቀመጥ ተገለይ! ይህ ጉዳይ በአሁኑ ጊዜ ነብያዊይ ሀዲስ ከመኖሩም ጋር ተዘንግቷል የአላህ መልእክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም)እንዲህ ብለዋል፦
ألا لا يخلون رجل بامرأة إلا كان ثالثهما الشيطان
"አዋጂ አንድት ሴት ከአንድ ወንድ ጋር አትቀማመጥም ሶስተኛቸዉ ሸይጧን ቢሆን እንጂ!"
[ጠላትሽ ሁልጊዜም ጠላትሽ ነዉ ና ተጠንቀቂለት]
ሴት እንደ ወንድ ሁሉ ከሀራም ነገር አይንን መስበርና ብልትን መጠበቅ ትታዝዛለች። "ለምእምናን ንገራቸው: ዓይኖቻቸውን (ያልተፈቀደን ከማየት) ይከልክሉ፣ብልቶቻቸውንም ይጠብቁ ፣ይህ ለነሱ የተሻለ ነው ፣አላህ በሚሰሩት ሁሉ ውስጥ ዐዋቂ ነው።" ~ዓይንን መስበር በተመለከተ ታላቁ ዓሊም ኢበኑል ቀይም (አል—ጀዋቡል ካፊ) በተሰኝዉ መፀሀፍቸው ውሰጥ (ገጽ:129—135)እንዲህ ብለዋል እይታን መጠበቅ ብልትን የመጠበቅ መሰረት ነው ፣ ዓይኑን የለቀቀ ሰው በእርግጥ ራሱን ጥፍት ውስጥ ጥሏል፣ (ነብዩ ስነላሁ አለይሂ ወሰለም ) እንዲህ ብለዋል :—"ዐሊይ ሆይ! እይታን እይታ አታስከትልበት ፣ የምትፈቀድልህ የመጀመሪያዋ ናት ።" ሳይታስብ በድገት የሚከሰተውን እይታ ማለታቸው ነው ። ስለሆነም በአሁኑ ዘመን የሙስሊም ሴቶች ሚና ከሀራም ነገር ዓይንን መስበር ብልትን መጠበቅ አለብን በተለይ ወጣቶች።
●እነዚህን ማድረግ ከቻልሽ አጠር ያለች ምክር ልጨምርልሽ፦
■ ክርክርን ደረቅነትን አታብዢ ይሄም ጉዳይ ላንቺ የልብ መፈሰድ ሰበብ ሊሆን ይችላል እና!
■ለእህቶችሽ (ለጓደኞችሽ) መልካም ፈለግ አርአያ ሁኚላቸዉ!
■ኩራትን አትላበሺ ኩራት ከሰይጣናዊ ተግባር አንዱ ነዉ ተዋዱእን መተናነስን ተላበሺ ድልን ትትጎናፅፉያለሽ
■የባህታዉያንን አለባበስ አረማመድ አመጋገብ የኑሮ ዘይቤ ከመከታተል ተቆጠቢ ነብያዉይ ግልፅ ሀዲስም ሰፍሮበታልና ! የአላህ መልእክተኛ ከሆኑ ህዝቦች ጋር የተመሳሰለ ከነሱ ነዉ ብለዋል! መሆንን ትሻለሽን እህት አለሜ? መቸም ሰፍሮበታልና መልስሽ አልፈልግም መሆኑን! እንግዳዉስ ሰለፎችን ሞዴልሽ አድርጊ!
■ተግባርሽ በኢልም የተመሰረተ ይሁን የሽርክ የኹራፋት ቦታወችን እራቂ ስራሽ ሁሉ ልክ አዉሎ ንፋስ እንደበተነዉ አመድ እንዳይሆን ተጠንቀቂ!
■በሀገራችን ያሉ ተኩላወች ሊያታልሉሽ አይገባም ፊዳከ በሚል ስም ፊዳ እንዳያደርጉሽ ከነሽዳ ከመንዙማ ከተሰዉፍ በርእ ሁኚ! የነብዩ ወዳጂ የሆነ አዋጁን ይስማ ይተግብር አላህ ይሄን ብሎናል!
قُلْ إِن كُنتُمْ تُحِبُّونَ اللَّهَ فَاتَّبِعُونِي يُحْبِبْكُمُ اللَّهُ وَيَغْفِرْ لَكُمْ ذُنُوبَكُمْ ۗ وَاللَّهُ غَفُورٌ رَّحِيمٌ
በላቸው፡- «አላህን የምትወዱ እንደኾናችሁ ተከተሉኝ፤ አላህ ይወዳችኋልና፡፡ ኀጢኣቶቻችሁንም ለናንተ ይምራልና፡፡ አላህም መሓሪ አዛኝ ነው፡፡»
■ከእኩይ ተግባሮች እራቂ የትም ሁነሽ አላህ እንደሚያይሽ አትዘንጊ!
■ጥርት ያልሽ ሰለፊይ ሴት ሁኚ በስሙ ብቻ መጠራትሽ ስራሽ ወደኋላ ካስቀረሽ ሰለፊይ ሴትን ልትሆኚ አትችይም!
ኢማም አልዋዲዒ የሰለፍያን ሴት ዉድነት ሲናገሩ እንዲህ ይላሁ የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጡ ዉዶች ናቸዉ!
<<ዉድ ሁኝ>>
■ኸይር ሲመጣ አመስጋኝ ሸር ሲመጣ ሶብርን ትእግስትን ተላበሺ!
■ለትዳር አጋር ሲመጣልሽ ማንነቱን በደንብ አጣሪ ዲኑን አኽላቁንም አትዘንጊ!
{ቂለ ወቃለ ንግግሮችን ቦታ አትስጪ}
■ሰአትሽ ሂወትሽ ነዉ እና ተጠቀሚበት በከንቱ አታሳልፊዉ በተለይ ሶሻል ሚዲያን ነጋ ጠባ አትከታተይ እሱ ኸይር እንዳለዉ ሁሉ ሸርም አለዉ!
■ያለ ኢልም ምንም ለዉጥ የለም እና የግባችን መነሻ ኢልም መገብየት መስራት ማስተማር ነዉ አላህ ያግራልን!