Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

የዚህ አመት ረመዳን አለቀ እንጂ አላህን ማምለክ አላለቀም

የዚህ አመት ረመዳን አለቀ እንጂ አላህን ማምለክ አላለቀም።
አላህ ለነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ሞት እስኪመጣቸው ተገዛኝ ብሎ እንዲህ ሲል ያዛቸዋል
وَاعْبُدْ رَبَّكَ حَتَّىٰ يَأْتِيَكَ الْيَقِينُ
"እውነቱም (ሞት) እስኪመጣህ ድረስ ጌታህን ተገዛው"
የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ ሲሉ አስተምረዋል
"የአደም ልጅ ሲሞት ከ3 ነገር በቀር ስራው ይቋረጣል"
ከዚህ ሀዲስ የምንማረው ከዚህ አርስት ጋር የሚሄደው አንድ ሰው ሞት እስኪመጣው ድረስ የኸይር በሮችን ሁሉ ሊተገብራቸው የሸር በሮችን ሊርቃቸው ይገባል።
ውድ የአላህ ባርያዎች ሆይ! ሌሎች ሀይማኖት ላይ ያሉ ሁሉ ሙስሊሞች በፆም ወቅት ምን ያህል ወደ ጌታቸው ትዕዛዝ ተጎታችና ፈፃሚ እንደሆኑ መስክረዋል።
ምንኛ አምሮብን ነበር በረመዳኑ ወር፣ አላህ የረመዳን ወር ጌታ፣ ከረመዳንም ውጭ ትእዛዙ ሊከበር ክልከላው ሊራቅ ይገባል።
በረመዳን ብቻ አላህን ሲያመልክ የነበረ፣
ይሀው የዘንድሮ ረመዳን አልቋል፣
በረመዳንም ከረመዳን ውጭም አላህን የሚያመልክ፣
እነሆ አላህ ህያው ሞት የማይነካውን እያመለከ ነውና፣
በዚሁ መንገድ ላይ ሞት እስኪመጣው ሊፀና ይገባዋል።
አላህን ሞት እስኪመጣቸው ፀንተው ከሚያመልኩት ያድርገን።