የቂያም ቀን ተቃርቧል!!
ይህ ምስሉ ላይ የምታዩትን ሰው ሷሊሕ አልመጛሚሲይ ይባላል። የመስጂዱል ቁባ ኢማም እና ኸጢብ ነው። በፌስቡክ ላይ በርሱ ስም የአማርኛ ፔጅ ተከፍቶለት ሰዎች ዘንድ እየተዋወቀ ይገኛል። አንዳንዶቻችሁ ወደ ቁባ መስጂድ በመሄድ ሙሃደራዎቹን ታደምጡ ይሆናል። አንዳንዶቻችሁ ደግሞ ጭራሹን ላታውቁት ትችሉ ይሆናል።
ይህንን ስለርሱ የሚያትት ፅሁፍ ለመፃፍ ሳስብ ምናልባትም ብዙ አድናቂዎቹ ሊቀየሙኝ እንደሚችሉ አይጠፋኝም። ጭራሽ የማያውቁት ደግሞ ስለርሱ መነገሩ ምንም ፋይዳ እንደሌለው ያስቡ ይሆናል። ነገር ግን እኔ የአላህን እንጂ የሰውን ውዴታ ፈልጌ አልከተብኩትም። ይህን አንብበው በፌስቡክ በአማርኛ ስራዎቹን እየተረጎሙ የሚያሰራጩት ሰዎች ወጥመድ ላይ ህዝቡ እንዳይወድቅ ብሎም በዩቱዩብም ይሁን ቁባ መስጂድ በመሄድ የርሱን ትምህርት የሚከታተሉትን ሰዎች ከዚህ ሰውየ ለማስጠንቀቅ ይሆነኝ ዘንድ የአላህን ፊት ከጅዬበት ብቻ እና ብቻ ነው።
ይህ ሰው በቅርቡ MBC በተባለው ቻናል ላይ ቀርቦ በርካታ ከሸሪዓችን የሚጋጩ ነገራቶችን ተናግሯል። ይህ የርሱ እምነት መሆኑንም አስምሯል። ከተናገራቸው አስደንጋጭ እና እኛን ጨምሮ ሌሎች የርሱን ሙሃደራ የሚያደምጡ ሰዎችን አደጋ ላይ ከሚጥል ፈታዋዎቹ ውስጥ ሙዚቃ በኢስላም ሐራም (ክልክል) አለመሆኑን መናገሩ ነው። በርግጥ ሰውየው ይህን መናገሩ ከርሱ የሚጠበቅ ቢሆንም ለአድናቂዎቹ ግን ቆም ብለው ማስተዋል እንደሚገባቸው የሚጠቁም ነው። የኔም ስራ ይህ ነው። ኢንሻ አላህ።
መጛሚሲ (አላህ ሂዳያ ይስጠውና) አላህ ሱብሓነሁ ወተዓላ በቁርኣኑ የከለከለው ሙዚቃን ሳይሆን መዝፈንን ነው። ብሏል። አክሎም በቁርአን ውስጥ የተጠቀሰው ወሬ (የሚለው ቃል) ሙዚቃ ወይንም የሙዚቃን መሳሪያ አይደለም። እርሱን ሐራም የሚያደርግ ደግሞ በቁርኣን ላይ የለም። አላህ ሙዚቃን ክልክል ቢያደርግ ኖሮ «ሙዚቃ መሳሪያን አትቅረቡ» ብሎ በቁርአኑ በነገረን ነበር። ሲል ይደመጣል።
ከራሱ አንደበት ለማድመጥ
በፅሁፍ (ዐረብኛ)
http://bit.ly/25pTdUv
በቪዲዮ (ዐረብኛ) (ከ1፡45 ጀምሮ)
https://www.youtube.com/ watch?v=vwv09AGUUMs
የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም የቂያም ቀን ሲቃረብ ይህ እንደሚከሰት እንዲህ ብለውን ከ1400 አመታት በፊት ነግረውን ነበር
قال النَّبِيَّ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ ፥
(لَيَكُونَنَّ مِنْ أُمَّتِي أَقْوَامٌ يَسْتَحِلُّونَ الْحِرَ وَالْحَرِيرَ وَالْخَمْرَ وَالْمَعَازِفَ)
«በኡመቴ ውስጥ ወደፊት ዝሙትን፣ ሐርን፣ አስካሪ መጠጥን እና የሙዚቃ መሳሪያን የሚፈቅዱ ሰዎች ይኖራሉ።»
[ቡካሪ ዘግበውታል]
ሷሊሕ አልመጛሚሲ የአላህ መልእክተኛ የዛሬ 1400 አመታት በፊት ካስጠነቀቋቸው ሰዎች ውስጥ መሆኑ ምንም የማያወላዳ ነው። ነገር ግን ስሜቱ አሸንፎት እሱን የሚከተል ከመልእክተኛው ማስጠንቀቂያ እንዳፈነገጠ ራሱ ለራሱ ይንገረው።
በርግጥ መጛሚሲ ሙዚቃን ለመፍቀድ በታሪክ የመጀመሪያው ሰው አይደለም። ከዚህ ቀደም እነ ጘዛሊ፣ ዩሱፍ አልቀረዷዊ፣ እና የቀድሞው የመካ ሐረም አሰጋጅ የነበረው ዐዲል አልከልባኒ በይዘት ከመጛሚሲ ጋር የሚገናኝ ፈታዋ ሰጥተዋል። በርካታ የእውቀት ባልተቤቶችም ምላሽ ሰጥተውበታል። የመጛሚሲ የሚለየው እሱ የሙዚቃ መሳሪውያውን ፈቅዶ መዝፈኑን ግን ክልክል ማድረጉ ነው። ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ የሙዚቃ መሳሪያ ክልክል ለመሆኑ ኢጅማእ (የዑለማዎች ሙሉ ስምምነት) እንዳለበት ይናገራሉ። [መጅሙዑል ፈትዋ]
ይህ ሙዚቃን ሓላል የማድረግ ጉዳይ ሱዑዲ እና ግብፅ ብሎም ኳታር ላይ የሚያበቃና ሃበሻ ከዚህ ረመጥ የዳነ መስሏችሁ ከሆነ በርግጥም ተሳስታችኋል። ከዚህ ቀደም በዩሱፍ አልቀረዷዊ አስተሳሰብ የተበረዙ የሃገራችን ወጣት ፀሃፊዎችም ሳይጨምሩ ሳይቀንሱ ይህንኑ ፈታዋ ሲያስተላልፉ እንደነበር ይታወሳል። ከነርሱም ውስጥ አቡ በክር አለሙ የተባለው ግለሰብ እና ሐሰን ታጁ የተባለው ፀሃፊ ተጠቃሾች ናቸው። ሐሰን ታጁ በራዲዮ ቀርቦ ሙዚቃን ሓላል ነው ማለቱም ይታወቃል።
በአላህ ይሁንብኝ ይህን ስፅፍ ከመሬት ተነስቶ የሰዎችን ስም እያነሱ ማስጠንቀቅ አምሮኝ አይደለም። ሆኖም ቢያንስ በማውቃት ኢምንት የሆነች ነገር ከአላህ ዘንድ የሆነ አማና እንዳለብኝ ግን አውቃለሁ። እንደምትመለከቱት ዛሬ ላይ ከላይ የጠቀስኳቸውን ሰዎች መፃህፍት በየመክተባዎች የሚያሰራጩ፣ እየተረጎሙ ለገበያ የሚያቀርቡ፣ ዌብሳይቶችና ማሕበራዊ ድረገፆች ላይ የሰዎቹን ፈትዋዎች እየበተኑ የሚገኙ ሰዎች በመኖራቸው ይህንን በግሌ እያየሁ ዝም ማለቴ ከአላህ የሆነ ቅጣት እንዳይደርስብኝ ለነፍሴ ስለምሰጋ ብቻ ነው።
ሰውባን ረዲየላሁ ዐንሁ እንዳወራው ረሱል ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ አሉ፦
( إِنَّمَا أَخَافُ عَلَى أُمَّتِي الْأَئِمَّةَ الْمُضِلِّينَ )
«እኔ ለኡመቴ የምፈራው አጥማሚ የሆኑ ኢማሞችን ነው አሉኝ።» [አልባኒ በሶሒሕ ኢብን አቢ ዳውድ ላይ ሶሒሕ ብለውታል]
ሙዚቃን ሓላል የሚያደርጉ ሰዎችን ማስጠንቀቅ በእኛ ላይ ዋጂብ ይሆንብናል። ምክንያቱም አላህ እኛ የነቢዩ ሰላልሁ ዐለይሂ ወሰለም ኡመቶችን ልቅና የገለፀን በጥሩ ስለምናዝ እና ከመጥፎም ስለምንከለክል ነው።
አላህ እንዲህ ይላል፦
{كُنْتُمْ خَيْرَ أُمَّةٍ أُخْرِجَتْ لِلنَّاسِ تَأْمُرُونَ بِالْمَعْرُوفِ وَتَنْهَوْنَ عَنِ الْمُنْكَرِ وَتُؤْمِنُونَ بِاللَّهِ}
((ለሰዎች ከተገለጸች ሕዝብ ሁሉ በላጭ ሆናችሁ፤ በጽድቅ ነገር ታዛላችሁ ከመጥፎም ነገር ትከለክላላችሁ በአላህም (ተውሒድ) ታምናላችሁ))
[ሱረቱልዒምራን 110]
ይህን ያላደረግን እንደሆነ ከአላህ የመጣ በላእ በእኛ ላይ ይወርድብናልና። አላህ ስለ በኒ ኢስራኢሎች ሲናገር እንዲህ ይላል፦
{لُعِنَ الَّذِينَ كَفَرُوا مِنْ بَنِي إِسْرَائِيلَ عَلَى لِسَانِ دَاوُدَ وَعِيسَى ابْنِ مَرْيَمَ ذَلِكَ بِمَا عَصَوْا وَكَانُوا يَعْتَدُونَ}[፫] ثم فسر هذا العصيان فقال سبحانه፥ {كَانُوا لا يَتَنَاهَوْنَ عَنْ مُنْكَرٍ فَعَلُوهُ لَبِئْسَ مَا كَانُوا يَفْعَلُونَ}
((ከእስራኤል ልጆች እነዚያ የካዱት በዳውድና በመርየም ልጅ በዒሳ ምላስ ተረገሙ፤ ይህ ትእዛዝን በመጣሳቸውና ወሰንን የሚያልፉ በመሆናቸው ነው።))
ቀጥሎም ይህን በኒ ኢስራኢሎች በነቢያቶች የተረገሙበትን ምክንያት አላህ ሲያብራራልን እንዲህ ይላል፦
{ذَلِكَ بِمَا عَصَوْا وَكَانُوا يَعْتَدُونَ * كَانُوا لا يَتَنَاهَوْنَ عَنْ مُنْكَرٍ فَعَلُوهُ}
((ከሠሩት መጥፎ ነገር አይከላከሉም (*) ነበር፤ ይሠሩት የነበሩት ነገር በእርግጥ ከፋ)) [ሱረቱልማዒዳህ 78-79]
ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በጥሩ ማዘዝና በመጥፎ መከልከል በእኛ ላይ ግዴታ መሆኑን ይህን ያላደረግን እንደሆን የሚከተለንን ሲነግሩን፦
(والذي نفسي بيده لتأمرن بالمعروف ولتنهون عن المنكر أو ليوشكن الله أن يبعث عليكم عقابا من عنده ثم لتدعنه فلا يستجيب لكم)
«ነፍሴ በእጁ በሆነችው ጌታ እምላለሁ በጥሩ ታዛላችሁ፤ ከመጥፎም ትከለክላላችሁ። ያለበለዚያ አላህ ከርሱ የሆነ ቅጣትን በናንተ ላይ ይልክባችኋል። ያኔ ዱዐ ብታደርጉለትም አይቀበላችሁም። »
[ቲርሚዚይ ዘግበውታል አልባኒ በሶሒሕ አልጃሚዕ ላይ ሶሒሕ ብለውታል]
አንዳንዶች እንደሚያስቡት ከጥመት ተጣሪዎች ማስጠንቀቅ በሙስሊሞች መካከል ልዩነት የሚፈጥር እኩይ ተግባር አይደለም እንዲያውም በኡማው መካከል አንድነት እና ወንድማችነት የሚያመጣ ቅዱስ ተግባር ነው።
አላህ እንዲህ ይላል፦
{وَالْمُؤْمِنُونَ وَالْمُؤْمِنَاتُ بَعْضُهُمْ أَوْلِيَاءُ بَعْضٍ يَأْمُرُونَ بِالْمَعْرُوفِ وَيَنْهَوْنَ عَنِ الْمُنْكَرِ
((ምእምናንና ምእምናትም ከፊሎቻቸዉ ለከፊሉ ረዳቶች ናቸው በደግ ነገር ያዛሉ፤ ከክፉም ይከለክላሉ)) [ሱረቱልተውባህ]
በመጨረሻም ከዚሁ ርእስ ጋር ተያይዞ ከላይ የተጠቀሱት ሙዚቃን ሓላል ያደረጉ ዱዐቶች በመፅሃፍም ይሁን በራዲዮ፣ በጋዜጣ፣ በማሕበራዊ ድረ ገፆች የምታስተዋውቁ ሰዎች አላህን ትፈሩ ዘንድ መልእክቴን አስተላልፋለሁ። እነዚህ የጥመት ተጣሪዎች እናንተ ያስተዋወቃችሁት ግለሰብ ወንጀል ላይ ቢወድቅ ትርፉ ለናንተም መሆኑን ማወቅ በናንተ ላይ የተገባ ነው።
የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም እንዲህ ይላሉ፦
(( من دعا إلى هدى كان له من الأجر مثل أجور من تبعه لا ينقص ذلك من أجورهم شيئاً، ومن دعا إلى ضلالة كان عليه من الإثم مثل آثام من تبعه لا ينقص ذلك من آثامهم شيئاً))
«ወደ መልካም ነገር የተጣራ (መልካሙን ነገር ፈፃሚው) ተካታዮቹ የሚያገኙትን ምንዳ ሳይቀነስ ያገኛል። ወደ ጥመትም የተጣራ በርሱ ላይ የተከተሉትን ተከታዮች ወንጀል አንዳችም ሳይቀነስ ያገኛል።»
[ሙስሊም ዘግበውታል]
አላህ ይጠብቀን
የአላህ ሰላምና ውዳሴ በነቢያችን ላይ በቤተሰቦቻቸው እና በባልደረቦቻቸው ላይ ይሁን

https://www.youtube.com/