Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ጠያቂ:- «(በረመዷን) ከባለቤቱ ጋር ግንኙነት እየፈፀመ ሳለ አዛን ያለበት ሰው ፍርዱ ምንድን ነው?»

ጠያቂ:-
«(በረመዷን) ከባለቤቱ ጋር ግንኙነት እየፈፀመ ሳለ አዛን ያለበት ሰው ፍርዱ ምንድን ነው?»

ሸይኹል ዐላማህ ሙሐመድ ኢብኑ ሃዲ አልመድኸሊይ (ሐፊዘሁላህ)፦

«ማለትም እርሱ ከሚስቱ ጋር ግንኙነት እያደረገ ሳለ የሶላት አዛን ጥሪ ከተደረገ በርሱ ላይ ያለበት (ግንኙነቱን) ማቆም ነው። ሌላ ነገር የለበትም።»

[ፈታዋ ሊሸይኹል ዐላማህ ሙሐመድ ኡብኑ ሓዲ]
-----------------------------------------

ጥ ያቄ ፦
« አዛን እየሰማ ግንኙነት ለቀጠለ ሰውስ? »

የዑለማዎች ጥናትና ፈትዋ ቋሚ ኮሚቴ፤

« ጎህ ከመቅደዱ በፊት ከሚስቱ ጋር ግንኙነት ያደረገና እስከ ሁለተኛው ጎህ መቅደድ ድረስ ግንኙነቱን ለቀጠለ ሰው ፆሙን ሊፆም በርሱ ላይ ግዴታ ነው። በረመዷን የቀን ክፍለ ጊዜ ላይ ግንኙነት ያደረገ ሰው የሚጠበቅበትን የፆም ማካካሻ ሊፈፅም ይገባል። ነገሩ ግልፅ እንደሚያሳየው ይህ ግለሰብ ምንም እንኳን ሙአዚኑ ሁለተኛውን (የሱብሒ ሶላትን) አዛን ሲጣራ ቢሰማም ግንኙነቱን ማቋረጥ ላይ ዝንጉ ሆኗል። እርሱ ግን አዛኑን በሰማ ጊዜ ግንኙነቱን ማቋረጥ ነበረበት። ሆኖም እርሱ ግን ለማቋረጥ ፋንታ ግንኙነቱን ቀጥሏልና ማካካሻውን ሊያወጣ በርሱ ላይ የተገባ ነው። ማካካሻውም ሙስሊም የሆነን ባሪያ ነፃ ማውጣት ሲሆን እሱን ካልቻለ ተከታታይ ሁለት ወር መፆም ይገባዋል። በህመምና በእድሜ መግፋት አማካኝነት ይህንንም ማድረግ ካልቻለ ለስልሳ ምስኪኖች ለእያንዳንዳቸው በአንፃሩ የሶስት ኪሎ ያህል ስንዴ፣ ሩዝ ወይንም በአገሪቷ ላይ ቋሚ የሆነውን የምግብ አይነት መመፅወት አለበት።

አላህ ስኬትን ያጎናፅፈን
የአላህ ሰላምና ውዳሴ በመልእክተኛው፣ በቤተሰቦቻቸው እና በባልደረቦቻቸው ላይ ይሁን።»

አባላት፡
ሸይኽ በክር አቡ ዘይድ (ረሒመሁላህ)
ሸይኽ ፈውዛን (ሐፊዘሁላህ)
ሸይኽ ዐብዱልዐዚዝ አሉ ሸይኽ (ሐፊዘሁላህ)
ሰብሳቢ ፤ ሸይኽ ዐብዱልዐዚዝ ኢብኑ ባዝ (ረሒመሁላህ)