አብድረህማን እና ጓደኞቹ፣ አመተላህ እና ጓደኞቿ፡፡
ውድ የአላህ ባርያዎች ሆይ! አላህ ረመዳን ወር በሰላም ያድርሰን፡፡ ረመዳን ውድ ወር ነው፡፡ አትራፊዎች ለመሆን መሰነቅ ግድ ይለናል፡፡ በረመዳን ውስጥ በጣም ብዙ የሚሰሩ ወደ አላህ የሚያቃርቡ ተግባራቶች አሉ፡፡ ከነዚህም ውስጥ
1) ቁርዓን መቅራት፣ ሲቀራ በጥሞና ማዳመጥ፣
2) ሰደቃ ማብዛት፣
3) ተራዊህ ሰላት እና የመሳሰሉት
ለዛሬ መፃፍ የፈለግኩት ስለ ሰደቃ ነው፡፡ ሰደቃ መስጠት ወይንም ምፅዋት ከአማኞች ባህሪያት አንዱ ነው፡፡ የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) በረመዳን ይበልጥ ቸር ይሆኑ ነበር፡፡ እኛም የሳቸውን አርዓያ በመከተል ሰደቃን ልናበዛ ይገባል፡፡
ብዙ ቦታ ላይ የሆነ መልካምን ነገር መስራት ሲፈለግ ‹‹ለአህለል ኸይሮች ይነገር፣ አህለል ኸይሮች ቢፈለጉስ›› የሚባል አባባል አለ፡፡ ግን በብዛት ውድ የአላህ ባርያዎች ሆይ! ሙስሊሞች በቀላሉ ሊሰሩት የሚችሉት በጣም ብዙ መልካም ስራዎች አሉ፡፡
‹‹50 ሎሚ ለአንድ ሰው ሸክሙ ነው፣ ለ50 ሰው ጌጡ ነው›› እንደሚባለው፡፡ በአንድነት መዋጮ በማውጣት ሁሉም በአላህ ፍቃድ በየአካባቢው ያለውን ሙስሊም የተቸገረ ቤተሰብ ሊደጉምና ሊሰድቅለት ይገባል፡፡
አንተ የአላህ ባርያ አብድረህማን (አብደላህ) ሆይ! አንተና ጓደኞችህ የተፈጠራችሁት ለቁም ነገር ነውና፣ የተቸገረውም ሙስሊም ወንድምና እህታችን ነውና፣ ገንዘባችሁን በማዋጣት ለእነ …. አዎ ሰፈራችሁ ውስጥ ለምታውቋቸው ቡዙ ምስኪኖች ተምር፣ ዱቄት፣ ዘይት እና ሌሎችንም በአካባቢያችሁ የተለመዱ ሰደቃዎችን በመስጠት መረዳዳት ይቻላል፡፡ እህቴ አመተላህም እንዲሁ ከጓደኞችሽ ጋር አብረሽ በመሆን በየአካባቢያችሁ ያሉትን ምስኪኖች ከአላህ በታች እርዱዋቸው፡፡
አላህ እንዲህ ይላል
وَتَعَاوَنُوا۟ عَلَى ٱلْبِرِّ وَٱلتَّقْوَىٰ
በበጎ ነገርና አላህን በመፍራትም ተረዳዱ፡፡

መልካም ረመዳን እመኛለሁ፡፡ አላህ ሸዕባንን ይባርክልን፣ ረመዳን በሰላም ያድርሰን፣ እሱ ለሚወደው ሁሉ ይግጠመን፡፡