“ቱርክ ሆይ! እናመሰግናለን!”
በቅርቡ ኢኽዋኖች ኢስታንቡል ላይ ያደረጉት ኮንፈረንስ ርእስ ነው፡፡ መቼም የውጮቹ ኢኽዋኖች ሲስሉ እኛ ጋር የሚያነጥሱ አሉና እዚህም ሲያራግቡት ነበር፡፡ በዚህ ኮንፈረንስ ላይ እንደ ቀርዷዊ፣ ኻሊድ ሚሽዐልና ሌሎችም ታዋቂ ኢኽዋኖች ተገኝተው በርካታ መግለጫዎችን ሲያወጡ ነበር፡፡ በመግለጫቸውም የቱርኩን ኤርዶጋን በተጋነነ መልኩ ሲያወድሱ ነበር፡፡
“ከኺላፋው ዋና ከተማ… ከኢስታንቡል!!” ይላል አንዱ፡፡ ቱርክ ውስጥ ኺላፋ አለ እንዴ?! ወላሂ የቱርክ ባለስልጣናትም እንዲህ አይሉም!!
“ድሮም የኢስላም ዋና ከተማ፣ ዛሬም የኢስላም ዋና ከተማ፣ ወደፊትም የኢስላም ዋና ከተማ” ይላል ሌላው፡፡ እውነት ቱርክ በኢስላማዊ ህግ ነው የምትመራው? በጭራሽ!! ታዲያ ከሌሎች የሙስሊም ሃገራት ምንድን ነው የሚለያት?!
“ትልቁ የሙስሊሞች ሱልጧን የሆነውን (ኤርዶጋንን) ማን ሊቃወመው ይችላል? የሙስሊሞች ሱልጧን፣ የኡማው ሱልጧን፣ ከሙስሊሙ ኡማ በኢስላም ስም፣ በሱንናህ ስም፣ በዐቂዳህ ስም፣ በሸሪዐህ ስም፣ … ባለው ሃይል ሁሉ የሚከላከል” ይላል ቱባው፡፡ ሌላም ሌላም…
ከቱርክ መንግስት በኩል የተሰማው ግን ለኢኽዋኖች አስደንጋጭ ነበር፡፡ የቱርክ መንግስት ጠቅላይ ሚኒስቴር አማካሪ የሆነው ዑመር አልፋሩቅ የዚህን ኮንፈረንስ አራጋቢዎች የሚያስድነግጥ ነገር ተናግሯል፡፡ ሃገራቸው ላይ ዴሞክራሲን አምክነው ቱርክም ላይ ሊያመክኑ የሚተጉ እንደሆኑ ገልፁዋል፡፡
ይሄውና ተጋበዙ፡፡