Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

በደጋሚዎችና በጠንቋዮች ዘንድ ደጅ መጥናት እንዴት ይታያል?

በደጋሚዎችና በጠንቋዮች ዘንድ ደጅ መጥናት እንዴት ይታያል?

በዚህ ዘመን ሙስሊሞች ከተፈተኑበት ነገር ወደ ደጋሚዎችና አጭበርባሪዎች ጋር በመመላለስ አንዳቸው በአንዳቸው ላይ ጉዳትን ለማድረስ መሞከራቸው ነው፡፡ ሙስሊሞችን ማስቸገር፣ ጉዳትን በሱ ላይ መፈፀም ትልቅ ወንጀል ነው፡፡ አላህ I እንዳለው

“እነዚያ ምእመናንንና ምእመናትን ባልሰሩት ነገር የሚያሰቃዩ እብለትንና ግልፅ ሀጢአትን በእርግጥ ተሸከሙ”
(አል አህዛብ 58)

እንዲሁም አንድ ሙስሊምን ፈተና ላይ መጣል ትልቅ ወንጀል ነው፡፡ አላህ እንዳለው

“እነዚያ ምእመናንንና ምእመናትን ያሰቃዩ ከዚያም ያልተፀፀቱ ለእርሱ የገሀነም ቅጣት አላቸው ለእነሱም የመቃጠሉ ስቃይ አላቸው”
(አል ቡሩጅ 1ዐ)

ወደ ጠንቋዩችና አዋቂ ተብዬ ጋር መመላለስና ደጅ መጥናትን ኢስላም ከልሏል፡፡ የአላህ መልዕክተኛ የዚህ መጨረሻው ውርደትና መጥፎ ነገር እንደሆነ አብራርተዋል፡፡

ከነብያችን (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ሚስቶች አንደኛዋ ነብያችን (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል ትላለች
«ወደ ጠንቋይ ዘንድ መጥቶ ስለአንድ ጉዳይ የጠየቀ ግለሰብን የአርባ ቀን ሰላቱ ተቀባይነት አይኖረውም”
ሙስሊም ዘግበውታል

አቡ ሁረይራ ነብያችን (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ ብሏል
“ወደ ጠንቋይ ወይም አዋቂ ተብዬ ዘንድ ሄዶ የሚናገረውን እውነት ብሎ የተቀበለ በሙሐመድ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ላይ በወረደው ቁርአን ክዷል፡፡”
አህመድ ዘግበውታል

የደጋሚዎችንና የጠንቋዮችን ደጅ መጥናት መጨረሻው ጥፋት መሆኑ ምንም ጥርጥር የለውም፡፡ የደጋሚዎችን ደጅ መጥናት በዱንያም በአኺራም ኪሰራ ስለሆነ ልንጠነቀቀውና ልንርቀው ይገባል፡፡

‪#‎ሺፋእ‬

ቁርዓናዊ ፈውስ ለጂን እና ሲህር !
ፔጁን ላይክ ለማድረግ፡-
https://www.facebook.com/nosihr
ሼር በማድረግ ሙስሊሙን ዑማ በብዛት እየጎዳ ያለውን የሲህር በሽታ
ለመከላከል የበኩሎን አስተዋፅዖ ያበርክቱ!