ሸፋዓ (ምልጃ)
ነብዩም ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ሆኑ ማንኛውም ደግ ሰው አላህ ዘንድ አማላጅ እንዲሆንልን የሚጠየቀው አላህን ብቻ ነው፡፡ ለምሳሌ ነብዩ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም የቂያማ እለት ሸፋዓ (አማላጅ) እንዲሆኑን ስንፈልግ “ጌታዬ ሆይ! የቂያማ እለት ነብዩን ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም አማላጅ አድርግልኝ” ብሎ መለመን የተፈቀደ ነው፡፡ ነገር ግን ነብዩንም ሆነ ሌላን ሠው እባክህን ነገ አማላጅ ሁነኝ ብሎ መለመን የማይፈቀድ ሽርክ ነው፡፡ ምክንያቱም ይህን ማድረግ የሚችለው አላህ ብቻ ስለሆነና ከአላህ ሌላ ማንም ሊፈፅመው የማይችለውን ነገር ፍጡርን መለመን ሽርክ ስለሆነ ነው፡፡
ሸፈዓ በሁለት ይከፈላል፡-
1. የተረጋገጠ ሸፈዓ እና
2. የተወገደ ሸፈዓ ናቸው፡፡
የተረጋገጠ ሸፈዓ፡- ከአላህ ብቻ የሚለመን ሲሆን ይህም ተገቢ የሚሆነው ተውሂድን ፈፃሚ ለሆነና በአላህ ላይ ለማያጋራ ብቻ ነው፡፡
ይህ ምልጃ ተፈፃሚ የሚሆነው አላህ ለአማላጁ ሲፈቅድና አማላጁና ተማላጁንም ሲወድ ብቻ ነው፡፡
አላህ እንዲህ ይላል፡-
مَن ذَا الَّذِي يَشْفَعُ عِندَهُ إِلَّا بِإِذْنِهِ
“እርሱ ዘንድ በፈቃዱ ቢኾን እንጂ የሚያማልድ ማነው?” (አል በቀራህ 255)
وَكَم مِّن مَّلَكٍ فِي السَّمَاوَاتِ لَا تُغْنِي شَفَاعَتُهُمْ شَيْئًا إِلَّا مِن بَعْدِ أَن يَأْذَنَ اللَّهُ لِمَن يَشَاءُ وَيَرْضَى
“በሰማያት ውስጥ ካለ መልአክም ብዙዎች ለሚሻውና ለሚወደው ሰው ከፈቀደ በኋላ ቢሆን እንጅ ምልጃቸው ምንም አትጠቅምም” (አን ነጅም 26)
وَلَا تَنفَعُ الشَّفَاعَةُ عِندَهُ إِلَّا لِمَنْ أَذِنَ لَهُ
“ምልጃም እርሱ ለፈቀደለት ሰው ብቻ ቢሆን እንጅ እርሱ ዘንድ ምንም አትጠቅምም” (ሰበእ 23)
وَلَا يَشْفَعُونَ إِلَّا لِمَنِ ارْتَضَى
“ለወደደውም ሰው እንጅ ለሌላ አያማልዱም” (አል አንቢያእ 28)
የተወገደው ሸፈዓ፡- አላህ ያስወገደው ያልፈቀደውና ያልወደደው ሲሆን እሱም ከአላህ ውጭ ከሆነ ፍጡር የሚለመን ነው፡፡
አላህ እንዲህ ይላል፡-
وَأَنذِرْ بِهِ الَّذِينَ يَخَافُونَ أَن يُحْشَرُوا إِلَى رَبِّهِمْ لَيْسَ لَهُم مِّن دُونِهِ وَلِيٌّ وَلَا شَفِيعٌ لَّعَلَّهُمْ يَتَّقُونَ
እነዚያንም ከእርሱ ሌላ ረዳትና አማላጅ የሌላቸው ሲኾኑ ወደ ጌታቸው መስሰብሰብን የሚፈሩትን ይጠነቀቁ ዘንድ በርሱ (በቁርኣን) አስፈራራ፡፡ (አል-አንዓም 51)
የቁርዓን እና ሀዲስን መረጃ በራሳቸው ፍላጎት ሳይለውጡ የሚከተሉ አማኞች (አህሉ ሱንና ወል ጀመዓ) የቂያማ ዕለት በግንባር ቀደምነት ነብዩ ከዚያ ሌሎች ነቢያት ደጋግ ባሮች እንደሚያማልዱና በነሱም ምልጃ ምክንያት ኃጢአተኛ ሙስሊሞች ጀሐነም እንዳይገቡ ወይም የገቡት እንዲወጡ እንደሚደረግ የሚያምኑ ሲሆን ሙስሊምን በወንጀል ምክንያት የሚያከፍሩ (ኸዋሪጆች) ግን ይህን አይቀበሉም፡፡
ነብዩ እንዲህ ይላሉ፡- “አላህ፦ መልአኮች አማለዱ ነብዮችም አማለዱ የቀረው የአዛኞች አዛኝ ነው ይልና መልካም ሰርተው የማያውቁ ሰዎችን ከእሳት ዘግኖ ያወጣል”
#እምነትህን_ጠብቅ
የፌስ ቡክ ገፃችንን ለማግኘት
https://m.facebook.com/ emnetihintebiq

https://m.facebook.com/