Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ኒፋቅ (ንፍቅና)

ኒፋቅ (ንፍቅና)

እምነትን ከላይ በማንፀባረቅ ክህደትን በውስጥ በመደበቅ ንፍቅና ይባላል፡፡
አላህ እንዲህ ብሏል ፡-
ذَٰلِكَ بِأَنَّهُمْ آمَنُوا ثُمَّ كَفَرُوا فَطُبِعَ عَلَى قُلُوبِهِمْ فَهُمْ لَا يَفْقَهُونَ
‹‹ይህ እነርሱ (በምላስ) ያመኑ ከዚያም (በልብ) የካዱ በመኾናቸው ነው፡፡ በልቦቻቸውም ላይ ታተመባቸው፤ ስለዚህ እነርሱ አያውቁም፡፡››
(ሙናፊቁን 3)

ኒፋቅ ሁለት አይነት ነው፡-

1. የልብ ንፍቅና፡-

ይህ ከእስልምና የሚያስወጣ ሲሆን ከነዚህም ከአይነቶቹም መካከል::

1,መልዕክተኛን ማስተባበል፣
2,መልዕክተኛው ካመጣው ውስጥ የተወሰነውን ማስተባበል፣
3,መልዕክተኛውን መጥላት፣
4,የመልዕክተኛው ሀይማኖት ሲዋረድ መደሰትና
5 የመልዕክተኛው ሃይማኖት የበላይ ሲሆን መጥላት ናቸው፡፡

2. የተግባር ንፍቅና፡-

ይህ ትንሹ ኩፍር በመሆኑ ከእስልምና ባያስወጣም ነገር ግን አደገኛ ወንጀልና ከባድ ኃጢአት ነው፡፡ ከነዚህም ውስጥ ነብዩ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) በሀዲስ እንዲህ በማለት የጠቀሱት ይካተታሉ

‹‹አራት ባህሪዎች ያሉበት ሙልጭ ያለ መናፍቅ ይሆናል ከአራቱ አንዱ ያለበት ሰው ግን እስኪተወው ድረስ ከመናፍቅ ባህሪዎች አንዱ አለበት ሲታመን በካድ፣ ሲናገር መዋሸት፣ ቃሉን የሚያፈርስና ሲከራከር ድንበር መጣስ፡፡››

[አል ቡኻሪይና ሙስሊም]

በሌላም ሀዲስ እንዲህ ብለዋል

‹‹የመናፍቅ ምልክት ሶስት ነው ሲናገር መዋሸት፣ ቀጠሮን ማፍረስና ሲታመን መካድ፡፡››

አላህ ከንፍቅና ይጠብቀን!

‪#‎እምነትህን_ጠብቅ‬
የፌስ ቡክ ገፃችንን ለማግኘት
https://m.facebook.com/emnetihintebiq