የረመዳን ወር እና የዩሱፍ ዐለይሂ ሰላም ተመሳስሎሽ
(በአንድ አመት ውስጥ ያሉ) አስራ ሁለት ወራት ልክ እንደ የዕቁብ ዐለይሂ ሰላም አስራ ሁለት ልጆች አምሳያ ናቸው ይባላል። በወራት መካከል ያለው ረመዳን ወር በወንድሞቹ መካከል ያለው ዩሱፍ አምሳያ ነው። ዩሱፍ ዐለይሂ ሰላም አባቱ ዘንድ ከሌሎች ወንድሞቹ የበለጠ ተወዳጅ ነበር። ልክ እንዲሁ የረመዳን ወር የሩቅን አዋቂ የሆነው (አላህ) ዘንድ ተወዳጅ ወር ነው።
ለሙሐመድ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ኡመት በዚህ ላይ መልካም የሆነ (አስተማሪ) ነጥብ ያለው። ።
ዩሱፍ ዐለይሂ ሰላም (ወንድሞቹ ያደረሱበት ትልቅ በደል ቢኖርም) ለነርሱ ርህራሄ እና ይቅር ባይነት (አፍው) ነበረው። እንዲህም ባለ ጊዜ
(لا تثريب عليكم اليوم)
{{ «ዛሬ በናንተ ላይ ወቀሳ የለባችሁም።» }} [ዩሱፍ፤92]
ልክ እንዲሁ የረመዳን ወርም ርህራሄ፣ በረከት፣ ፀጋ እና መልካም ነገራቶች ፣ ከእሳት ነፃ መውጫ፣ ከፍ ካለው ንጉስ (አላህ) ማህርታን ማስግኛ (ሲሆን)፤ ሌሎች ወራት የሌላቸውን (ረመዳን) በውስጡ አሉት። በሌሎች ወራት ውስጥ የሰበሰብነውን እኩይ እና ወንጀሎችን (የምናራግፍበት ነው።)
ሌላኛው አስተማሪ ነጥብ ደግሞ የሚጠቁመን የዩሱፍ ወንድሞች ያለባቸው ኃጢዓት እና ስ ህተት እንዳለ ሆኖ ከዩሱፍ እርዳታን ሽተው ወደርሱ በመጡ ጊዜ በመልካምነት ተቀበላቸው። ያሉበትን ሁነት አስተካከለላቸው። ተርበው በነበሩበት ሰአት መገባቸው። ወደመጡበት እንዲመለሱም ፈቀደላቸው። ለሰራተኖቹም ፦
(እህል የገዙበትንም ገንዘብ እኛ እንዳልተቀበልናቸው እንዳያውቁ ወደ መጫኛዎቻቸው እህሉን ጫኑላቸው።)አላቸው።
በመሆኑም አንዱ ብቻውን የአስራ አንዱን ክፍተት ሞላ። በተመሳሳይም ረመዳን ወር ብቻውን የምንሰራው (መልካም) ስራ የአስራ እንዱን ወራት የስራ ክፍተት ይሞላል። ሁሉን አዋቂ የሆነው ጌታችንን መታዘዝ ላይ ምን ያህል ክፍተትና ጉድለት እንዳለብን አስቡት?
እኛ በሌሎች ወራት ላይ ያሳለፍነውን ዝንጉነት በዚህ ወር ለማከም እንመኛለን። የተበላሹብንን (ዲናዊ) ጉዳዮችም እንዲሁ። በስኬት እና በደስታ ልናሽገውም ጭምር። መሃሪ በሆነው ንጉስ ገመድም ለመተሳሰር። ኢንሻ አላህ በርሱ ፀጋ፣ መልካምነት፣ ይቅር ባይነትና መሃሪነት። እርሱ እኮ ሁሉን ሰሚ ነው። እርሱ እኮ አጋዣችን እና ጠባቂያችንነው።
[ቡስታኑ ዋዒዚን ወርሪያድ ሳሚኢን 1/217]