Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ታላቁ ዓሊም ሸይኽ ሷሊሕ ኢብኑ ፈውዛን አልፈውዛን አላህ ይጠብቃቸውና የማህበራዊ መገናኛ መንገዶች ለናንተ ልትጠቀሙባቸው የሚገቡ ጥሩ እድሎች ናቸው .....

ታላቁ ዓሊም ሸይኽ ሷሊሕ ኢብኑ ፈውዛን አልፈውዛን አላህ ይጠብቃቸውና እንዲህ ይላሉ:–

"የማህበራዊ መገናኛ መንገዶች ለናንተ ልትጠቀሙባቸው የሚገቡ ጥሩ እድሎች ናቸው። ለተንኮለኞችና ለጥመት ሰባኪዎች እንዳትተዋቸው።" (አሀምይየቱል ዐቂደቲ አስሶሒሐህ)

እናስተውል!
መስጂዶች በጥመት ቡድኖች እጅ ሆኑ ብለህ ተስፋ እንዳትቆርጥ። መስጂድ ተነጠቅን ብለህ እጅህን አጣጥፈህ አትቀመጥ። ጉልበተኞች አላንቀሳቀሱንም ብለህ አትርበትበት።
አስታውስ ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በድብቅ ያስተማሩበትም ዘመን እንደነበር ከታሪክ ተማር። አማራጮች ሲጠቡ ወደ ሌላ አማራጭ ተመልከት። ዛሬ ላይ በእጃችን ከሚገኙ የማስተማሪያ መንገዶች ውስጥ እንደ ፌስቡክ፣ ዋትሳፕ፣ ቴሌግራም እና ሌሎችም የማህበራዊ መገናኛ መንገዶች ቀዳሚውን ቦታ ይይዛሉ።
በፍፁም ለአጥፊ ኃይላት እጅ እንዳትሰጥ። የሚጠበቅብህን ሃላፊነት ተወጣ። ሶሐቦች ሕይወታቸውን ሳይቀር እንደገበሩ አትርሳ። ስለሆነም እውነቱን ለማድረስ፣ ሀሰትን ለማርከስ ከቻልክ በእውቀትህ፣ ካለህ በገንዘብህ፣ በምትችለው ሁሉ ተንቀሳቀስ። ከፊትህ ያለው ወይ እጅግ የሚያስቋምጥ ጀነት ነው። ወይ ደግሞ አስፈሪ የሆነ እሳት። ካለህ አትሳሳ። የፈለግከውን ብትለፋ፣ የፈለግከውን ብትለግስ የቂን ብለህ ጀነትን ካለምክ ውድ አይደለም። ነገ የቂያማ ቀን እራሳቸውን ከጀሀነም ለማትረፍ ዱንያን ሁለት እጥፍ ቢሰጣቸው ቤዛ አድርገው ለማቅረብ የማያመነቱ ሰዎች ይኖራሉ። ያ ጊዜ ከመምጣቱ በፊት ዛሬን ተግተህ ስራ። ለዲንህ ታገል፣ ለሱንናህ ታገል፣ ለተውሒድ ታገል። የአጋር መቅለል፣ የጠላት መብዛት አያሳስብህ። መስጂዱን ብታጣ ባሉህ ሚዲያዎች ተጠቀም። ፌስቡክህ፣ ዋትሳብህ፣… ከሃዲው፣ አህባሹ፣ ኢኽዋኑ፣… የማይነጥቅህ መስጂድህ የዳዕዋ መድረክህ ናቸው። እነሱ ለጥፋት ሲፈነጩ ተመልካች አትሁን። የማህበራዊ ሚዲያ ዳዕዋ ለስንቶች ሂዳያ ሰበብ እንደሆነ በተግባር እያየነው ነው። የስንቱ ሴረኞች ተንኮል በመጋለጡ ስንቱ ተርፏል። ዛሬን አጥብቀህ ከሰራህ የሚሰድብህ፣ የሚረግምህ አካል ነገ ይቅርታ ይጠይቅሃል። ህዝብህ ላይ አትፍረድ። ለዘመናት የጥፋት ኃይሎች እግር ከወርች ጠፍረው ይዘውታል። በትንሽ ጥረት የተንኮል ድራቸው ሲበጣጠስ እያየን ነው። ለዚህ ደግሞ የማህበራዊ ሚዲያዎች ደዕዋ ሚና ቀላል አይደለም። ስለዚህ እነዚህን መገናኛዎች አጥፊዎች ለጥፋት ሲያውሏቸው አንተ ኸይር ለማሰራጨት ተንኮልን ለማክሸፍ በሚገባ ተጠቀማቸው።
ሕዝባችንን አንድየው ከጥፋት ይጠብቀው፣ በተውሒድና በሱንናህ ላይ ይሰብስበን፣ መንገድ የሳቱ ወገኖቻችንንም ከዐርሹ በላይ ያለው ጌታ ወደ መንገዱ ይመልሳቸው። ኣሚን።