Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

አንባር ክርና የመሳሰሉ ነገሮችን ማጥለቅ!

አንባር ክርና የመሳሰሉ ነገሮችን ማጥለቅ!
ዓረቦች ከእስልምና በፊት በነበረው የድንቁርና ዘመን ይህንንና የመሳሰሉትን ክፋትን ለመመከት፣ መልካምን ለማስገኘት ወይም ከቡዳ ለመጠበቅ ያደርጉት ነበር፡፡
አላህ እንዲህ ብሏል፡-
وَلَئِن سَأَلْتَهُم مَّنْ خَلَقَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ لَيَقُولُنَّ اللَّهُ قُلْ أَفَرَأَيْتُم مَّا تَدْعُونَ مِن دُونِ اللَّهِ إِنْ أَرَادَنِيَ اللَّهُ بِضُرٍّ هَلْ هُنَّ كَاشِفَاتُ ضُرِّهِ أَوْ أَرَادَنِي بِرَحْمَةٍ هَلْ هُنَّ مُمْسِكَاتُ رَحْمَتِهِ قُلْ حَسْبِيَ اللَّهُ عَلَيْهِ يَتَوَكَّلُ الْمُتَوَكِّلُونَ
«ከአላህ ሌላ የምትግገዟቸውን (ጣዖታት) አያችሁን? (ንገሩኝ) አላህ በጉዳት ቢፈልገኝ እነርሱ ጉዳቱን ገላጮች ናቸውን? ወይስ በችሮታው ቢፈቅደኝ እነርሱ ችሮታውን አጋጆች ናቸውን?» በላቸው፡፡ «አላህ በቂዬ ነው፡፡ በእርሱ ላይ ተመኪዎች ይመካሉ» በል፡፡ (አል ዙምር 38)
በሌላም አንቀጽ እንዲህ ይላል፦
قُلِ ادْعُوا الَّذِينَ زَعَمْتُم مِّن دُونِهِ فَلَا يَمْلِكُونَ كَشْفَ الضُّرِّ عَنكُمْ وَلَا تَحْوِيلًا
«እነዚያን ከእርሱ ሌላ (አማልክት) የምትሏቸውን ጥሩ፡፡ ከእናንተም ላይ ጉዳትን ማስወገድን (ወደ ሌላ) ማዞርንም አይችሉም» በላቸው፡፡ (አል ኢስራህ 56)
ከዒምራን ኢብኑ ሁሰይን እንደተዘገበው ‹‹ነብዩ አንድ ሰውዬ እጁ ላይ ከመዳብ የሆነ አንባር አጥልቆ ሲያዩት “ይህ ምንድነው?” ብለው ጠየቁት “ለድካም በሽታ ነው” አላቸው:: እሳቸውም እንዲህ በማለት ወቀሱት “አውልቃት ድካምን እንጂ አትጨምርልህም እጅህ ላይ እያለች ከሞትክ አትድንም፡፡››
ከሁዘይፋ ኢብኑል የማን እንደተዘገበው ‹‹አንድን ሰው በመታመሙ እጁ ላይ ክር አስሮ አየውና ከበጠሱበት በኋላ ይህን አንቀጽ አነበቡ፦
وَمَا يُؤْمِنُ أَكْثَرُهُم بِاللَّهِ إِلَّا وَهُم مُّشْرِكُونَ
‹‹አብዛኞቻቸውም፤ እነሱ አጋሪዎች ኾነው እንጂ በአላህ አያምኑም፡፡›› (ዩሱፍ 1ዐ6)
ለ. አንባር፣ ክርና የመሳሰሉትን ማጥለቅ ሸሪዓዊ ድንጋጌው ሀራም (ክልክል) ሲሆን የተጠለቀው ራሱ ያለ አላህ ፈቃድ ተፅእኖ ያሳድራል የሚል እምነት ካለው ከአላህ ውጭ አስተናባሪ ጌታ አለ ማለት በመሆኑ በአላህ ጌትነት ላይ ትልቁን ሽርክ አጋርቷል ማለት ነው::
ነገሮች ሁሉ በአላህ እጅ እንደሆኑና ያጠለቀው ነገር ግን ለፈውስ ምክንያት ብቻ እንደሆነ ቢያምን ደግሞ ትንሹን ሽርክ ፈፅሟል፡፡ ምክንያቱም ሰበብ ያልሆነን ነገር እንደሰበብ ቆጥሮ በልቡና በስራውም ከአላህ ሌላ ወደሆነ አካል ዞሯል፡፡ ይህ ደግሞ ወደ ትልቁ ሽርክ ለመሸጋገር በር የሚከፍት ነው፡፡
ቁርዓናዊ ፈውስ ለጂን እና ሲህር !
ፔጁን ላይክ ለማድረግ፡-
https://www.facebook.com/nosihr
ሼር በማድረግ ሙስሊሙን ዑማ በብዛት እየጎዳ ያለውን የሲህር በሽታ ለመከላከል የበኩሎን አስተዋፅዖ ያበርክቱ!