ወንጀል የሚያስከትለው መዘዝ!
“አልጀዋብ አልካፊ ሊመን ሰአለ ዐኒ ደዋእ አሽ ሻፊ” በሚለው ኪታባቸው አል ኢማም ኢብኑልቀይም ሀጢኣት ሊያስከትል የሚችለውን መጥፎ አሻራ ሲዘረዝሩ እንዲህ ይላሉ፤
حرمان العلم، وحرمان الرزق، ووحشة في القلب بينه وبين الناس، ووحشة بينه
وبين الله، وتعسير الأمور، والمعصية تضعف القلب وتمرضه، والعاصي يحرم
الطاعة بمعصيته، المعصية تمحق بركة العمر، وتكثر الشياطين.. المعاصي تزرع
أمثالها ويولّد بعضها بعضًا.. العاصي يألف المعصية ولا يستقبحها، هوان
العاصي على ربه، المعصية تفسد العقل، وسبب لحدوث الفساد في الأرض.. المعصية
تطفئ الغيرة، وتزيل النعم، وتحل النقم،
ويلقي الله تعالى بسببها الرعب في قلب العاصي.. المعصية تطمس البصيرة،
وتجعل صاحبها أسيرًا للشيطان.. المعصية تصغّر النفوس وتحقّرها، وتجعل
صاحبها سجينًا لشهواته، مقيدًا لهواه.. المعصية تُسقط كرامة الإنسان،
العاصي تجترئ عليه شياطين الإنس والجن.. وربما منعته المعصية من النطق
بالشهادة عند الاحتضار
“(ሀጢኣት) ዕውቀትን ይነፍጋል፤ ሲሣይን ይከለክላል፣ በቀልብ ውስጥ በአንድ ሰውና በሌሎች መካከል ባዶነትን
ይፈጥራል፣ ከአላህ ያራርቃል፣ ነገሮችን ያከብዳል። ሀጢኣት ቀልብን በማዳከም ለበሽታ ያጋልጠዋል፤ ሀጢኣተኛ ሰው
በሠራው ሀጢአት ምክኒያት የአላህን ትእዛዝ መፈፀም ያቅተዋል፤ ሀጢኣት የእድሜን በረከት ትነሣለች፣ ሸይጧንን
ታበዛለች ... ሀጢኣት አምሣያዋን ትተካለች፤ ከፊሏም ከፊሉን ይወልዳል። ሀጢኣትን የሚያዘወትር ሰው ሀጢኣቱ ልማድ
ይሆንበትና ከመላመዱ የተነሣ ምንም ላይመስለው ይችላል። ሀጢኣተኛ ሰው አላህ ዘንድ የተዋረደና የተናቀ ነው። ሀጢኣት
ንፁህ አዕምሮን ታበላሻለች፣ በምድር ላይ ጥፋት እንዲስፋፋም ምክኒያት ነች .. ሀጢኣት ተቆርቋሪነትንና በጎ
ቅናትን ታጠፋለች፣ መልካም ፀጋዎችን ትወስዳለች፣ የአላህን ቁጣ ታስከትላለች፣ በሷም ምክኒያት በሀጢኣተኛ ቀልብ ላይ
አላህ ፍርሃትን ይለቃል ... ሀጢኣት እውነትን ከማየት ትጋርዳለች፣ ባለቤቱንም የሸይጧን ምርኮ ታደርጋለች፣ …
ሀጢኣት አንድን ሰው ታስንቃለች ታዋርደዋለችም፤ ባለቤቱንም የደመ ነፍሱ ተገዠ፣ የስሜቱ ምርኮኛ አድርጋ
ታስቀራለች፣.. ሀጢኣት የሰውን ክብር ታወርዳለች፣ ሀጢኣተኛ ሰው የሰውም ሆነ የጅን ሸይጧኖች ይዳፈሩታል ...
በሞት አፋፍ ላይ የደረሠ ሰው በሀጢኣቱ ምክኒያት በሸሃዳ መመስከር የማይታደልበት ሁኔታም ሊኖር ይችላል።”
#ሺፋዕ
ቁርዓናዊ ፈውስ ለጂን እና ሲህር !
ፔጁን ላይክ ለማድረግ፡-
https://www.facebook.com/nosihr