Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ውዱ ወንድሜ አንቺስ ውዷ እህቴ እንደው ፍጥረተ አለሙ ሁሉ አላህን እንደሚያውቀው ፤እንደሚያጠራው አረ እንደውም ለሱም ሱጁድ እንደሚያደርጉለት ታውቁ ይሆን?

Kedir Kedu Ahmed
ወቅታዊ የሚል ግሩፕ ውስጥ ስገባ ያጋጣሚ አንድ ፅሁፍ እጅጉን ማረከኝ። ፅሁፉን ያዘጋጀው አቡ አብደላህ ይባላል ሃፊዘሁላህ። በዚህ ሰአት ብዙም ፌስ ቡክ ላይ ባናየውም። እናም እላችኋለው ፅሁፉን ኮፒ አድርጌ ብለቀው ብዙ ጥቅሞች ይኖሩታል ብዬ ስላመንኩኝ እንካቹ ብያለው። አደራችሁን ፁሁፉን ሳታነቡ እንዳታልፉት (ምክር እንጂ ትእዛዝ አይደለም።)
ሱበሃነላህ!! የአላህ ተዐዓምር ግሩም ነው፡፡
ﺍﻟﺤﻤﺪ ﻟﻠﻪ ﻭﺍﻟﺼﻼﺓ ﻭﺍﻟﺴﻼﻡ ﻋﻠﻰ ﺭﺳﻮﻝ ﺍﻟﻠﻪ، ﻭﻋﻠﻰ ﺁﻟﻪ ﻭﺃﺻﺤﺎﺑﻪ ﻭﻣﻦ ﺍﻫﺘﺪﻯ ﺑﻬﺪﺍﻩ، ﺃﻣﺎ ﺑﻌﺪ
ውዱ ወንድሜ አንቺስ ውዷ እህቴ እንደው ፍጥረተ አለሙ ሁሉ አላህን እንደሚያውቀው ፤እንደሚያጠራው አረ እንደውም ለሱም ሱጁድ እንደሚያደርጉለት ታውቁ ይሆን? አብረውኝ ትንሽ ቆይታ ያድርጉ በአላህ ፍቃድ የቻልኩትን ያክል አካፍላችኋለው፡፡
አላህ እንዲህ ያላል፡-
ﺗُﺴَﺒِّﺢُ ﻟَﻪُ ﺍﻟﺴَّﻤَﻮَﺍﺕُ ﺍﻟﺴَّﺒْﻊُ ﻭَﺍﻟْﺄَﺭْﺽُ ﻭَﻣَﻦْ ﻓِﻴﻬِﻦَّ ﻭَﺇِﻥْ ﻣِﻦْ ﺷَﻲْﺀٍ ﺇِﻟَّﺎ ﻳُﺴَﺒِّﺢُ ﺑِﺤَﻤْﺪِﻩِ ﻭَﻟَﻜِﻦْ ﻟَﺎ ﺗَﻔْﻘَﻬُﻮﻥَ ﺗَﺴْﺒِﻴﺤَﻬُﻢْ ﺇِﻧَّﻪُ ﻛَﺎﻥَ ﺣَﻠِﻴﻤًﺎ ﻏَﻔُﻮﺭًﺍ
‹‹ሰባቱ ሰማያት እና ምድርም፡ በውስጣቸው ያለው ሁሉ ለርሱ (ለአላህ) ያጠራሉ(ያወድሳሉ)፤ ከነገርም ሁሉ ከማመስገን ጋር የሚያጠራው (የሚያወድሰው) እንጂ አንድም የለም፤ ነገር ግን የነሱን ማጥራት አታውቁም እሱ (አላህ) ታጋሽ መሃሪ ነው፡፡›› ሱረቱል ኢስራዕ 44
ﺃَﻟَﻢْ ﺗَﺮَ ﺃَﻥَّ ﺍﻟﻠَّﻪَ ﻳُﺴَﺒِّﺢُ ﻟَﻪُ ﻣَﻦْ ﻓِﻲ ﺍﻟﺴَّﻤَﺎﻭَﺍﺕِ ﻭَﺍﻟْﺄَﺭْﺽِ ﻭَﺍﻟﻄَّﻴْﺮُ ﺻَﺎﻓَّﺎﺕٍ ﻛُﻞٌّ ﻗَﺪْ ﻋَﻠِﻢَ ﺻَﻠَﺎﺗَﻪُ ﻭَﺗَﺴْﺒِﻴﺤَﻪُ ﻭَﺍﻟﻠَّﻪُ ﻋَﻠِﻴﻢٌ ﺑِﻤَﺎ ﻳَﻔْﻌَﻠُﻮﻥَ ( 41 )
‹‹ለአላህ በሰማየት ና በምድር ውስጥ ያለ ሁሉ ፤በራሪዎችም ክንፎቻቸውን ( አየር ላይ የዘረጉ) ሆነው ለርሱ (ለአላህ) የሚያጠሩ (የሚያወድሱ) መሆናቸውን አላወቅክምን ? ሁሉም ስግደቱን እና ማጥራቱን በእርግጥ አወቀ፡፡ አላህም የሚሰሩትን ሁል አዋቂ ነው፡፡››
ሱብሃነላህ !! እናንተዬ እጅግ በጣም አይደንቅም!! ? አድንደው ምንስ ተሰማቹ ? እንዲህስ ብላቹ ምን ትሉ ይሆን? ነጎድጓድም ጌታውን (ሱወ) ያወድሰዋል፡፡ አላህም እንዲህ ይላል፡፡
ﻭَﻳُﺴَﺒِّﺢُ ﺍﻟﺮَّﻋْﺪُ ﺑِﺤَﻤْﺪِﻩِ ﻭَﺍﻟْﻤَﻠَﺎﺋِﻜَﺔُ ﻣِﻦْ ﺧِﻴﻔَﺘِﻪِ
‹‹ነጎድጓድም አላህን በማመስገን ያጠራል፤ መላእክትም እርሱን በመፍራት( ያጠሩታል)……….››
እስኪ እናስበው እኚህ እኛ ዘንድ ትኩረት ማንሰጣቸው ፍጥረታት እንኳን ጌታቸውን እንዲህ ሲያጠሩ፤ እኔ እና አንተ/ቺ ግን የት ይሁን ያለነው? እናንተ ምድር ላይ ምትክ አድርጎ የሾማቹህ ያላህ ባሪያዎች ሆይ እወቁ!! ፍጥረተ አለሙ ሁሉ፡ በሰማይም በምድርም ያለ ሁሉ አላህን ያወድሳል፡፡ እንደው እስኪ የአላህን ፍጥረታት ቆጥረን እንኳን ባንዘልቃቸውም ፤በሰማያት ና በምድር ካሉት ፍጥረታት ውስጥ የተወሰኑትን ወደ አእምሮዋችን በማምጣት ለተወሰኑ ደቂቃዎች ተፈኩር እናድርግ፡፡ የውሀ ጅረቶች፤ ዛፎች፤ አእዋፍ፤ ጥቃቅን ነፍሳት፤ በራሪዎች፤ ከምድር ስር የሚኖሩ ትላትሎች፤ በውሀ ውስጥ የሚኖሩ ነፍሳት (አሳ፤ ዘንዶ፤ዶልፊን፤ ጉማሬ፤ አዞ………….) ፤ከድንጋይ ስር የሚኖሩ እንቁራሪቶች፤ በሆዳቸው የሚጎተቱ እንሰሳቶች ፤ አውሬዎች፤………………ሱበሃነላህ!! የምናወቀው የማነውቀው፤ ነፍስ ያለው ነፍስ የሌለው ሁሉ አላህን ካወደሰ፤ ለአላህ ሱጁድ ካደረገ፤ እኔ እና እናንተስ? ጠግበን በልተን፤ ጠግበን ጠጥተን፤ ነግደን ውለን፤ ጤና ተሰጥቶን፤ ተመችቶን ውለን፤ ተመችቶን አድረን፤ ከብርድ ተጠብቀን ፤ ከፀሀይ ተጠልለን፤ የአላህን ራህመት በሰፊው እየተቋደስን ጌታችንን ማጥራት ምነው ተሳነን? ለሱስ መስገድን ምነው ኮራን?
ረመዳን ና ጁምዓ መስጂድ መሙላታችን
ከዚህ ውጪ ለምን ይሆን መቅረታችን?
ቀኑን ውለን በሰላም ስነገባ እቤታችን
ለምን ረሳን ማመስገኑን ጌታችንን ?
እኔስ ፈራሁኝ፤ ፈራሁኝ ለራሴ
በሰራሁት ወንጀል እንዳትጠፋ ነፍሴ፡፡
አላህ ሆይ ፀሀፊውንም አንባቢውንም ባወቁት የሚሰሩበት አድርጋቸው፡፡