ሙዘኪራ የአልዐቂደቱ አልዋሲጢያህ መልእክት
ለአንድ ሰው በጀነት ወይም በእሳት መመስከር፦
በጀነት መመስከር ሁለት አይነት ሲሆን ጥቅል እና ለእያንዳንዱ ሰው መመስከር ናቸው።
ጥቅል የሆነው ምስክርነት፡ አንድን ሰው በደረጃ ሳይነጥሉ ለሁሉም አማኞች በጀነት መመስከር ማለት ነው።
ማስረጃውም አላህ እንዲህ ይላል፡-
إِنَّ الَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ كَانَتْ لَهُمْ جَنَّاتُ الْفِرْدَوْسِ نُزُلًا الكهف:١٠٧
‹‹እነዚያ ያመኑትና መልካም ስራዎችን የሰሩ ጀነተል ፊርደውስ መስፈሪያ አላቸው፡፡”
ነጥሎ ለአንድ ግለሰብ መመስከር፦ ከቁርኣንና ከሐዲስ ማስረጃ እስካልመጣ አንድን ግለሰብ የጀነት ነው ብሎ መመስከር አይቻልም፡፡ መልዕክተኛው ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም በጀነት የመሰከሩለትን እኛም እንመሰክርለታለን፡፡ ለምሳሌ፡- አስሩ በጀነት የተበሰሩ ሰዎችን፣ ሣቢት ኢብኑ ቀይስ ቢን ሸማስ፣ ኡካሻህ ኢብኑ ሚህሰን እና ሌሎችም፡፡
ልክ እንደዚሁ በእሳት መመስከር በሁለት ይከፈላል፡፡
ጥቅል እና ለእያንዳንዱ ሰው መመስከር።
ጥቅል ምስክርነት፡- የካዱ ሰዎች በአጠቃላይ የእሳት ናቸው ማለት ሲሆን ማስረጃው የአላህ U ቃል ነው፡፡
‹‹እነዚያ በአንቀፆቻችን የካዱ እሳት እናስገባቸዋለን፡፡”
ነጥሎ አንድ ግለሰብ የእሳት ነው ብሎ መመስከር፡-
አንድ ግለሰብ የእሳት ነው ብሎ ለመመስከር በቁርኣን እና በሐዲስ ላይ የተመሰረተ ነው፡፡
ለምሳሌ፡- አቡ ለሀብ እና ባለቤቱ፣አቡ ጣሊብ፣ዓምር ኢብኑ ሉሀይእ፣ኢብኑ አልኹዛኢይ ሌሎችም (የእሳት ናቸው ብሎ መመስከር ይቻላል፡፡)
ሙዘኪራ
"የአል ዐቂደቱ አልዋሲጢያህ አጭር ማብራሪያ" ከሚለው መፅሐፍ የተወሰደ