አሳሳቢ ትምህርቶች ለህዝበ ሙስሊሙ الدروس المهمة لعامة الأمة
የአላህ
ስሞችና ባህሪዎችን ለማፅደቅ ትክክለኛው መንገድ አላህና መልዕክተኛው ያረጋገጡትን ያለ “ተህሪፍ” (ትርጉሙ
ሳይዛባ) ፣ ያለ “ተዕጢል” (ትርጉም የለሽ ሳይደረግ)፣ ያለ “ተክይፍ” (አይነቱ ሳይጠቀስ) እና ያለ “ተምሢል”
(አምሳል ሳይደረግለት) ማመን ነው፡፡
ተህሪፍ (ትርጉሙን ማዛባት) የተፈለገውን ትርጉም መቀየር ማለት ሲሆን በሁለት አይነቶች ይከፈላል፦
1. “ተህሪፉ ለፍዝ” (ቃሉን ማጥመም) ይህ የሚሆነው የቁርአን ወይም የሀዲስ ቃላቶች ላይ ሌላ ቃልን በመጨመር፣በመቀነስ ወይም አነባቡን በመለወጥ ነው፡፡ ለምሳሌ : ﺍﻟﺮَّﺣْﻤَٰﻦُ ﻋَﻠَﻰ ﺍﻟْﻌَﺮْﺵِ ﺍﺳْﺘَﻮَﻯ:طه :ه
`ኢስተዋ` የሚለውን `ኢስተውላ` በሚል መቀየር:: (በዚህ... ሳቢያ አላህ ዐርሽ ላይ ተደላደለ በሚል የሚሰጠውን ትርጉም ዐርሽን ተቆጣጠረ በሚል እንዲለወጥ ያደርጋል::)
2. ተህሪፉል መዕና (ትርጉሙን ማጣመም) የቁርአንና የሀዲስን ቃሎች አላህ ባልፈለገው ትርጉም መተርጐም ማለት ነው፡፡ ለምሳሌ “የድ” (እጅ) የሚለውን ሀይል ወይም ፀጋ በማለት ትርጉሙን መለወጥ::
እንዲህ አይነቱ ትርጓሜ ሸሪዓውም ሆነ ቋንቋው አይቀበሉትም፡፡
“ተዕጢል” (ትርጉም የለሽ ማድረግ) አላህ በምንም ባህሪ አይገለፅም ብሎ ማስተባበል ማለት ነው፡፡
በ”ተህሪፍ” እና በ”ተዕጢል” መካከል ያለው ለውጥ፡- “ተህሪፍ” ማስረጃዎች የሚደግፉትን ትክክለኛ ትርጉም በሐሰት ትርጉም መቀየር ሲሆን “ተዕጢል” ደግሞ ትክክለኛውን ትርጉም አግልሎ ያለ ተለዋጭ ትርጉም መተው ነው፡፡
“ተክይፍ” የባህሪውን ሁኔታና አይነት መወሰን ማለት ነው፡፡ ለምሳሌ የአላሀ እጅ እንዲህ አይነት ነው፣ አላህ ዐርሽ ላይ ሲደላደል በእንዲህ አይነት ሁኔታ ነው በመሳሰሉት መልኩ መዘርዘር ማለት ሲሆን ይህ ተግባር ስህተት ነው፡፡ ምክንያቱም ከአላህ በቀር የእርሱን ባህሪ ሁኔታ የሚያውቅ የለም፤ ፍጡራን ይህን ማወቅ አይችሉም፡፡
“ተምሢል” የአላህን ባህሪያቶች ማመሳሰል ማለት ነው፡፡ ለምሳሌ የአላህ መስሚያ እንደኛ ነው፣ የእርሱ ፊት እንደኛ ፊት ነው ማለት ነው፡፡
በዚህ ርዕስ ውስጥ ሶስት መሰረቶችን ተግባራዊ ማድረግ በአላህ ስሞችና ባህሪዎች ዙሪያ የተስተካከለ አቋም እንዲኖር ይረዳል፡
አንደኛው መሠረት፡ የአላህን ባህሪ ከፍጡራን ጋር ከማመሳሰል መጠንቀቅ፡፡

ሁለተኛው መሠረት፡ አላህና መልዕክተኛው እርሱን በሰየሙበት ስሞችና በገለፁበት ባህሪያት በሚገባው መልኩ ማመን፡፡
ሶስተኛው መሠረት፡ የአላህን ባህሪያት አይነትና ሁኔታዎችን ማወቅ ስለማይቻል ለማወቅ ከመቋመጥ መቆጠብ፡፡
እነዚህን ሶስት መሠረቶች ያረጋገጠ በአላህ ስሞችና ባህሪዎች ትክክለኛ የሆነውንና ታላላቅ ዑለማዎች ያፀደቁትን እምነት ያረጋግጣል፡፡