ሐሰን
ታጁ ስለ አንድነት ስለ ወንድማማችነት የሚስብከው በሚጠቅመን መልኩ አይደለም። ስለ አንድነት አይሰብክም አልልም።
ነገር ግን የሚጣራለት አንድነት በሱ ብልሹ የአስተሳሰብ ቅኝት የተቀኘ አንድነት ነው። “አትጨቃጨቁ” እያለ በሺርክ
ወደተወረረው መውሊድ በሙሉ ሃይሉ ዑለማዎችን እያብጠለጠለ፣ እየዋሸም ጭምር ይጠራናል። ነገ ደግሞ “አትጨቃጨቁ” ብሎ
ለሙዚቃ ወግኖ ልባችንን ያወልቀናል። ሌላ ጊዜም “አትጨቃጨቁ” ብሎ ወደ አሽዐርያህ ይጠራናል። “አትጨቃጨቁ ”
እያለ የተወሱል ቀሚስ አልብሶ ሙታንን ወደማምለክ እየተጣራ ይነተርከናል። ጠብቁ! በሐሰን ታጁ “አትጨቃጨቁ” ርእሶች
ገና ብዙ እንጨቃጨቃለን። እንዲህ ነው ወደ አንድነት መጣራት። ዑለማእ እያብጠለጠሉ፣ ኢትዮጵያዊ እስልምና
ኢትዮጵያዊ ወዙን እንደያዘ እንዲቆይ አይነት እየሰበከ፣ በሃሳብ የማይጋሩትን በፅንፈኝነት እየወረፈ የታል
“አትጨቃጨቁ”?!
“በሳውዲም ሆነ በሌሎች ሰለፊ/ወሃቢ ቀመስ እስላማዊ ዩኒቨርሲቲዎችእና ተቋማት ወይም ሰለፊ/ወሃቢ ስብእናዎች የሚሰሩ ጥናትና ምርምሮች በሙሉ ከሱፍያ መስመር ጋር የተገናኙ አጀንዳዎችን የሚያዩበት መነጽር ምንግዜም ጥቁር
ነው” ይለናል። [መውሊድ: 198]
ግን ሱፍያ ቀመስ ተቋማትና ስብእናዎች ውሀቢ የሚሉትን ክፍል የሚያዩበትስ መነፅር ምን አይነት ነው? ለማንም እንደማይሰወር ባውቅም በሀሰን ቋንቋ ሲገለፅ እንመልከተው። ይሄውና፦
“መውሊድን ከታሪካችን ነጥለን ማውጣት የሚቻል አይሆንም። እርሱን ስንጥል የሚተርፈን ነገር የለምና ሙሉ ታሪካችንን አብረን እንወረውራለን። ይህንን ማንታችንን የዘነጋ ወይም ያጣጣለ የተሀድሶ ንቅናቄ “አረም እንጂ” ሰብል አይሆንም። “እንክርዳድ እንጂ” ስንዴ አይሆንም። «ለጊዜው የሚበጅ ቢመስለንም ውሎ አድሮ ጥፋት ማስከተሉ አይቀርም።»” [መውሊድ: 219‐220]
ዑለማዎችን እያብጠለጠለ፣ በዒልም አማኔ ሸፍጥ ኦየፈፀመ፣ በሀሳብ የማይጋሩትን የነቢዩን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ቤተሰቦች በመጥላት በነስብ ተውሳክ፣ የነቢዩን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ስም መወሳትን በመጥላትና መሰል እጅግ አደገኛ ወንጀሎች እየወነጀለ፣ እንደ አረም፣ እንደ እንክርዳድ እየሳለ “አትጨቃጨቁ” እያለ ሊሸብበን ይሞክራል። የሰከነ ምሁራዊ ውይይት በማድረግ ስም እየሰበከ ያስተኛናል።
[“መውሊድ: ታሪክ፣ ግድፈት፣ እርምት ከሚለው የኢብኑ ሙነወር መፅሀፍ ከገፅ 330‐331 የተወሰደ”]