Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

የአላህ ባህሪያት ስለተወሱባቸው ሐዲሦች የኢስላም ምሁራን አቋም!



የአላህ ባህሪያት ስለተወሱባቸው ሐዲሦች የኢስላም ምሁራን አቋም!

ታዋቂው አል-ኢማም አት-ቲርሚዚ በታዋቂው የሐዲሥ ጥራዛቸው አንዳንድ የአላህ ባህሪያት ስለተወሱባቸው ሐዲሦች የኢስላም ምሁራን የተናገሩትን እንዲህ ሲሉ ያስተላልፋሉ፦

« ..በርካታ የእውቀት ባለቤቶች የአላህ ባህሪያትና ጌታ በየለሊቱ ወደ ቅርቢቱ ሰማይ መውረዱ ስለተወሳባቸው ይህን መሰል የሐዲሥ ዘገባዎች እንዲህ ብለዋል:- “በዚህ ላይ ያሉ ዘገባዎች የተረጋገጡ ናቸው፤ ይታመንባቸዋል፤ (በንፅፅር) አይገመትም፤ እንዴትም አይባልም” ብለዋል፤ እንደዚሁ ከማሊክ፣ ከሱፍያን ኢብን ዑየይና እና ከዐብዱላህ ኢብኑ’ል-ሙባረክ እነኚህን ሀዲሦች አስመልክቶ “ያለ እንዴት (ስለ ሁነታው ሳታወሱ) (ተቀብላችሁ) አስኪዷቸው!” ማለታቸው ተዘግቧል። (የተቀሩት) የአህሉ’ስ-ሱናህ ወል-ጀማዓህ ሊቃውንት አቋምም እንዲሁ ነው። ጀህሚይ-ያዎች ግን እነዚህን ዘገባዎች አስተባበሉ፤ “ይህ ማመሳሰል ነው!” አሉም!
አላህ ከአንድ በላይ ቦታዎች ላይ እጅን፣ መስማትንና ማየትን በርግጥ አውስቷል፤ ጀህሚይ-ያዎች ግን እነዚህን አንቀፆች በ‘ተእዊል’ ተርጉመው የእውቀት ባለቤቶች ከገለፁት በተለየ መልኩ አብራሯቸው! እናም “አላህ ኣደምን በእጁ አልፈጠረም” አሉ! እንዲሁም “እዚህ ቦታ ላይ የ‘እጅ’ ትርጓሜ ‘ሀይል’ ነው!” አሉ! ኢስሓቅ ኢብኑ ኢብራሂም [ኢብኑ ራሀወይህ] እንዲህ አሉ፦ “ማመሳሰል የሚሆነው “እንዲህ ያልለ ወይም ይሄ አይነት እጅ”፣ ‘እንዲህ ያልለ ወይም ይሄ አይነት መስማት’ ሲባል ነው፤…ነገር ግን አላህ እንደተናገረው ‘እጅ፣ መስማት፣ ማየት’ ብሎ ‘እንዴት’ ካላለ፣ ‘እንዲህ አይነት፣ እንዲያ ያለ መስማት..’ ካላለ ማመሳሰል አይሆንም። አላህ ራሱ በመፅሃፉ እንዳለው ‘እንደርሱ ያልለ (አምሳያ) ምንም የለም፤ እርሱም ሰሚውና ተመልካቹ ነው’ [አሽ-ሹራ 11]»

[“ሱነኑ’ት-ቲርሚዚይ” ኪታቡ’ዝ-ዘካህ፤ ከሐዲሥ ቁጥር (662) በኋላ]

«..وقد قال غير واحد من أهل العلم في هذا الحديث وما يشبه هذا من الروايات من الصفات، ونزول الرب - تبارك وتعالى- كل ليلة إلى السماء الدنيا، قَالُوا: قَدْ ثبتت الرِّوَايَاتُ فِى هَذَا، وَيُؤْمَنُ بِهَا، وَلاَ يُتَوَهَّمُ، وَلاَ يُقَالُ: كَيْفَ. هَكَذَا رُوِىَ عَنْ مَالِكٍ وَسُفْيَانَ بْنِ عُيَيْنَةَ وَعَبْدِ اللَّهِ بْنِ الْمُبَارَكِ؛ أَنَّهُمْ قَالُوا فِى هَذِهِ الأَحَادِيثِ:أَمِرُّوهَا بِلاَ كَيْف. وَهَكَذَا قَوْلُ أَهْلِ الْعِلْمِ مِنْ أَهْلِ السُّنَّةِ وَالْجَمَاعَةِ، وَأَمَّا الجَهْمِيَّةُ فَأَنْكَرَتْ هَذِهِ الرِّوَايَاتِ وَقَالُوا: هَذَا تَشْبِيهٌ، قَدْ ذَكَرَ اللَّهُ عَزَّ وَجَلَّ فِي غَيْرِ مَوْضِعٍ مِنْ كِتَابهِ اليَدَ وَالسَّمْعَ وَالبَصَرَ، فَتَأَوَّلَتِ الجَهْمِيَّةُ هَذِهِ الآيَاتِ؛ فَفَسَّرُوهَا عَلَى غَيْرِ مَا فَسَّرَ أَهْلُ العِلْمِ، وَقَالُوا: إِنَّ اللَّهَ لَمْ يَخْلُقْ آدَمَ بِيَدِه! وَقَالُوا: إِنَّ مَعْنَى اليَدِ هَاهُنَا القُوَّة! وقَالَ إِسْحَاقُ بْنُ إِبْرَاهِيمَ: إِنَّمَا يَكُونُ التَّشْبِيهُ إِذَا قَالَ: يَدٌ كَيَدٍ، أَوْ مِثْلُ يَدٍ، أَوْ سَمْعٌ كَسَمْعٍ، أَوْ مِثْلُ سَمْعٍ... وَأَمَّا إِذَا قَالَ كَمَا قَالَ اللَّهُ تَعَالَى: يَدٌ، وَسَمْعٌ، وَبَصَرٌ، وَلاَ يَقُولُ: كَيْفَ، وَلاَ يَقُولُ: مِثْلُ سَمْعٍ، وَلاَ كَسَمْعٍ، فَهَذَا لاَ يَكُونُ تَشْبِيهًا، وَهُوَ كَمَا قَالَ اللَّهُ تَعَالَى فِي كِتَابهِ: {لَيْسَ كَمِثْلِهِ شَيْءٌ وَهُوَ السَّمِيعُ البَصِيرُ} [الشورى: ١١]
(سنن الترمذي، كتاب الزكاة، بعد حديث رقم: 662)

☞ “የአማኞች ጋሻ”
#አስማዕወሲፋት

የፌስ ቡክ ገፃችንን ላይክ ያድርጉ
https://www.facebook.com/asmaewesifat
ሼር ማድረግም እንዳይረሱ