Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ተውሂድን ማወቅና መቀበል ከሚያስገኛቸው ጥቅሞች

📎 ተውሂድን ማወቅና መቀበል ከሚያስገኛቸው ጥቅሞች፤
አላህ፤ በጌታነቱ፣ በተመላኪነቱ፣ በስሞቹና በባህሪዎቹ አንድ መሆኑን በሚገባ ያመነ ሰው ከሚያገኛቸው ውጤቶችና ፋይዳዎች ጥቂቶቹን እንደሚከተለው ለመዘርዘር እንሞክራለን፡፡


✅1ኛ. አንድ ባሪያ በዚህ ሰበብ የዱንያንና የአኼራን እድለኝነት ይጐናፀፋል፡፡ በሁለቱም ሀገሮች የሚገጥመው ስኬት የሚረጋገጠው በአላህ በማመን ብቻ ነው፡፡
✔የስኬቱ መጠን በአላህ በስሞቹና በባህሪዎቹ ባለው እምነት ልክ ነው፡፡

✅2ኛ. አንድ ሰው በአላህ፣ በስሞቹና በባህሪዎቹ የሚኖረው እምነት አላህን በሚገባ ለመፍራትና ትዕዛዙን ለመፈፀም ምክንያት ይሆነዋል፡፡
✔ ጌታውን ይበልጥ ባወቀ ቁጥር ወደርሱ ይበልጥ የቀረበ፣ እርሱን የሚፈራ፣ አምልኮውን በሚገባ የሚፈፅምና ኃጢአቶችን የሚርቅ ይሆናል፡፡

✅ 3ኛ. አንድ ባሪያ በተዉሂድ እምነቱ በዱንያና በአኺራ የልብ መረጋጋትን፣ የህሊና እረፍትን፣ ሰላምና መመራትን ይጐናፀፋል፡፡
አላህ እንዲህ ይላል፦
الَّذِينَ آمَنُوا وَتَطْمَئِنُّ قُلُوبُهُم بِذِكْرِ اللَّهِ أَلَا بِذِكْرِ اللَّهِ تَطْمَئِنُّ الْقُلُوب
ُ
‹‹ እነዚያ ያመኑ ልቦቻቸውም አላህን በማውሳት የሚረጋጉ ናቸው፡፡ ንቁ! አላህን በማውሳት ልቦች ይረካሉ፡፡›› (አል ረዕድ 28)

✅ 4ኛ. በአኺራ መልካም ምንዳን የማግኘት መስፈርቱ በአላህ ማመን ነው፡፡
✔ አንድ ሰው በአላህ በማመኑ እና ግዴታዎችን በመወጣቱ የአኺራን መልካም ምንዳ አግኝቶ የሰማይና የምድር ስፋት ያለውን ጀነት ያገኛል፡፡ አይን አይቶት፣ ጆሮም ሰምቶት፣በሰው ልብ ውል ብሎ እንኳን የማያውቀውን ፀጋ ይጐናፀፋል፡፡

በአንፃሩ ደግሞ ከብርቱው የእሳት ቅጣት ይድናል፡፡
ከዚህ ሁሉ የሚበልጠው ጸጋ ደግሞ የአላህን ውዴታ ማግኘቱ እና የአላህ ቁጣ የማያገኘው መሆኑ ነው፡፡ በትንሳኤ ዕለት የአላህን የተከበረ ፊት በማየት ይደሰታል። ያለምንም ችግር በደስታ ይንፈላሰሳል፡፡
✅ 5ኛ. በአላህ ማመን ስራዎችን የተስተካከሉና ተቀባይነት ያላቸው ያደርጋቸዋል፡፡ እምነት ከሌለ ግን ምንም የበዛ ስራ ቢሆን ተቀባይነት ሳይኖረው ወደ ሰሪው ይመለሳል፡፡
አላህ እንዲህ ይላል፦
وَمَن يَكْفُرْ بِالْإِيمَانِ فَقَدْ حَبِطَ عَمَلُهُ وَهُوَ فِي الْآخِرَةِ مِنَ الْخَاسِرِين
َ
‹‹ከእምነትም የሚመለስ ሰው በእርግጥ ሥራው ተበላሸ፡፡ በመጨረሻም ቀን እርሱ ከከሳሪዎቹ ነው፡፡›› (አል ማኢዳህ 5)

وَمَنْ أَرَادَ الْآخِرَةَ وَسَعَى لَهَا سَعْيَهَا وَهُوَ مُؤْمِنٌ فَأُولَئِكَ كَانَ سَعْيُهُم مَّشْكُورًا
‹‹መጨረሻይቱንም ዓለም የፈለገ ሰው፤ እርሱ አማኝ ኾኖ ለርሷ (ተገቢ) ሥራዋን የሠራም ሰው እነዚህ ሥራቸው የተመሰገነ ይሆናል፡፡››
(አል ኢስራእ 19)

✅ 6ኛ. ትክክለኛ የሆነ ተውሂድ ፅናትን ያጎናፅፋል። አማኙ ሀቅን በማወቅና ያወቀውንም በመተግበር ላይ እንዲፀና ይረዳዋል።
✔ ጠቃሚ ግሳጼዎችን ለመቀበል ራሱን ያዘጋጃል። ከጥመት ፍልስፍናዎች የራቀ፣ ፍላጐቱ ያማረ፣ ለመልካም ተግባራት የሚሽቀዳደም፣ የተከለከሉና የተጠሉ ነገሮችን የሚርቅ፣ መልካም ስነምግባሮችን የተላበሰ ይሆናል፡፡
✅ 7ኛ. አማኞች፤ በሚገጥሟቸው እንደ ሀዘን እና ደስታ የመሳሰሉ ነገሮችን ሁሉ አላህ በሚወደው መልኩ ያስተናግዳሉ።
☞በደስታ ጊዜ፤ በእምነታቸው በመታገዝ አላህን በማመስገንና በማወደስ የእሱን ፀጋ እሱ በሚወደው መልኩ ይጠቀሙበታል፡፡
☞በችግርና በሀዘን ጊዜም እምነታቸው ፅናትን ያላብሳቸዋል፡፡
☞በፍራቻ ጊዜም በእምነታቸው ይታገዙና ልባቸው ረግቶ ጌታቸው ላይ ያላቸው መተማመን ይጠነክራል፡፡
☞አላህን ሲታዘዙና መልካምን ለመስራት ሲታደሉ ደግሞ ይህ የአላህ ፀጋ እና ውለታ መሆኑን አውቀው ምስጋናቸውን ይበልጥ ለማሟላት በመጣር አላህ እንዲያፀናቸውና እንዲቀበላቸው ይለምናሉ፡፡
☞ ሀጢአትን ሲፈፅሙ ደግሞ እምነታቸው ወደ ንስሃ ይገፋፋቸዉና ከሀጢአት ክፋትና መዘዝ ለመላቀቅ ይጥራሉ፡፡
🔗 በአጠቃላይ የአማኞች ተግባር የሚታገዘው በአላህ ላይ ባላቸው እምነት ነው፡፡
✅ 8ኛ. የአላህን ስሞችና ባህሪዎች ማወቅ አላህን መውደድን ያስገኛል፡፡ ምክንያቱም የአላህ ስሞችና ባህሪዎች በሁሉም መልኩ የተሟሉ ሲሆኑ ነፍስ ደግሞ ሙሉዕን ነገር ትወዳለች፡፡
✔የአላህ ውዴታ በልብ ውሰጥ ከፀና አካልም መልካምን ለመስራት ታዛዥ ይሆናል።
🔗 ሰዎችም የተፈጠሩበትን ዓላማ ከግብ በማድረስ አላህን በብቸኝነት ያመልካሉ፡፡
✅9ኛ. የአላህን ስሞችና ባህሪዎችን ማወቅ አላህ የፍጡራኖችን ጉዳይ በማስተካከል ብቸኛ መሆኑን እርግጠኛ እንድንሆን ያደርጋል፡፡
✔ተውሂድ የዱንያም ይሁን የአኺራን መልካም ነገሮች ሁሉ ለማሳካት በአላህ ብቻ እንድንመካ ያደርጋል::
🔗 በአላህ የተመካ እርሱ በቂው ነውና አማኝ ሰው እውነትም እድለኛ ነው፡፡
🔚 ዓላማችን ኢስላማዊ እውቀትን ማዳረስ ነው::