Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

የሰለፎች አቋም የተገነባባቸው ሁለቱ መሰረቶች

የሰለፎች አቋም የተገነባባቸው ሁለቱ መሰረቶች

በጥቅሉ ስለ አላህ ባህሪዎች ያላቸው አቋም በሁለት መሰረቶች ላይ የተገነባ ነው።

የመጀመሪያው፡

አላህ እንደ ማንገላጀት፣ እንቅልፍ፣ አቅም ማጣት እና አለማወቅን ከመሳሰሉ የጉድለት ባህሪዎች ሁሉ የነጻ ነው፤

ሁለተኛው፡

አላህን ከፍጥረታት ምንም ነገር በምንም አይነት ባህሪ አይመስለውም፤ አላህም ከጉድለት ሁሉ በነጹ ምሉዕ ባህሪዎች ይገለጻል።

ይህንን ከሚያብራሩ ቁርዓናዊና ሀዲሳዊ መረጃዎች መካከል፤

የጉድለት ባህሪዎችን “ነፍይ” ዉድቅ ከሚያደርጉ መረጃዎች መካከል፦

«لَيْسَ كَمِثْلِهِ شَيْءٌ ُ»

‹‹የሚመስለው ምንም ነገር የለም፡፡»
(አል ሹራ 11)

ምሉዕ ባህሪዎችን ከሚያጸድቁ መረጃዎች

«وَهُوَ السَّمِيعُ البَصِيرُ»

«እርሱም ሰሚው ተመልካቹ ነው፡፡››
(አል ሹራ 11)

የጉድለት ባህሪዎችን “ነፍይ” ዉድቅ ከሚያደርጉና ምሉዕ ባህሪዎችን ከሚያጸድቁ መረጃዎች መካከል፤

قوله تعالى: (وَتَوَكَّلْ عَلَى الْحَيِّ الَّذِي لا يَمُوتُ ) الفرقان: 58

«በዚያም በማይሞተው ‘ሕያው’ አምላክ ላይ ተመካ፡፡» አልፉርቃን 58

የጉድለት ባህሪዎችን “ነፍይ” ዉድቅ ከሚያደርጉና ምሉዕ ባህሪዎችን ከሚያጸድቁ መረጃዎች መካከል፤

قوله تعالى: (اللَّهُ لا إِلَهَ إِلَّا هُوَ الْحَيُّ الْقَيُّومُ لا تَأْخُذُهُ سِنَةٌ وَلا نَوْمٌ ) البقرة : 255

«አላህ ከእርሱ በቀር በሀቅ የሚመለክ ሌላ አምላክ የለም፡፡ ሕያው ራሱን ቻይ ነው፡፡ ማንገላጀትም እንቅልፍም አትይዘውም፡፡»

የጉድለት ባህሪዎችን “ነፍይ” ዉድቅ ከሚያደርጉና ምሉዕ ባህሪዎችን ከሚያጸድቁ ሀዲሳዊ መረጃዎች መካከል፤

لما رفع بعض الصحابة أصواتهم بالتكبير وهم معه في السّفر قال رسول اللهه: "أيها الناس ارْبعُوا عَلَى أَنْفُسِكُمْ فَإِنَّكُمْ مَا تَدْعُونَ أَصَمَّ وَلَا غَائِبًا إِنَّمَا تَدْعُونَ سَمِيعًا بَصِيرًا ..."
رواه البخاري ومسلم

የአላህ መልዕክተኛ ﷺ በጉዞ ላይ እያሉ አንዳንድ ባልደረቦቻቸው ድምጻቸውን በጣም ከፍ አድርገው ተክቢር ሲያደርጉ እንዲህ ብለዋቸዋል፦

«እናንተ ሰዎች ሆይ! ለነፍሳችሁ እዘኑላት፤ እናንተ የምትጣሩት የማይሰማን አምላክ አይደለም፤ እሩቅም አይደለም። የምትጣሩት፤ ሰሚና ተመልካች የሆነውን አምላክ ነው።»

[ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል::]

የጉድለት ባህሪዎችን “ነፍይ” ዉድቅ ከሚያደርጉ የሀዲስ መረጃዎች

قال صلى الله عليه وسلم : "إن الله لا ينام ولا ينبغي له أن ينام" رواه مسلم في صحيحه

የአላህ መልዕክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦

«እናንተ አላህ አይተኛም፤ መተኛትም ለእርሱ ተገቢ አይደለም»
[ሙስሊም ዘግበውታል::]

☞ “የአማኞች ጋሻ”

# አስማዕወሲፋት

የፌስ ቡክ ገፃችንን ላይክ ያድርጉ
https://www.facebook.com/asmaewesifat
ሼር ማድረግም እንዳይረሱ