Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

የአላህ ስሞችና ባህሪዎችን አስመልክቶ የዚህ ኡማህ አበው ትውልዶች (ሰለፉሳሊህ) እና የታላላቅ ኢማሞች አካሄድ



የአላህ ስሞችና ባህሪዎችን አስመልክቶ የዚህ ኡማህ አበው ትውልዶች (ሰለፉሳሊህ) እና የታላላቅ ኢማሞች አካሄድ

قال شيخ الإسلام ابن تيمية: "وطريقة سلف الأمة وأئمتها: أنهم يصفون الله بما وصف به نفسه وبما وصفه به رسوله مِنْ غَيْرِ تَحْرِيفٍ وَلا تَعْطِيل، وَلا تَكْييفٍ وَلا تَمْثِيل، إثبات بلا تمثيل، وتنزيه بلا تعطيل، إثبات الصفات، ونفي مماثلة المخلوقات، قال تعالى: {لَيْسَ كَمِثْلِهِ شَيْءٌ} فهذا رد على الممثلة {وَهُوَ السَّمِيعُ الْبَصِيرُ} الشورى: 11 رد على المعطلة." منهاج السنة 2/523

ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ እንዲህ ብለዋል፡ {የዚህ ኡማህ ቀዳሚ ትውልዶች (ሰለፎች) እና ታላላቅ ኢማሞች አካሄድ፡- አላህ እራሱን በገለጸባቸው እና መልዕክተኛው እርሱን በገለጹባቸው ባህሪዎች አላህን ይገልጹታል፤ ይህንን ሲያደርጉም፤ ያለ “ተህሪፍ” (ትርጉም ማዛባት) እና ያለ “ተዕጢል” (ትርጉም አልባ ማድረግ)፣ እንዲሁም ያለ “ተክዪፍ” (የባህሪዉን ሁኔታና ምንነት መግለጽ) እና ያለ “ተምሢል” (አምሳያ ማድረግ) ነው፤ ባህሪዎችን ሲያጸድቁ አያመሳስሉም፤ አላህን ከአምሳያና ከጉድለት ባህሪዎች ሲያጠሩም ባህሪዎችን ትርጉም አልባ አያደርጉም፤ ከፍጡራን ጋር ያለን መመሳሰል ውድቅ በማድረግ ባህሪዎችን ማጽደቅ ነው መንገዳቸው።
አላህ እንዲህ ይላል፦

لَيْسَ كَمِثْلِهِ شَيْءٌ وَهُوَ السَّمِيعُ الْبَصِيرُ} الشورى: ١١}

‹‹የሚመስለው ምንም ነገር የለም፡፡ እርሱም ሰሚው ተመልካቹ ነው፡፡›› (አል ሹራ 11)

«የሚመስለው ምንም ነገር የለም» የሚለው ክፍል አላህን ከፍጥረታቱ ጋር ለሚያመሳስሉ “ሙሸቢሀዎች” መመሳሰል እንደሌለ ምላሽ ይሰጣል።
«እርሱም ሰሚው ተመልካቹ ነው፡፡›› የሚለው ክፍል ደግሞ ባህሪዎችን ለሚያስተባብሉ “ለሙዓጢላዎች” ለአላህ የተገቡ ባህሪያት እንዳሉት ምላሽ ይሰጣል።}

(ሚንሀጁ ሱናህ ቅጽ ገጽ 523 )

ይህንን ለማረጋገጥ እና ለማመሳከር ይረዳ ዘንድ ታላላቅ አሊሞች እና የመዝሀብ መሪዎች እምነት ምን እንደሚመስል ከራሳቸው ንግግሮች የተወሰዱ ዘገባዎች ተሰብስበው በዚህ ክፍል መጨረሻ ላይ ሰፍረዋል። የአህሉሱና ተጻራሪ የሆኑት ጀህሚያና ሙዕተዚላ ወይም አሻዒራ የተባሉት ቡድኖች በጽሁፎቻቸው፤ «አመለካከታችንን የሚደግፍ የኡለማዎች የአቋም ስምምነት ወይም ‘ኢጅማዕ’ አለ» ሲሉ የራሳቸውን ኡለማዎች የውስጥ ስምምነት ለመግለጽ እንጂ የሰለፎችን ኢጅማዕ ለማለት እንዳልሆነ ልብ ማለት ያስፈልጋል። አቋማቸው ከሰለፎች አቋም የተለየ እንደሆነ እና ከሰለፎች አቋም በተቃራኒው በዕውቀት እና በጥበብ የተሞላ እንደሆነ በድፍረት ይናገራሉ፡፡ ሱና የአንድነት መሰረት እንደሆነው ሁሉ ቢድዓ የልዩነት መንስኤና ምክንያት ነውና የሱና ተጻራሪዎች ብዙዉን ጊዜ በመሀከላቸው ስምምነት አይኖርም። ብዙዉን ጊዜ “አጅመዓ አስሀቡና” “የእኛ ባልደረቦች በዚህ ተስማምተዋል” በማለት ነው የሚገልጹት። የኡለማዎቻቸው ኢጅማዕ እንዳለበት በዚህ መልኩ የሚናገሩበት ጉዳይ እንኳ ሲፈተሽ፤ ብዙዉን ጊዜ ስምምነቱ ትክክል እንዳልሆነ በሚያሳይ መልኩ እነርሱ ዘንድ ከተከበሩና ንግግራቸው ቦታ ካለው ኢማሞቻቸው እንዳልተስማሙበት ግልጽ ይሆናል። የአህሉሱና ተጻራሪዎች፤ ወጣ ላለው አቋማቸው እንኳን የሰለፎችን አቋም ሊያቀርቡ ቀርቶ የራሳቸዉን ኡለማዎች ስምምነት እንኳ ማቅረብ አይችሉም።

ስለዚህ ሀቀኛውን የአህሉሱና መንገድ በመከተል ሰሀቦች እና ታቢዒዮች የነበሩበትን እምነት ለመያዝ “አላህና መልዕክተኛው ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ያረጋገጡትን ስምና ባህሪዎች ስናፀድቅ ከላይ የተጠቀሱትን አራት የጥመት በሮች መዝጋት የግድ ይላል።

☞ “የአማኞች ጋሻ”

#አስማዕወሲፋት

የፌስ ቡክ ገፃችንን ላይክ ያድርጉ
https://www.facebook.com/asmaewesifat
ሼር ማድረግም እንዳይረሱ