《 ፀፀት ፈፅሞ መጀመሪያ አትመጣም !》
እነሆ ለነፍሱ የሚበጀውን ባላወቀ አንድ ወጣት አረብ አቀጣጣይነት የተጀመረው የአረቡ አለም የውድቀት ጉዞ አምስት የመከራና የሰቆቃ ብሎም የውርደት አመታትን አስቆጠረ። በአረቡ አለም የሚገኙ ሙስሊሞች በነዚህ አመታት ውስጥ አጅግ የከፋ ጉዳት አግኝቷቸዋል።በሌላው አለም ያለው ሙስሊምም ውስጡ እጅግ እንዲደማ ሆኖአል። በምዕራባውያን የተሳከረ የፖለቲካ አስተሳሰብ የተጠመቁ ቂሎች <አብዮት> እና <የአረቡ አለም መነቃቃት> እያሉ የሚያሞካሹት ቀውስ ከጎበኛቸው ሀገራት መካከል የተረጋጋ ሀገር ማግኘት ህልም ሆነ። ችግሩ እጅግ በጠናበት በ ሶሪያ ያሉ ህፃናት ሚመገቡት አጥተው አፈር እና ሳር መብላታቸው ሲታሰብ እንዴት ሀዘንን መቋቋም ይቻላል??? ታላቁ ሰሀባ ሙአዊያህ አላህ ስራውን ይውደድለትና ያስተዳደራት ሻም የ ከሀዲያን ጉልበት ማሳያ ሆና ህዝቦቿ በስደት ሲያልቁ ማየት እንዴት የከፋ ነገር ነው። እጅግ የሚያሳዝነው የጥፋቱን መንስኤ ያልተረዱ በቁጥር የበዙ ሙስሊሞች መኖራቸው ነው። መለኮታዊውን ትእዛዝ ወደ ጎን ገሸሽ አድርጎ ውዳቂ የሰው ልጅ አስተሳሰቦችን መከተል በዱኒያም ሆነ በ መጪው አለም ውርደትን እንደሚያስከትል ጥርጥር የለውም።
“…ፀፀት በማይጠቅምበት ዕለት መፀፀታችሁ አይቀርም… " ይህ በ<አብዮቱ> ከተወገዱ መሪዎች አንዱ ህዝቦቹን ሲያስጠነቅቅ ተናገረው ተብሎ በማህበራዊ ድረ ገፅ ተሰራጭቶ ያነበብሁት ነው። ዛሬ ላይ አረቦች ከ አመታት በፊት የነበሩበትን ህይወት እጅጉን እየተመኙት መሆኑን ላስተዋለ የንግግሩን ትክከለኛነት ያረጋግጣል። በሀያሉ ጌታችን ላይ ያለን እምነት ፈፅሞ ተስፋ እንዳንቆርጥ ያደርገናል፤ እናም ነገሮች እንደሚስተካከሉ ተስፋ እናደርጋለን። በዳዮችም የእጃቸውን ማግኘታቸው ልክ ከለሊቱ ቀጥሎ ንጋት መምጣቱ እንደማይቀረው የተረጋገጠ ነው።
« አላህንም በደለኞች (በዳዮች) ከሚሰሩት ግፍ ዘንጊ ኣድርገህ አታስብ።
የሚያቆያቸው ዓይኖች በእርሱ እስከሚያፈጡበት ቀን ድረስ ብቻ ነው ። »
ኢብራሂም: 42