Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ያ ረብ! ከጥቂቶቹ ባሪያዎችክ አድርገኝ

ያ ረብ! ከጥቂቶቹ ባሪያዎችክ አድርገኝ

በአንድ ወቅት ዑመረል ፋሩቅ (ረዲየላሁ ዐንሁ) በአንድ የንግድ ስፍራ እያለፈ ሳለ አንድ ነጋዴ ፤ ‹‹ አላህ ሆይ! ከጥቂቶቹ ባሪያዎችክ አድርገኝ ›› ብሎ ዱዐ ሲያደርግ ይሰማዋል።

ዑመርም:- ‹‹ ይሄን ዱዐ ከየት ነው ያገኘከው?›› ብሎ ይጠይቀዋል

ነጋዴውም:- ‹‹ አላህ በቁርአኑ ከባሮቼ በጣም አመስጋኞቹም ጥቂቶች ናቸው›› ይላል አለው ።

ዑመርም እራሱን ወቅሶ አለቀሰ እንዲህም አለ:- ‹‹ ዑመር ሆይ ካንተ በላይ ሕዝቦችክ ዓዋቂዎች ናቸው። ያ አላህ! ከጥቂቶቹ ባሪያዎችክ አድርገኝ።» ብሎ እሱም ዱዐ አደረገ። ረዲየላሁ ዐንሁ

ዛሬ ላይ ብዙሃን ያሉበት መንገድ ቀጥተኛው መንገድ ተደርጎ መወሰድ ከተጀመረ ሰነባብቷል። ቁርኣናዊም ሆነ ሐዲሳዊ መረጃዎች እንደሚያሳዩን ግን ሐቅ ተከታዮች ሁሌም በቁጥር አነስተኛ መሆናቸውን ነበር።
በተመሳሳይም በምድር ላይ ብዙሃንን ያሉበት መንገድ ትክክል እንዳልሆነ ብሎም የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ምድር ላይ ካሉት ብዙሃኑን እንዳይከተሉ ሲገስፃቸውና ብዙሃኑን ግን ቢከተሉ መዳረሻው የከፋ መሆኑን እንዲህ ሲል አላህ ይነግራቸዋል።

وَإِن تُطِعْ أَكْثَرَ‌ مَن فِي الْأَرْ‌ضِ يُضِلُّوكَ عَن سَبِيلِ اللَّـهِ ۚ
((በምድርም ካሉት ሰዎች አብዛኞቹን ብትከተል ከአላህ መንገድ ያሳስቱሃል፡፡ )) [6:116]

አላህ ቁርኣን ላይ ስለ ብዙሃን ሲናገር :-
« ብዙሃኑ ...!»

✔ አያውቁም (7:187)
✔ አያመሰግኑም (2:243)
✔ አያምኑም (11:17)
✔ አመፀኞች ናቸው (5:59)
✔ ይስታሉ (6:111)
✔ እውነቱን አያውቁም (21:24)
✔ እንቢተኞች ናቸው (21:24)
✔ አይሰሙም (8:21)

ስለዚህም አላህ እንዳለው ከጥቂቶቹ ሁን !

✔ከባሮቼ በጣም አመስጋኞቹም ጥቂቶች ናቸው (34:13)
✔ ጥቂቶች እንጂ ከርሱ ጋር አላመኑም (11:40)
✔በመጠቀሚያ ገነቶች ውስጥ ሲሆኑ ፤ ከፊተኞቹ ብዙ ጭፍሮች ናቸው ፤ ከኋለኞቹም ጥቂቶች ናቸው (56:12-14)

አላህ ሆይ! ከጥቂቶቹ ባሪያዎቹ ያድርገን!