Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

መታኝና አለቀሰ፤ ቀድሞኝ ሄዶ ከሰሰ

"መታኝና አለቀሰ፤ ቀድሞኝ ሄዶ ከሰሰ"
ስለሺዓዎች ማውራት ከያዝን ሰንበት ብለናል፤ ዛሬ ደግሞ 'ሺዓዎች እውን የነቢዩን(ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ቤተሰብ ይወዳሉ ወይ?' የሚለውን ከራሳቸው ድርሳናት እንመልከት።
ሺዓዎች እምነታቸውን 'የአህለልበይት መዝሀብ' ሲሉ ይጠሩታል። ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ለነቢዩ(ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ቤተሰብ ፍቅር እንዳላቸው ይናገራሉ። ከዚህም አልፎ ሙሾ እያወረዱ፣ ደረታቸውን እየደቁ፣ ልብሳቸውን እየቀደዱ፣ ፀጉራቸውን እየነጩ፣ ፊታቸውን እየሟጨሩ ሲላቸውም በስለትና በብረት ሰውነታቸውን እያደሙ በግፍ ለተገደሉ የነቢዩ(ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ቤተሰቦች እናዝናለን ይላሉ።
እውነታው ግን ይህ አይደለም። ወደ ኋላ መለስ ብለን ታሪክን ስናጠና የዛኔ በአይሁዳዊው ኢብን ሰበእ የተመሰረተው የሺዓዎች ቅቤ አንጓች ቡድን የነቢዩን(ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ቤተሰብ እንረዳለን እያለ የሚያርድ መሰሪ አንጃ ሆኖ እናገኘዋለን። ስለሺዓዎች የአዞ እንባ እና አስጠቂነት ምንም እንኳ በአህሉሱናዎች ዘንድ የተዘገቡ ብዙ እውነታዎች ቢኖሩም ከራሳቸው ድርሳናት አጣቅሰን ምን ያህል ውሸታም እና ከዳተኛ እንደሆኑ በሶስት ምሳሌ እንመልከት።
=> በሺዓዎች ዘንድ እንደዋና ከሚታዩት ኪታቦች አንዱ በሆነው አል-ካፊ 8/338 ላይ አሊ(ረ.ዓ) በውስጣቸው ሸርን ደብቀው ከላይ ያንተ ደጋፊ ነን ስለሚሉት ሺዓዎች እንዲህ ይላል … "ሺአዎችን ብለያቸው 'ዋሲፋዎች'(1) እንጂ ሌላ ሁነው አላገኛቸውም፤ ብፈትናቸው አፈንጋጮች(ሙርተድ) ሁነው እንጂ አላገኛቸውም፤ ባጣራቸው ከሺህ አንድም ጥሩ አላገኝም"
=> በሌላ የሺዓዎች ኪታብ ላይ ሐሰን(ረ.ዓ) እንዲህ ይላል "በአላህ ይሁንብኝ 'የአንተ ቡድን(ሺዓ) ነን' እያሉ ከሚሞግቱት ይልቅ ሙዓዊያ(ረ.ዓ) ለኔ ጥሩ ሆኖ ይታየኛል። እኔን መግደል ፈለጉ ንብረቴንም ቀሙ ..." አልኢህቲጃጅ 2/10
=> አሁንም የሺዓዎች ኪታብ በሆነው ነሕጁል በላጋ ገፅ 142 እንደሰፈረው ሑሰይን ቢን አሊ(ረ.ዓ) የናንተ ሺዓ(ቡድን) ነን ብለው ወደ ኩፋ እንዲመጣ ከጠሩት በኋላ ጠላት ሁነው የተጋደሉትን ሺዓዎች እንዲህ ሲል ዱዓ ያደርግባቸዋል ... "አላህ ሆይ፣ ካቆየሀቸው መበተንን በትናቸው፣ በተለያየ መንገድ ላይም አድርጋቸው፣ የነርሱን ወዳጅነትም አትቀበላቸው፣ እነርሱ እኮ እንርዳችሁ ብለው ጠርተው ጠላት ሁነው የገደሉን ናቸው"
እኝህ ናቸው እንግዲ ሺዓዎች! አህሉሱናዎችን 'ለነቢዩ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ቤተሰብ ውዴታ የላቸውም' ሲሉ የሚከሱት ...
ገጣሚው እንዲህ ይላል
"መታኝና አለቀሰ
ቀድሞኝ ሄዶ ከሰሰ"
…………………………………………………………………
(1) 'ዋሲፋዎች' በማለት አሊ(ረ.ዓ) ሲገልፃቸው በትክክል ምን ለማለት እንደፈለገ አልደረስንበትም።
(2) ከላይ በራሳቸው በሺዓዎች ድርሳን በሰፈረው የሁሰይን(ረ.ዓ) ንግግር ትክክለኛ የሑሰይን ገዳዮች እነማን እንደሆኑ ግልፅ ይሆናል። ዛሬ ለሁሰይን ሞት እናለቅሳለን የሚሉት ሺዓዎች ታላቁን ሰሀቢና የነቢዩን(ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) የልጅ ልጅ ራሳቸው ገለው ነው እንግዲህ የአዞ እንባ የሚያነቡት። ለዚህ ነው ከራሳቸው የወጣው ሰይድ ሙህሲን አል አሚን አዕያኑ ሺዓ በተሰኘው መፅሀፍ ላይ በገፅ 1/34 ላይ እንዲህ የሚለው ...
"ከዒራቅ ሰዎች ሀያ ሺህ ያክል ለሁሰይን ቃል ገቡ፤ ሆኖም ካዱትና በሱ እና በጫንቃቸው ላይ ባለው ቃል ኪዳን አፈነገጡ፤ ከዛም ገደሉት"
ፔጁን በቴሌግራም ለመከታተል ...
https://telegram.me/lillahi