♻"ማነው ያለው?! "♻
🔊ባልና ሚስት በተለያዩ ምክኒያቶች ለተወሰነም ይሁን ላልተወሰነ ጊዜ ተራርቀው ቢኖሩ በዚህ ብቻ ጋብቻቸው አይፈርስም (ኒካሑ አይወርድም)✔✔
✍ሐቁ ይህ ሆኖ ሳለ ግን ብዙ ሰዎች፦"ባልና ሚስት ከ6 ወይም ከ 4 ወር በላይ ተለያይተው ከቆዩ ኒካሑ ይወርዳል" ሲሉ ይሰማል
👉 ይህ አባባል ከቁርኣንም ይሁን ከሐዲሥ እንዲሁም ከዑለማዎች ንግግር -👌ምንም ዓይነት መሰረትና ማስረጃ የሌለው
ተራ ወሬ ነው❗
📌ባል በአንደበቱ ወይም
📝በፊርማው
በተደገፈ ፅሁፉ ኒካሕ አውርጃለሁ እስካላለ ድረስ ወይም ሚስት ባሌ ለረጅም ጊዜ ከኔ በመራቁ ምክኒያት ሐቄን
አልጠበቀም :-በማለት ሸሪዓ ፍርድ ቤት ቃዲ ጋር ሔዳ አመልክታ ሁኔታውን አጣርቶ ኒካሑን ቃዲ እስካላወረደው ድረስ
ለ60ና ለ70 ዓመታትም ኧረ እስከ ህይዎታቸው ፍፃሜም ድረስ ተራርቀው ቢኖሩ በመራራቃቸውብቻ
ኒካሑአይወርድም
❗ ✍ ይህ በእንዲህ እንዳለ፥ ባል ሚስቱን ቢበዛ ከ6 ወራት በላይ ያለ ፈቃዷ ተለይቷት
ርቋትሊኖር አይገባም📍ይህንንም ማድረጉ ከሚስት ሐቆች መሐል አንዱ ሊባል የሚችልን ነገር ትቷል ቢባል እንጂ በዚህ ብቻ ኒካሑ አይወርድም
❗ ✆
✈ ችግርና የተለያዩ
ምክኒያቶች ያለያያቸው ባልና ሚስቶችን አላህበሰላምና በፍቅር ያገናኛቸው
🍃 🚫ያለ እውቀት ለሚናገሩም አደብ ይስጣቸው
✂ ✏መልእክቴ እዚህ አበቃ📎
✉አሕመድ ኣደም አሽሸራሪይ