Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ከሠለፎች ማኅደር ሱናን በመከተል ላይ ትጋት ይኑርህ !!!

ከሠለፎች ማኅደር
💭 أحرص على اتباع السنة
📝قال الإمام ابن القيم-رحمه الله-:
💭ሱናን በመከተል ላይ ትጋት ይኑርህ !!!
ኢብኑል ቀይም [አላህ ይዘንላቸውና] ቀጣዩን ብለዋል:-

«በታላቁ የጥም ቀን ሰዋች "ሐውድ" ከተሰኘው ኩሬ የመጠጣታቸው ሁኔታ የነቢዩን صلى الله عليه وآله وسلم ሱንና በተከተሉትና ከሱ በተጎነጩት ልክ ነው የሚሆነው።
ስለሆነም በዚህች ዓለም ከሱንናቸው በመጎንጨት የረካባት እዚያም ወደ ሐውዳቸው በመውረድ ይጠጣታል ይረካባታል።
ለነቢዩም صلى الله عليه وآله وسلم ታላላቅ የሆኑ ሁለት ኩሬዎች አላቸው።
እነሱም☞
1ኛው:- በዱንያ ህይወት ላይ ያለው ሲሆን እሱም ሱናቸው፣ ይዘውት የመጡት መልእክታቸው ሲሆን
2ኛው:- ደግሞ በመጨረሻዋ ቀን ያለው [አንዴ ከተጎነጯት ጥም የሚባል ነገር ዝር የማይልበት ሐውድ የተሰኘው] ኩሬ ነው።
👆 ስለዚህም በትንሳዔዋ እለት ከኩሬያቸው የሚጠጡት በዚህች ዓለም ህይወታቸው ሱናቸውን የተጠጧት [የተጎነጯት፣ ያጣጣሟት፣ የተላበሷት፣ በመተግበር የረኩባት] ናቸው።
🔹እንደሚታወቀው ከዚህች ኩሬያቸው የሚጠጡም የሚከለከሉም፣ ትንሽ የሚጠጡና በርከት አድርገው የሚጠጡም አሉ። [ሁሉም እንደየስራው ይታደላታልና]።»
📘إجتماع الجيوش الإسلامية ص: (85).
📘[ኢጅቲማዕ አልጁዩሹል ኢስላሚያ ገጽ 85]