የዘመናችን ታላቁ ሙሐዲስ ሸይኽ አልባኒ(ረሂመሁላህ) እንዲህ ብለዋል፦ "ባለንበት በአሁኑ ወቅት "ኢስላህ" ማስተካከል፣ማበጀት በአብዮት አይጀመርም…
እንዲሁም አመጸኛ ሙስሊም መሪዎች ላይ ማመፅና መፈንቅለ መንግስት ማድረግ ይቅርና ካፊር መንግስት ላይ እንኳ በመሳሪያ መውጣት የማበጀት መንገድ አይደለም።
"ኢስላህ" ተሐድሶ የሚጀምረው ከአስርት አመታት አንስቶ ዘውትር የምደጋግመው አባባል አለ፦
እርሱም፦ "ተስፊያ እና ተርቢያ" የሚባሉት ነገር ናቸው።
በዚህ አካሄድ ላይ አንድ ሰው አስታውሶ ተገንዝቦ የሚራመድ ከሆነ በቂ ነው።
በዚህ መንገድ ከእኛ ጋር ካልተጓዘ ሊያውቅ የሚገባው ነገር ቢኖር፦ ምን አይነት ሰው ይዞ እና እንዴት አብዮት እንደሚወጣ? ሊያስረዳን ይገባል።
እንደምናውቀው አብዛኛው ሰው (ጃሂል) ነው።
አብዛኛው ሸሪኣን ያቃል የሚባለው ሰው ደግሞ እኛን ይፃረራል… ሴቶቻቸው ለብሰው የተራቆቱ …
የግብይት ስርኣታቸው ደግሞ ከሸሪዓ አስተምህሮት ጋር ይፃረራል ወዘተ…
ሁላችንም እንደምናምነው ከሆነ የአላህ እርዳታ እና እገዛ ሙዕሚን ለሆኑ ባሮች ሊያገኙ ዘንድ መስፈርቱ፦
አንድ ቃል ነው እርሱም፦
"የአላህን(ዲን) ከረዳቹ… ይረዳችኋል።
የአላህ እርዳታ በሁለት መልኩ ይገኛል፦
የመጀመሪያው በሸሪዓዊ ዕውቀት ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ፦ ያወቅነው ተግባር ላይ በማዋል ነው።
ሁላችሁም እንደምታውቁት ሰለፎቻችን ዘንድ ከነበረው ሸሪዓዊ እውቀት በአሁኑ ወቅት ዕውቀታችን ከፍተኛ ከሐቅ መዘንበል ገጥሞታል …
ለዚህም ሲባል ሁላችሁም በምታውቁት ሐዲስ ላይ ተዘግቦ እንደመጣው ፦
ጅማሪው ላይ፦"በዒናህ"(የአራጣ አሰራር አንዱ ስርአት ነው) በተገበያያቹ ግዜ የበሬ ጭራ ይዛችሁ (ልማት) እያላችሁ…
መጨረሻም፦"ወደ ዲናችሁ እስክተመለሱ የማይነሳላችሁ ውርደትን በላያችሁ ያደርግባችኋል።"…
ዛሬ ዲናችን ውስጥ እጅግ ብዙ የሆኑ ግንዛቤዎች ገብተውበታል…
ቅርንጫፋዊ ርእሶች ብቻ ሳይሆን እነሱም እንደሚሉት መሰረታዊ አጀንዳዎች ላይ ጭምር የተሳሳተ ግንዛቤ አለ…
ሸሪኣዊ ህግጋት ላይ ብቻ ሳይሆን እንዲያውም ዐቂዳ ላይም ስህተቶች አሉ።
በወቅታችን አብዛኛው ሙስሊም አሽዓሪያ አሊያም ማቱሪዲያ ነው…
ታዲያ በነዚህ ነው ኢስላም ድል የሚያገኘውን?!…
ስለዚህ "ተስፊያ እና ተርቢያ" መኖር ይኖርባቸዋል ።
"ወደ ዲናችሁ እስክትመለሱ የማይላቀቃችሁ ውርደት የበላይ ያደርግባችኋል።" የሚለው፦
በትክክለኛ አረዳድ ወደ ዲናችሁ መመለስ ማለት ነው…
ስለዚህም ደዕዋችንን ስለ ትክክለኛው ኢስላም ግንዛብ በመስጠት መሆን አለበት…
በዚህም ላይ ተርቢያ ፣ ትምህርት በመስጠት፣ያላሰለሰ ጥረት ማድረግ የግድ ይላል…
" የዚያኔ በአላህ እርዳታ ሙዕሚኖች ተደሳቾች ናቸው።"
ከዚህ ውጭ ያለ አካሄድና መንገዶች፦
ሙስሊሞች ክብራቸው እና ልቅናቸው ሊመልሱ በፍጹም አይችሉም…
【ሲልሲለቱ አልሁዳ አቀኑት ካሴት ቁጥር (799)】
كلام يكتب بماء الذهب:
قال الشيخ محمد ناصر الدين الألباني - رحمه الله -:
إن الإصلاح اليوم لا يبدأ (بالثورة)..
(وبالخروج) على الحاكم الكافر..
فضلاً عن الخروج على الحاكم (الفاسق)..
وإنما (الإصلاح) يبدأ كما نقول نحن دائماً وأبداً..
من عشرات السنين "بالتصفية والتربية"..
فإن كان الرجل معنا في هذا المنهج (فيذكر) بهذا ويكفي..
وإن كان ليس معنا فينبغي أن يعلم..
وأن نفهم منه كيف يريد وبمن يريد أن يخرج؟..
أكثر المسلمين (جهلة)..
وأكثر المسلمين الذين يعلمون بعض الأحكام الشرعية هم (يخالفونها)..
فنساؤهم كاسيات عاريات..
ومعاملاتهم مخالفة لأحكام الشريعة في كثير من نواحيها إلخ...
ونحن جميعاً نعتقد بأن نصر الله لعباده المؤمنين..
مشروط بكلمة واحدة: {إن تنصروا الله}..
ونصر الله إنما يكون:
أولاً: بالعلم..
ثانياً: بالعمل..
والعلم اليوم كما تعلمون جميعاً..
فيه (إنحراف) كبير جداً عن العلم الذي كان عليه السلف الصالح..
ولذلك ففي الحديث الذي تعرفونه..
الذي مطلعه: "إذا تبايعتم بالعينة و أخذتم أذناب البقر..."..
إلى: "سلط الله عليكم ذلا لا ينزعه عنكم حتى ترجعوا إلى دينكم"..
الدين اليوم له مفاهيم (عديدة) جداً..
وليس فقط في الفروع..
بل وكما يقولون وفي الأصول..
ليس فقط في الأحكام..
بل وفي العقائد..
فأنتم تعرفون اليوم أكثر المسلمين إما أشاعرة أو ماتريدية..
أبهؤلاء ينتصر الإسلام؟!..
إذن لا بد من (التصفية والتربية)..
ف "سلط الله عليكم ذلا لا ينزعه عنكم حتى ترجعوا إلى دينكم"..
أي (بالمفهوم) الصحيح..
فإذن يجب أن (نبدأ) بتفهيم الناس هذا الإسلام بالمفهوم الصحيح..
وتربيتهم على ذلك..
{ويومئذ يفرح المؤمنون بنصر الله}..
أما غيرها من سبيل..
ما يمكن أبداً أن يعود إلى المسلمين عزهم ومجدهم..
انتهى كلامه رحمه الله .
سلسلة الهدى والنور.. شريط رقم: (799)..