"ሰላማዊ ሰልፍ"
የሚሉት ስሙ ብቻ እንጂ ሰላማዊ ከዛ ውጭ የጥመት፣ የጥፋት፣ ኢስላም የማያውቀው፣ ፖለቲከኞች በቅርብ አመታት ውስጥ
ወደ ኢስላሙ አለም ለማዝለቅና ሙስሊሙን መሳርያ ከታጠቁ ባለስልጣናት ፊት ለፊት ተፋጦ መስዋት (ፊዳ) እንዲሆን
ኢስላምን ሽፋን ያደረገ በኢስላም ስም የሚነግዱበት ፀያፍ ተግባር ነው።
ምእራቡ አለም ላይ እና ሰላም
ያለባቸው አረብ አገራት ላይ በሰላም ተቀምጠው ከጁምአ ሰላት በኀላ ከእስልምና ጋር የሚጋጩ የክህደት መፈክሮችን
እንዲፈከሩ የሚቀሰቀሱ ብሎም ንፁሀኑን መሳርያ ከታጠቁ ሀይሎች ጋር ተፋጠጥ ጀነት አለልህ ብለው የሚሰብኩ፣ ለዚህ
አላማ የሞቱትን ሰመአታት እያሉ የሚፎግሩ ዲያስፖራ ፖለቲከኞች አሉ።
የሙስሊሙ ህዝብ እንዲህ አይነት የማይሰሩት የሚናገሩ እኩይ ተግባር ያላቸውን ግለሰቦችም ሆነ ድርጅቶች ሊርቅ ይገባዋል።
ኢስላም ለእያንዳንዱ ችግር መድሀኒት አስቀምጧል። ለአንድ ችግር የማይገባውን መድሀኒት የወሰደ ግለሰብ ከችግሩ ሊወጣ ቀርቶ በችግር ላይ ችግር ነው የሚያጋጥመው።
ሙስሊሙ አረብ አገራት ላይ ሰላማዊ ተብሎ የተጀመረው የየጁምአው ሰለፍ ዛሬ ሰላማቸውን አሳጥቷቸው፣ በሚሊዬን
የሚቆጠሩ ሞተው፣ ተሰደው፣ ተደፍረው፣ ጠላት የነበራቸውን ንብረት እየዘረፈ፣ ሰላምን አጥተው የወንበዴ መጫወቻ
ሆነዋል። የናፈቁትን ነፃነት አይደለም ሊያገኙት የዛሬን በሰላም ማደር ትልቁ ምኞታቸው ሆኗል። ነብያት የሄዱበትን
መንገድ ያልሄድ 2 አገር ይከስራል።
የአእምሮ ባለቤቶች ከዚህ ብዙ ይማራሉ።