Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ሴት ልጅን ሸሪዐዊ ዕውቀት ማስተማር ሕብረተሰብን ማስተማር ነው!

ሴት ልጅን ሸሪዐዊ ዕውቀት ማስተማር ሕብረተሰብን ማስተማር ነው!
ሴቶች ...
– እናቶች
– እሕቶች
– ሚስቶች
– ልጆች ናቸው ።
ሴት ስትማር እራሷን ቀይራ ልጇንም በኢስላማዊ ተርቢያ ኮትኩታ ታሳድጋለች ። ያኔ ..
መጪው ትውልድም ከመሠረቱ ያብባል ። ሕፃናት አፋቸውን በ “ላኢላሃ ኢለላህ” በ “አላሁ አክበር” ከሊማ ይፈታሉ ። ለማንነታቸው ተምሳሌት ማንንም ሳይሆን ታላቁና ተወዳጁ የአላህ ነቢይ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለምን እና ሶሓቦችን ያደርጋሉ ። ገና በልጅነት አዕምሮዋቸው ግባቸውን በጀነቱል ፊርደውስ ይቀርፃሉ ። በኢስላም ውስጥ ለኢስላም ኖረው ለኢስላም መሞትን ይመኛሉ ። ያኛው ተናፋቂ የነሶሓቢው ኢብኑ ዑመር ፣ ኢብኑ መስዑድ (ሪድዋኑላሂ ዐለይሂም) ፣ የነ ኢማሙ ሻፊዒይ ፣ የነኢማሙ አሕመድ ፣ የነኢማም ቡኻሪ ፣ የነኢብኑ ሐጀር ፣ የነኢብኑ ተይሚያህ ፣ የነኢማም ዐብዱልወሃብ፣ የነኢብኑ ባዝ ፣ የነአልባኒ ተተኪ ትውልድ ይፈጠራል ።
በሽርክና ቢድዐ የተጨማለቀው ጨለማ ዘመን በዕውቀት ላይ በተመረኮዘው ተተኪ ትውልድ በተውሒድና በሱና ብርሐን ይታደሳል ።
በጭፍን ተከታይነት ፣ በዘር ወገንተኝነት ፣ በጅሕልና ፅልመት ፣ በአውሬነት ባሕሪ የተላበሰ ክፉ ዘመን የነገው እናቶች በገበዩት ሸሪዐዊ ዕውቀት እራሳቸውን ልጆቻቸውንም ኮትኩተው በኢስላማዊ አደብ በማሳደግ ትውልድን ሊቀይሩ ከምንም በላይ አስፈላጊና ይበልጥ የተገባ ነው ።
ስለዚህ ውዷ እሕቴ ይህን ሃላፊነትሽን ለመወጣት ዛሬውኑ ሸሪዐዊ ዕውቀትን መፈለግ ይኖርብሻል የሚለው ትልቁ ልባዊ ምክሬ ነው ።