Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

በሰውነታችን ላይ ያለ ዘይት ወይም ቅባት ውዱእ ስናደርግ ውሀ ወደ ቆዳችን እንዳይደርስ የሚያደርግበት ሁኔታ ሲፈጠር ምን ማድረግ ይኖርብናል?

#ፈታዋ_ተንቢሀት

🔗 በሰውነታችን ላይ ያለ ዘይት ወይም ቅባት ውዱእ ስናደርግ ውሀ ወደ ቆዳችን እንዳይደርስ የሚያደርግበት ሁኔታ ሲፈጠር ምን ማድረግ ይኖርብናል?

📄ተከታታይ መልእክቶች ከ "ፈታዋ ለሙስሊም ሴቶች" መፅሀፍ

👉🏻 ሸይኸ ሙሀመድ ኢብን ሷሊህ አል ዑሰይሚን

ጥያቄ፦ አንድ አሊም ሲናገሩ እንደሰማሁት በሰውነታችን ያለ ዘይት ውድእ ስናደርግ ውሀ ወደ ቆዳችን እንድይደርስ ሊያደርግ ይችላል። እኔ ደግሞ አንዳንድ ጊዜ ምግብ ሳዘጋጅ የዘይት ፍንጣሪ በጸጉሬና በሌላው የሰውነት ክፍል ላይ ያርፍል። ታዲያ በዚህ ጊዜ ውዱእ ላደርግ ስዘጋጅ በመጀመሪያ ይህንን ዘይት ያረፈበትን የሰውነት ክፍል ብቻ በሳሙና ማጠብ ነው ግዴታው ወይንስ በአጠቃላይ የሰውነቴን ሁሉ መታጠብ ይኖርብኛል? በተመሳሳይ ሁኔታም በህመም ምክንያት ፀጉሬ ላይ ዘይት አደርጋለሁ ስለሆነም ምን ማድረግ ነው ያለብኝ ?

መልስ፦ ይህንን ጥያቄ ከመመለሴ በፊት ሃያሉና የልቅና ባለቤት የሆነው አላህ በቁርአን እንደሚከተለው መናገሩን መግለጽ እፈልጋለው።

{ﻳَﺎ ﺃَﻳُّﻬَﺎ اﻟَّﺬِﻳﻦَ ﺁﻣَﻨُﻮا ﺇِﺫَا ﻗُﻤْﺘُﻢْ ﺇِﻟَﻰ اﻟﺼَّﻼَﺓِ ﻓَﺎﻏْﺴِﻠُﻮا ﻭُﺟُﻮﻫَﻜُﻢْ ﻭَﺃَﻳْﺪِﻳَﻜُﻢْ ﺇِﻟَﻰ اﻟْﻤَﺮَاﻓِﻖِ ﻭَاﻣْﺴَﺤُﻮا ﺑِﺮُءُﻭﺳِﻜُﻢْ ﻭَﺃَﺭْﺟُﻠَﻜُﻢْ ﺇِﻟَﻰ اﻟْﻜَﻌْﺒَﻴْﻦِ} المائدة 6

«እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ወደ ሶላት በቆማችሁ (ለመቆም ባሰባችሁ) ጊዜ ፊቶቻችሁን፣ እጆቻችሁንም እስከ ክርኖች እጠቡ፡፡ ራሶቻችሁንም (በውሃ) አብሱ፡፡ እግሮቻችሁንም እስከ ቁርጭምጭሚቶች (እጠቡ)፡፡» አል ማኢዳህ 6

ስለሆነም በቁርአን አንቀጽ የወረደው ትእዛዝ እንደሚያሳየን የተወሰነውን የሰውነት ክፍላችንን መታጠብ የተወሰነውን ደግሞ ማበስ እንደሚገባን ነው። ይህን ስናደርግ ማንኛውም ውሀ ወደ ቆዳችን እንዳይደርስ የሚያደርግን ነገር ማስወገድ እንዳለብን ግልጽ ነው።
በዚህም ምክንያት፤ አንድ ሰው ውዱእ በሚያደርግበት ጊዜ ሊያጥባቸው ግዴታ በሆኑበት የሰውነት ክፍሎቹ ላይ የሚገኝን ዘይት ማስወገድ ግድ ይለዋል።

ሆኖም ግን በሰውነቱ ላይ ያለው የዘይቱ ቅሪት ብቻ ከሆነ ያንን በማጠብ ካስወገደ በኋላ ውዱእ ማድረግ ነው። ለጠያቂዋ እህታችን የምንሰጣት ምክር ውድኡ በምታደርግበት ጊዜ በእጇ የሰውነት ክፍሎቿን በማሸት ዘይቱ በሚገባ መልቀቅና አለመልቀቁን ማረጋገጥ ያለባት መሆኑን ነው። ምክንያቱም በተለምዶ ዘይትና ውሀ የመቀላቀል ባህሪ የላቸውምና። እንደዛ ከሆነ ደግሞ ውሀው ዘይቱን አልፎ ወደ ቆዳዋ ላይደርስ ይችላል።

እንግዲህ ይህ እህታችን የተቀባችውን ዘይት በጠጣርነት (በመርጋት መልካ ካልሆነ) ውዱእ ማድረግን አይከለክላትምና በሳሙና መታጠቡም አስፈላጊ አይደለም። ስትታጠብ እጇን ቆዳዋ ላይ በማዟዟር ማሸት ይኖርባታል። ምክንያቱም ውሃው ቆዳዋ ላይ ሳያደርስ ኮለል ብሎ ሊወርድ ስለሚችል ነው።

© ተንቢሀት
https://www.fb.com/tenbihat

📱https://telegram.me/tenbihat