Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ሰላት ከሰገዱ በኋላ መስገጃዎ ላይ መፅናት ምን ያህል አጅር እንደሚያስገኝ ያውቃሉን?

ሰላት ከሰገዱ በኋላ መስገጃዎ ላይ መፅናት ምን ያህል አጅር እንደሚያስገኝ ያውቃሉን? የአላህ መልክተኛ e እንዲህ ብለዋል፦ “ከእናንተ መካከል አንዳቹ ሰላት የሰገደበት መስገጃው ላይ እስካለ እና ውዱእ እስካላጠፋ ድረስ መላኢካዎች በርሱ ላይ ሰለዋት ያወርዱለታል። “አላህ ሆይ ወንጀሉን ማረው፣አላህ ሆይ እዘንለት።” ይላሉ።” ቡኻሪ እና ሙስሊም ዘግበውታል ኢብኑ በጣል(ረሂመሁላህ) እንዲህ ይላሉ፦ “እጅግ ብዙ ወንጀል ያለበት ያለ ብዙ ልፋት ወንጀሉን አላህ እንዲያራግፍለት የሚፈልግ ሰው ካለ፦ መላኢካዎች እርሱ ላይ የሚያደርጉት ዱዓእና ኢስቲግፋር ይበዛለት ዘንድ ሰላት ከሰገደ በኋላ መስገጃው ላይ በመፅናት እድሉን ይጠቀም ።” [“ሸርሑ አልቡኻሪ”(2/95)] © www.nesiha.com