Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ኡሙ ሰለማ ረዲየላሁ ዓንሃ እንዲህ ትላለች “የአላህ መልእክተኛ( صلى الله عليه وسلم) ዘንድ ተወዳጁ ልብስ ....


عَنْ أُمِّ سَلَمَةَ قَالَتْ كَانَ أَحَبَّ الثِّيَابِ إِلَى رَسُولِ اللَّهِ -صلى الله عليه وسلم- الْقَمِيصُ.
ኡሙ ሰለማ ረዲየላሁ ዓንሃ እንዲህ ትላለች “የአላህ መልእክተኛ( صلى الله عليه وسلم) ዘንድ ተወዳጁ ልብስ ቀሚስ(ጀለቢያ) ነበር::”አቡዳዉድ በቁጥር {1762} ዘግበውታል::አልባኒ ሰሒህ ብለውታል::
የአላህ መልእክተኛ( صلى الله عليه وسلمይህ አይነቱን አለባበስ ይወዱት የነበረበው
1ኛ_ ከማንኛውም ልብስ በበለጠ መልኩ አካልን በደንብ ስለሚሸፍን
2ኛ_ አካል ላይ ቀለል ስለሚል
3ኛ_ ዋጋውም ዝቅተኛ ስለሆነ ከኢኮኖሚ አንጻር ተጠቃሚን ስለማይጎዳ
በጥቅሉ የአላህ መልእክተኛ( صلى الله عليه وسلم) ነጭ ልብስን መልበስ ይወዱ ነበር::ቲርሚዚ በዘገቡት ሐዲስ የአላህ መልእክተኛ( صلى الله عليه وسلم) እንዲህ ብለዋል: “ከልብሳቹ ነጭ ነጩን ልበሱ ምርጡ ልብሳቹ ነውና ሙታናቹንም በእርሱ ከፍኑ” ሱነኑ ቲርሚዚ በቁጥር፡994 ዘግበውታል
ቢጫ እና ሙሉ በሙሉ ቀይ የሆነ ልብስ መልበስን ከልክለዋል