ዜሮ ከተውፊቅ ከማል ( Md Tofik ) " ኢክዋኖች" ማን ናቸው?
ኢክዋን አል ሙስሊሚን እጅግ የዘመኑት
ባስተሳሰባቸው እጅግ የመጠቁት
ባካዳሚክ ትምህርት ደራርበው የጫኑት
አእመሯቸው ሰፋ ቦርቀቅ ረቀቅ አሉ
ሄዱ ተራመዱ ተጓዙ አለፉ
በተማሩበት መስክ ኢስላምን ሊያስፋፉ
የ ሹብሃት መዓት እየደረደሩ
የማያውቀውን ህዝብ እያደናገሩ
ቀጠሉ ጨመሩ በ ዲን ውስጥ ፈጥራ
ሱናን ተቃራኒ እጅጉን ሚያስፈራ
ግልጽልጽ ብሎ የሚታየውን የ ኢስላም ጎዳና
በረዙት ከለሱት አመጡ ፈተና
እንደየ አየሩ እንዳካባቢው ስፍራ
ተስማሚ ነው ኢክዋን ከ ኩፋርም ጋራ
ብዙም ህዝብ አፈሩ ሰው ተከተላቸው
በ መልካም መንገድ ላይ እየመሰላቸው
እንዴትስ አይመሩ እንዴት አይከተሉ
ለ ሙስሊሙ ሁሉ አንደ ዝንባሌው ዲኑን እያግራሩ
በጣም አስቸጋሪው ትልቁ ስልታቸው
ከ ሱንዮች ጋራ መቀላቀላቸው
ልብስ አሳጥረዋል ሱና ነው ፂማቸው
እውነትን ፈላጊ እንዴት ይለያቸው
ራስታ መስለህ ብትሄድ ውይንም ረስተኀው
በ ቫዝሊን ምናምን ፈረዝረዝ አርገኀው
ይህ ሱና አይደለም ብለው አይነግሩህም
በ ጭራሽ በ ጭራሽ አይከለክሉህም
ሂጃብሽን ለቀሽ በስትይል ብትሄጂ
ባንዳንዶች አጠራር ብሎም ብትፈነጂ
ተጫሚ ጫማውን ቛቛ የሚለውን
ምንም አይሉሽም አይቃወሙሽም
ከ መጥፎ ከልክለው በ ጥሩ አያዙሽም
ለምን ብትይ
እንደየ አየሩ እንዳካባቢው ስፍራ
ተስማሚ ነው ኢክዋን ወንጀልም ቢሰራ
በ ሂወት እያለስሽ በጣም ይወዱሻል
መውሊድ ብታከብሪ ይንከባከቡሻል
ካልተቃወምሻቸው እጅግ ያቀርቡሻል
ቀብር ውስጥ ስትገቢ ቀብረው ይሸኙሻል
ያኔ ብቻሽን ሆነሽ ምንስ ይውጥሻል
ነቃ በይ እህቴ ሱና ያዋጣሻል።
ማነው እድለኛው እጣ የወጣለት
ማነው የባነነው ማነውስ የነቃው
ከ ኢክዋኖች ሴራ የተጠነቀቀው
አንተኛውም ስማ ላልሰማ አሰማ
ሃቅ መራራ ናት ጥቂት ነው የሚያውቃት
በቀደምቶች መንገድ የሚያስተነተናት
እናማ ወንደሜ ለአኼራህ ተጨነቅ
ከ ሰመመን ውጣ ከ ስሜት ተላቀቅ
ያኔ በ ፍርዱ ቀን እንዳተጨናነቅ
እንግዲህ ተመከር ተመክአህም ምከር
ባጭር ላስቀምጥልህ የ ኢክዋንን ሚስጢር
ያ ሁሉ ቢድአ ያ ሁሉ ኩራፋት
በ ዱንያም ትምህርት ዲግሪ እና ማስትሬት
ብትደምር ኢንጅነር ብትደምር ዶክተሬት
ጠብታ የለውም ሱናን ካልያዙበት
ጠቅልለህ ብትጨምቀው የ እውቀት ጭማቂ
ከላይ ብትክባቸው ብለህም "አዋቂ "
በሸሪኢዓ ሚዛን ሲመዘን ሲለካ
የ ኢክዋኖች እውቀት ዜሮ ነበር ለካ
አላህ ቀጥተኛውን መንገድ ይምራን አሚን።
ኢክዋን አል ሙስሊሚን እጅግ የዘመኑት
ባስተሳሰባቸው እጅግ የመጠቁት
ባካዳሚክ ትምህርት ደራርበው የጫኑት
አእመሯቸው ሰፋ ቦርቀቅ ረቀቅ አሉ
ሄዱ ተራመዱ ተጓዙ አለፉ
በተማሩበት መስክ ኢስላምን ሊያስፋፉ
የ ሹብሃት መዓት እየደረደሩ
የማያውቀውን ህዝብ እያደናገሩ
ቀጠሉ ጨመሩ በ ዲን ውስጥ ፈጥራ
ሱናን ተቃራኒ እጅጉን ሚያስፈራ
ግልጽልጽ ብሎ የሚታየውን የ ኢስላም ጎዳና
በረዙት ከለሱት አመጡ ፈተና
እንደየ አየሩ እንዳካባቢው ስፍራ
ተስማሚ ነው ኢክዋን ከ ኩፋርም ጋራ
ብዙም ህዝብ አፈሩ ሰው ተከተላቸው
በ መልካም መንገድ ላይ እየመሰላቸው
እንዴትስ አይመሩ እንዴት አይከተሉ
ለ ሙስሊሙ ሁሉ አንደ ዝንባሌው ዲኑን እያግራሩ
በጣም አስቸጋሪው ትልቁ ስልታቸው
ከ ሱንዮች ጋራ መቀላቀላቸው
ልብስ አሳጥረዋል ሱና ነው ፂማቸው
እውነትን ፈላጊ እንዴት ይለያቸው
ራስታ መስለህ ብትሄድ ውይንም ረስተኀው
በ ቫዝሊን ምናምን ፈረዝረዝ አርገኀው
ይህ ሱና አይደለም ብለው አይነግሩህም
በ ጭራሽ በ ጭራሽ አይከለክሉህም
ሂጃብሽን ለቀሽ በስትይል ብትሄጂ
ባንዳንዶች አጠራር ብሎም ብትፈነጂ
ተጫሚ ጫማውን ቛቛ የሚለውን
ምንም አይሉሽም አይቃወሙሽም
ከ መጥፎ ከልክለው በ ጥሩ አያዙሽም
ለምን ብትይ
እንደየ አየሩ እንዳካባቢው ስፍራ
ተስማሚ ነው ኢክዋን ወንጀልም ቢሰራ
በ ሂወት እያለስሽ በጣም ይወዱሻል
መውሊድ ብታከብሪ ይንከባከቡሻል
ካልተቃወምሻቸው እጅግ ያቀርቡሻል
ቀብር ውስጥ ስትገቢ ቀብረው ይሸኙሻል
ያኔ ብቻሽን ሆነሽ ምንስ ይውጥሻል
ነቃ በይ እህቴ ሱና ያዋጣሻል።
ማነው እድለኛው እጣ የወጣለት
ማነው የባነነው ማነውስ የነቃው
ከ ኢክዋኖች ሴራ የተጠነቀቀው
አንተኛውም ስማ ላልሰማ አሰማ
ሃቅ መራራ ናት ጥቂት ነው የሚያውቃት
በቀደምቶች መንገድ የሚያስተነተናት
እናማ ወንደሜ ለአኼራህ ተጨነቅ
ከ ሰመመን ውጣ ከ ስሜት ተላቀቅ
ያኔ በ ፍርዱ ቀን እንዳተጨናነቅ
እንግዲህ ተመከር ተመክአህም ምከር
ባጭር ላስቀምጥልህ የ ኢክዋንን ሚስጢር
ያ ሁሉ ቢድአ ያ ሁሉ ኩራፋት
በ ዱንያም ትምህርት ዲግሪ እና ማስትሬት
ብትደምር ኢንጅነር ብትደምር ዶክተሬት
ጠብታ የለውም ሱናን ካልያዙበት
ጠቅልለህ ብትጨምቀው የ እውቀት ጭማቂ
ከላይ ብትክባቸው ብለህም "አዋቂ "
በሸሪኢዓ ሚዛን ሲመዘን ሲለካ
የ ኢክዋኖች እውቀት ዜሮ ነበር ለካ
አላህ ቀጥተኛውን መንገድ ይምራን አሚን።