ልጓም ያልተበጀለት የአቶ ሐሰን ታጁ ብእር እንደ ተራራ የገዘፉ፣ በእውቀታቸው የመጠቁ፣ ታላላቅ የኢስላም ሊቃውንትን ክብር ሲያጎድፍ፣ በስብእናቸው ላይ ሲረማመድ፣ ባስ ሲልም ሲሳደብና ሲያሽሟጥጥ ያየ፣ ያነበበ፣ የሰማ አይንና ጆሮ ቂያም ቀን ለመቃረቡ ይህ በቂ ማስረጃ ይሆነዋል።
«መውሊድ» በተሰኘ መፅሃፉ ላይ አሰቃቂ በሆነ መልኩ ምላሱን ከዘረጋባቸው ዑለማዎች አንዱ ታላቁ የሸሪዐ ሊቅ አሽሸይኽ ሐሙድ አትቱወይጂሪ (ረሒመሁላህ) ናቸው።
በገፅ 65 ላይ ሐሰን ታጁ ለሸይኽ ቱወይጂሪና ለመሰሎቻቸው ጥያቄ አለኝ በማለት ጥያቄውን ሲዘጋ እንዲህ ሲል ያሽሟጥጣል « ታዲያ የናንተ ግንዛቤ ከየት #በቀለ? በምን ሚዛን የሰለፍ ተሰኘ? »
ዳግም በሸይኽ ቱወይጂሪ ረሒመሁላህ ላይ እንዲህ ሲል መርዛማ ምላሱን ይዘረጋል •።.
« ሸይኽ ቱወይጂሪ ይህን ጉልህ እውነታ አድበስብሰው ለማለፍ መሞከራቸው ምሁራዊ ታማኝነታቸውን ጥያቄ ውስጥ ይከተዋል።»
ገፅ 83
«ሙደሊስ» (ማለትም ፡አስመሳይ፣ አጭበርባሪ) ይላቸዋል ።
ገፅ 85
ዳግም በሸይኽ ቱወይጂሪ ረሒመሁላህ ላይ እንዲህ ሲል መርዛማ ምላሱን ይዘረጋል •።.
« ሸይኽ ቱወይጂሪ ይህን ጉልህ እውነታ አድበስብሰው ለማለፍ መሞከራቸው ምሁራዊ ታማኝነታቸውን ጥያቄ ውስጥ ይከተዋል።»
ገፅ 83
«ሙደሊስ» (ማለትም ፡አስመሳይ፣ አጭበርባሪ) ይላቸዋል ።
ገፅ 85
ቀጣዩ የሐሰን መውሊድ ጥናት ሰለባ የሆኑት ደግሞ ታላቁ የዘመናችን ዐሊም አሽሸይኽ ሷሊሕ ፈውዛን አልፈውዛን (ሐፊዘሁላህ) ናቸው።
« አንድ ሰው ይህን ድርጊት (ተድሊስ) በህይወቱ አንዴም ሲፈፅም ከታየ ከታማኝነት ጎራ ወዲያው ይወጣል። ሸይኽ ፈውዛን በዚህች መረጃ መሰረት <ሙደሊስ> ሆነዋል። » ገፅ 96
« አንድ ሰው ይህን ድርጊት (ተድሊስ) በህይወቱ አንዴም ሲፈፅም ከታየ ከታማኝነት ጎራ ወዲያው ይወጣል። ሸይኽ ፈውዛን በዚህች መረጃ መሰረት <ሙደሊስ> ሆነዋል። » ገፅ 96
ዋ ጥፋትህ የታጁ ልጅ!! ሸይክ ፈውዛንን ከታማኝነት ጎራ አስወጥተህ ማንን ልታስገባበት ነው? ዋ ጥፋትህ! ዋ ጥፋትህ!
በነገራችን ላይ ከዓመታት በፊት የሸይክ ፈውዛን ኩቱቦች በምድረ ሐበሻ ላይ በስፋት ሲሰራጭ ያስተዋለው አቶ ሐሰን ታጁ «ኢርሻድ» የተሰኘውን የሸይኹን ኪታብ ተርጎሞ በመሸጥ ኪሱን አደልቦበት እንደነበር ማንም ያውቃል። እሱ ኪታብ ማለት ዛሬ ላይ አሕባሾች በቲቪ እየቀረቡ «የዓለም ሽብር ስጋት የሚፈልቀው ከዚህ መፅሃፍ ነው ያሉት ኪታብ ነው።» ሐሰን ታጁ መፅሃፋቸውን ተርጎሞ ሳንቲም የቆጠረባቸውን የኚህን ታላቅ የእውቀት ተራራ ውለታ የመለሰው በ«ሙደሊስነት» ክስ መስርቶባቸው ከታማኝነት ሊስቱ በማስወጣት ሆነ። የበላበትን ወጪት ሰባሪ !!
አንዳንድ ሰው «ለሳንቲም ብሎ እንደሚሰራ ኒያውን በምን አወቅክ?» ይሉኛል። የዋሆች እላቸዋለሁ እኔም በተራዬ። ዑመር ረዲየላሁ ዐንሁ ይህንና ሌሎች ሙርጂዕኛ የሚሸቱ ክሶችን እንዲህ ሲል ይመልሳል...
عَبْدَ اللَّهِ بْنَ عُتْبَةَ قَالَ سَمِعْتُ عُمَرَ بْنَ الْخَطَّابِ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ يَقُولُ إِنَّ أُنَاسًا كَانُوا يُؤْخَذُونَ بِالْوَحْيِ فِي عَهْدِ رَسُولِ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ وَإِنَّ الْوَحْيَ قَدْ انْقَطَعَ وَإِنَّمَا نَأْخُذُكُمْ الْآنَ بِمَا ظَهَرَ لَنَا مِنْ أَعْمَالِكُمْ فَمَنْ أَظْهَرَ لَنَا خَيْرًا أَمِنَّاهُ وَقَرَّبْنَاهُ وَلَيْسَ إِلَيْنَا مِنْ سَرِيرَتِهِ شَيْءٌ اللَّهُ يُحَاسِبُهُ فِي سَرِيرَتِهِ وَمَنْ أَظْهَرَ لَنَا سُوءًا لَمْ نَأْمَنْهُ وَلَمْ نُصَدِّقْهُ وَإِنْ قَالَ إِنَّ سَرِيرَتَهُ حَسَنَةٌ
2498 صحيح البخاري كِتَاب الشَّهَادَاتِ بَاب الشُّهَدَاءِ الْعُدُولِ
ዐብዱላህ ቢን ዑትባህ ረዲየላሁ ዐንሁ ዑመር ቢን ኸጣብ ረዲየላሁ ዐንሁ እንዲህ ሲል ሰማሁት ይላል:-
« በርግጥም በረሱል ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ጊዜ ሰዎች በወህይ ይዳኙ ነበር። ነገር ግን አሁን ወህዩ ተቋርጣል። አሁን እኛ ግልፅ በምታደርጉት (በውጫዊ ተግባራቶቻች ሁ) እንዳኛች ለን ። መልካምን ነገር ግልፅ ያደረገልን እናምነዋለን፣ እንቀርበዋለን ውስጣዊ ጉዳዩን መዳኘት በእኛ ላይ የተገባ አይደለም። ለውስጣዊው አላህ ይተሳሰበዋል። መጥፎን፣ እኩይን ነገር ለኛ ግልፅ ያደረገልን አንተማመንበትም አናምነውምም በውስጤ መልካምን (ኒያ) አስቤ ነው ብልም እንኳን። »
[ሰሒሕ አልቡኻሪ ኪታቡል ሹሃዳት: 2498]

ቀጣዩ የሐሰን ታጁ የስድብ መለማመጃ ስብእና ደግሞ ታላቁ የተሐድሶ መሪ የተውሒድና ዳዕዋ ሙጀዲድ ሸይኹል ኢስላም ሙሐመድ ዐብዱልወሃብ ረሒመሁላህ ናቸው። ሐሰን መፅሃፉ ላይ « እከሌ እንደነገረኝ እከሌ እከሌን እንዲህ አሉት » በሚል ሰንሰለት ሸይኽ ሙሐመድ ዐብዱል ወሃብን እንዲህ ሲል ሬት ሬት የሚል ውርጅብኝ ይወርድባቸዋል ።
« ሆኖም የነዳጅ ከሳውዲ መገኘት ሙሐመድ ዐብዱልወሃብን ከአንዲት ቀዬ ዳዒነት አውጥቶ ሸይኩል ኢስላም አደረጋቸው። » ገፅ: 107
« ሆኖም የነዳጅ ከሳውዲ መገኘት ሙሐመድ ዐብዱልወሃብን ከአንዲት ቀዬ ዳዒነት አውጥቶ ሸይኩል ኢስላም አደረጋቸው። » ገፅ: 107
ረሱል ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለው ነበር:
فقد روى أبو داود عن أبي هريرة رضي الله عنه قال: قال رسول الله صلى الله عليه وسلم: إن الله يبعث لهذه الأمة على رأس كل مائة سنة من يجدد لها دينها.
<< በየመቶ ዓመቱ ራስ አላህ ይህን ዲን እንዲያድሱ (እንዲጀድዱ) አንዳንድ የተሐድሶ ስብእናዎችን ወድዚች ምድር ይልካል።>>
ሸይኩል ኢስላም ሙሐመድ ዐብዱልወሃብ ረሒመሁላህ ረሕመርተን ዋሲዐ የክፍለ ዘመናችን ሙጀዲድ እንደነበሩ በርካታ ዑለማዎች ተስማምተዋል። የተቀረውን አላህ ያውቃል።
ቀጣዩ ደግሞ ሸይኽ ዐብዱል ዐዚዝ (ረሒመሁላህን) የዘለፈበት ስልታዊ አገባብ ነው።
ሸይኹን በቀጥታ ሳይሆን በተዘዋዋሪ (በውሸት ተመርኩዘው ሐቁን «አቃላይ»፣ አሁንም በውሸት ተመርኩዘው ሐሰቱን «አካባጅ» ብሎ ሲያበቃ በርካታ ስሞችን ይጠቅስና እነዚህን ስብእናዎች «ተሳደቡ» (ተሳዳቢ) በማለት ባልዋሉበት መሬት፣ ባልተናገሩበት አፍ በቅጥፈት ይወነጅላቸዋል። ገፅ: 121, ገፅ: 163
እዚህ ጋር ማንሳት የምፈልገው አንድ ነገር አለ። ሐሰን ታጁ ሸይክ ኢብኑ ባዝ ረሒመሁላህን ተሳዳቢ አድርጎ ያቀረበበት ፅንሰ ሃሳብ ሸይኹ «መውሊድን የሚደግፉ ሰዎች የሚያከብሩት ያለምንም በቂ ሸሪዐዊ መነሻ ነው።» በማለታቸው መሆኑን ራሱ ከገለፀ በህዋላ ሐሰን መውሊድን ይደግፋሉ ያላቸውን እንደነ ጀላሉዲን አስ ሱዩጢ፣ የዳናው ከዋክብት፣ ጌታው ሸኽ ዐሊ ጎንደር፣ ከዚያም በስተመጨረሻ አያቱ የሆኑትን ሸኽ ለጋስ እያል ስማቸውን ከጠቀሰ በህዋላ «እነኚህ ሁሉ ትላልቅ የዒልም ሰራዊት መውሊድን ያለምንም በቂ ሸሪዐዊ መነሻ ይደግፉታል ማለት ስድብ ነው ይላል።»

ወላሂ ይህን ሳነብ ትዝ ያለኝ ተከታዮቹ የቁርአን አናቅፆች ናቸው።
1
{{ እነርሱም «አላህ ያወረደውን ተከተሉ» በተባሉ ጊዜ
«አይደለም አባቶቻችንን በርሱ ላይ ያገኘንበትን ነገር እንከተላለን» ይላሉ፡፡
አባቶቻቸው ምንም የማያውቁና (ወደ እውነት) የማይመሩም ቢኾኑ (ይከተሉዋቸዋልን?) }} [በቀራህ 170-171]
1
{{ እነርሱም «አላህ ያወረደውን ተከተሉ» በተባሉ ጊዜ
«አይደለም አባቶቻችንን በርሱ ላይ ያገኘንበትን ነገር እንከተላለን» ይላሉ፡፡
አባቶቻቸው ምንም የማያውቁና (ወደ እውነት) የማይመሩም ቢኾኑ (ይከተሉዋቸዋልን?) }} [በቀራህ 170-171]
2
{{ ለአባቱና ለሕዝቦቹ፦ ይህቺ ቅርጻ ቅርጽ፣ ያቺ እናንተ ለርሷ ተገዢዎች የሆናችሁት ምንድን ናት? ባለ ጊዜ (መራነው)። ፡፡
አባቶቻችን ለሷ ተገዢዎች ሆነው አገኘን አሉ።
እናንተም አባቶቻችሁም፣ በእርግጥ በግልጽ ስሕተት ውስጥ ነበራችሁ አላቸው።
በምሩ መጣልህን? ወይንስ አንተ ከሚቀልዱት ነህ? አሉት። }}
[አንቢያ 52-54]

3
{{ ለአባቱና ለሕዝቦቹ «ምንን ትግገዛላችሁ» ባለ ጊዜ፡፡
«ጣዖታትን እንገዛለን፤ እርሷንም በመገዛት ላይ እንቆያለን» አሉ፡፡
(እርሱም) አለ «በጠራችኋቸው ጊዜ ይሰሟችኋልን? >>
«ወይስ ይጠቅሟችኋልን ወይስ ይጎዷችኋልን»
«የለም፦ አባቶቻችን እንደዚሁ ሲሠሩ አገኘን» አሉት፡፡}}
[አልሹዐራ 70-74]
{{ ለአባቱና ለሕዝቦቹ «ምንን ትግገዛላችሁ» ባለ ጊዜ፡፡
«ጣዖታትን እንገዛለን፤ እርሷንም በመገዛት ላይ እንቆያለን» አሉ፡፡
(እርሱም) አለ «በጠራችኋቸው ጊዜ ይሰሟችኋልን? >>
«ወይስ ይጠቅሟችኋልን ወይስ ይጎዷችኋልን»
«የለም፦ አባቶቻችን እንደዚሁ ሲሠሩ አገኘን» አሉት፡፡}}
[አልሹዐራ 70-74]
4
{{ ለነሱም አላህ ያወረደውን ተከተሉ በተባሉ ጊዜ፣ አይደለም፣ በርሱ ላይ አባቶቻችንን ያገኘንበትን እንከተላለን፣ ይላሉ፤ ሰይጣን ወደ እሳት ቅጣት የሚጠራቸው ቢሆንም፣ (ይከተሉዋቸዋልን?) }}
[ሉቅማን 21]
{{ ለነሱም አላህ ያወረደውን ተከተሉ በተባሉ ጊዜ፣ አይደለም፣ በርሱ ላይ አባቶቻችንን ያገኘንበትን እንከተላለን፣ ይላሉ፤ ሰይጣን ወደ እሳት ቅጣት የሚጠራቸው ቢሆንም፣ (ይከተሉዋቸዋልን?) }}
[ሉቅማን 21]
5
{{ (ነገሩ) እንደዚሁም ነው፤ ከበፊጥ በማንኛይቱም ከተማ ውስጥ አስፈራሪን አልላክንም፣ ቅምጥሎችዋ፣ እኛ አባቶቻችንን በሃይማኖት አገኘን፤ እኛም በፈለጎቻቸው ላይ ተከታዮች ነን ያሉ ቢሆኑ እንጅ።
(አስፈራሪው) አባቶቻችሁን በርሱ ላይ ከአገኛችሁበት ይበልጥ ቀጥተኛን (ሃይማኖት) ቢያመጣላችሁም? አላቸው፤ እኛ በርሱ በተላካችሁበት ነገር ከሐዲዎች ነን አሉ።}}
[አልዙኽሩፍ 22-24]

አላህ ሐቅን ተናገረ!!
ተመልከቱ ሐሰን ታጁ ሸይኽ ኡብኑ ባዝን ተሳዳቢ አድርጎ የሳለበት የማስረጃ አንደምታ «አባቶቻችን የነበሩበትን የመውሊድ መንገድ ያለበቂ ሸሪዐዊ ምክንያት ነው» በማለታቸው ምክንያት ሲሆን እርሱም « አባቶቻችንን ሰደቡብኝ እኔ የአባቶቼን መንገድ ተከታይ ነኝ» የሚል እንጂ ሌላ አይደለም።
ተመልከቱ ሐሰን ታጁ ሸይኽ ኡብኑ ባዝን ተሳዳቢ አድርጎ የሳለበት የማስረጃ አንደምታ «አባቶቻችን የነበሩበትን የመውሊድ መንገድ ያለበቂ ሸሪዐዊ ምክንያት ነው» በማለታቸው ምክንያት ሲሆን እርሱም « አባቶቻችንን ሰደቡብኝ እኔ የአባቶቼን መንገድ ተከታይ ነኝ» የሚል እንጂ ሌላ አይደለም።
በተጨማሪ በገፅ ላይ የሸይክ ኢብኑ ባዝን ንግግር በማጣቀስ
« ርካሽ ፕሮፓጋንዳ እንጂ ሌላ አይደለም፣ አስቀያሚና አስነዋሪ የስም ማጥፋት » ብሎ ይወርፋቸዋል። ረሒመሁላህ ረሕመተን ዋሲዐ
« ርካሽ ፕሮፓጋንዳ እንጂ ሌላ አይደለም፣ አስቀያሚና አስነዋሪ የስም ማጥፋት » ብሎ ይወርፋቸዋል። ረሒመሁላህ ረሕመተን ዋሲዐ
በተጨማሪም ትንሽዬ እምቦቅጭላ ትንኝ ዝሆንን ሲተናኮል እንዴት መሰላችሁ? ኢኽዋኒው ሐሰን ታጁ ሸይኩል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያን «አፈንጋጭ ሙፍቲ» እያለ ሲተች ነው። ጉድ በል ጎንደር!!
ለማንኛውም በገፅ 167, በገፅ: 196 ላይ በሰው አስታኮ ሸይኹል ኢስላምን ሲሳደብ ጉብ ብሎ ታገኙታላች ሁ።
እያለ..... በዐሊም ላይ እየቀጠፈ በጅህልና አንደበቱ ሱናን መጣረሱን ተያይዞታል።
ብቻ ወላሂ ለነፍሴም ለዚህም ሰውየ ፈራሁለት።
እንደው ይህን ስፅፍ አላህ በመብረቅ በላ ከመሬት ያደባኛል ብሎም አይፈራ? አረረ አላህ አያምጣብን ወላሂ ።
ብቻ ወላሂ ለነፍሴም ለዚህም ሰውየ ፈራሁለት።
እንደው ይህን ስፅፍ አላህ በመብረቅ በላ ከመሬት ያደባኛል ብሎም አይፈራ? አረረ አላህ አያምጣብን ወላሂ ።
{{አላህ ከናንተ እነዚያን ያመኑትንና እነዚያንም እውቀትን የተሰጡትን በደረጃዎች ከፍ ያደርጋል}} [አልሙጀድላህ 11]
{{ እነዚያ የሚያውቁና እነዚያ የማያውቁ ይተካከላሉን? በላቸው፤ የሚገነዘቡት ባለ አእምሮዎቹ ናቸው። }} [ አል-ዙመር: 9]