Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ኡሙ ዘይነብ ፋጢማ ቢንት ቢንት ዐባስ (አላህ ይዘንላት) የሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ ጎበዝ ሴት ተማሪ!


ኡሙ ዘይነብ ፋጢማ ቢንት ቢንት ዐባስ (አላህ ይዘንላት)
የሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ ጎበዝ ሴት ተማሪ!
ኢብን ከሢር ረሒመሁላህ ስለእሷ ሲናገሩ:
« ከተከበሩ ዑለማዎች አንዷ ነበረች። በጥሩ ታዝ እና ከመጥፎም ትከለክል ነበር። የአሕመዲያ (የሱፊያ ጦሪቃ) ወንድና ሴት ተከታዮች ‘ሙዋኻት’ ትሄድ ነበር። ያሉበትን ሁኔታ፣ የአሕለል ቢድዐዎችን መሠረት እና ሌሎችንም (አፈንጋጮች) ትቃወም ነበር። ወንድ እንኳን የማይችለውን ትሰራ ነበር።
የተቂዩ ዲን ኢብን ተይሚያህ መጅሊስ (የትምህርት ገበታ) ዘንድ ትመጣና ከርሱ እውቀትን ትወስድ ነበር። ተቂዩ ዲን ሲያሞግሷት፣ ስለእውቀቷና ታላቅነቷ ሲናገር ሰምቼዋለሁ። እርሷ ‘አልሙጝኒ’ን በከፊል ወይንም በአብዛኛው ታውቃለች ይባልላታል። እርሱ (ሸይኹል ኢስላም) እሷ ለምትጠይቀው ብዙ መስዓላ (ርእሰ ጉዳይ) እና መልካም ጥያቄዎች ብሎም ለፈጣን አረዳዷ ራሱን ያዘጋጅ ነበር። እርሷ ለብዙ ሴቶች ቁርአንን ታስተምር ነበር። ከነርሱም ውስጥ የባለቤቴ እናት እና የጀማሉዲን አልሚዚ ባለቤት የሆነችው ዓኢሻ ቢንት ሲዲቅ አንዷ ነች።
[አልቢዳያ ወኒሐያ 14/91]
وكانت من العالمات الفاضلات، تأمر بالمعروف وتنهي عن المنكر، وتقوم على الأحمدية في مواخاتهم النساء والمردان، وتنكر أحوالهم وأصول أهل البدع وغيرهم، وتفعل من ذلك ما لا تقدر عليه الرجال.
وقد كانت تحضر مجلس الشيخ تقي الدين بن تيمية فاستفادت منه ذلك وغيره، وقد سمعتُ الشيخ تقي الدين يثني عليها ويصفها بالفضيلة والعلم، ويذكر عنها أنها كانت تستحضر كثيرا من المغني أو أكثره، وأنه كان يستعد لها من كثرة مسائلها وحسن سؤالاتها وسرعة فهمها، وهي التي ختّمت نساءً كثيرا القرآن.
منهن أم زوجتي عائشة بنت صديق، زوجة الشيخ جمال الدين الميزي.