Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ሴት መሻይኻት!

ሴት መሻይኻት!

#1 . እመት ዓኢሻ (ረዲየላሁ ዐንሃ)

አቡ ሙሳ አልአሽዐሪ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዲህ ይላል:
ما أشكل علينا أصحاب رسول الله صلى الله عليه وسلم حديث قط فسألنا عائشة إلا وجدنا عندها منه علما
«እኛ የረሱል ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ባልደረቦች ሐዲስ ላይ እክል አጋጥሞን ወደ ዓኢሻ ሄደን አንጠይቃትም (በጠየቅናት የትኛውም ሐዲስ ዙሪያ) ዒልሙ ቢኖራትና (ብትመልስልን) እንጂ።» [ሱነን አትቲርሚዚይ 3880]

#2 . عمرۃ بنت عبدالرحمان

ኢብን ሻህባህ አዝዙህሪይ (ታቢዒይ) ለቃሲም ኢብኑ ሙሐመድ እንዲህ አሉት:
« እውቀት ለመፈለግ ያለህን ቅንነት ይተየኛል። ስለ እውቀት ማእድን ልንገርህ? እውቀትን ማግኘት ከፈለግክ ከ عمرۃ بنت عبدالرحمان ተማር።»
ቃሲምም ይላል: “ ወደርሷ የሄድኩኝ ጊዜ የማትደርቅ የእውቀት ውቅያኖስ ሆና ነው ያገኘኋት።» [ሲየር አዕላም አንኑበላእ አዝዘሃቢ 4/508]

#3 . የሶስተኛው ክ/ዘመን መሻይኻት

በሶስተኛው ክ /ዘመንም እንስት መሻይኻት የነበሩ ሲሆን ታላላቅ የሐዲሥ ሰዎች የትምህርት ገበታቸውን ይካፈሉ ነበር።
– የሐቢብ ቢን ወሊድ ሴት ባሪያ የነበረችው እና ነፃ የተለቀቀችው እመት ዐቢዳህ የመዲና ሰዎችን ሐዲሥ የኢማም ማሊክን ጨምሮ ታስተላልፍ ነበር።
– የኢማም አሕመድ ኢብን ሐምበል ባለቤት ዐባሳህ፣ ዘይነብ ቢንት ሱለይማን፣ ኡሙ ዑመር ሠቅፊያህ፣ ነፊሳህ ቢንት ሐሰን፣ ኸዲጃህ ኡሙ ሙሐመድ እና ሌሎችም ነበሩ።
[ المقتبس من أنباء الأندلس لابن حیان القرطبی 228/1)]

#4 . ከሪማህ መሩዚያህ

ከርሷ እውቀትን ለመቅሰም ከባጝዳድ (ኢራቅ) እስከ መካህ (ሱዑዲ) ይመጡ የነበሩት ኢማም ኸጢብ አልባጝዳዲን ጨምሮ ሌሎች ዑለማዎችን ሰሒሕ አልቡኻሪን ታስተምር ነበር።
[ታሪኸል ኢስላም አዝዘሃቢ 10/233]

#5 . الوزراء بنت عمر

በደማስቆ (ሶሪያ) እና በግብፅ ሰሑሕ አልቡኻሪን ታስተምር ነበር።
[ذیل التقیید فی رواۃ السنن والأسانید 397/2 ]

#6 . ኡሙ አሕመድ ዘይነብ ቢንት መኪይ

90 አመታቸው ነበር። ብዙ ዑለማዎችን አስተምረዋል። ሙስነድ ኢማም አሕመድን ያስተምሩ ነበር።[ 607/7 ذرات الذہب ]

7. ኡሙ ኢብራሂም ፋጢማህ አልጁዝዳኒያህ ፥

መጅሙዑ አጥጠበራኒ ታስተምር ነበር።
(تاریخ اسلام ۔ت:تدمری 126/43)

8. የኢማም አቡ ዳውድ ልጅ ኡሙ ሰለማህ ፋጢማህ 

በወቅቱ የታወቀች ሙሐዲሣህ ነበረች። ፋጢማህ ቢንት ዐብዱረህማንም በጊዜው ከነበሩት ሙሐዲሣት አንዷ ነበረች።
[(تاریخ بغداد،ط: العلمیۃ 442/14) ]

9. ሸሂዳህ ቢንት አሕመድ 

በእውቀቷና በተማሪዎቿ አማካኝነት የሴቶች መኩሪያ በመባል ትታወቅ ነበር። (تاریخ بغداد ، ط: العلمیۃ394/15)
10. ታላላቅ ሊቃውንት በወቅቱ የነዚህ ሙሐዲሣቶችን የኢልም ገበታ ይካፈሉ ነበር።
(امۃ الواحد بنت قاضی ابی عبداﷲ حسین بن اسماعیل المحاملی (تاریخ اسلام ، ت:بشار 437/8)
ام الفتح امۃ السلام بنت القاضی احمد بن کامل بغدادیہ(تاریخ اسلام ، ت:بشار 465/8)
ام الحسین جمعۃبنت احمد المحیۃ (تاریخ اسلام ، ت:بشار 634/16)
فاطمہ بنت ہلال الکرجیہ(تاریخ اسلام ، ت:بشار 635/16)
طاہرۃ بنت احمد ا لتنوخیہ(تاریخ اسلام ، ت:بشار 635/16)

11. የእውቁ ዐሊም ኢብኑ ሐጀር አል አስቀላኒ እህት ست الرکب علی

የሸይኹል ኢስላም እህት ልጅ زینب بنت عبداﷲ
የኢብኑ ቁዳማህ ልጅ እና ሌሎችም ሙሐዲሣቶች በወቅቱ ነበሩ።
[الدررالکامنۃ فيعیان المائۃ الثا منۃ]
12. የታሪኽ አድዲሚሽቅ ፀሃፊ የሆነው ታላቁ ዐሊም ኢብኑ ዐሳኪር ሰማኒያ የሚሆኑት አስተማሪዎቹ ሴት ሙሐዲሣቶች እንደነበሩ ገለፇል። ነፊሳ ቢንይ ኢብራሂም የታላቁ ዐሊም አዝዘሃቢ አስተማሪ ነበረች። ست العرب بنت محمد البخاری ደግሞ በኢራቅ ውስጥ የሐፊዝ ሐይሰሚ አስተማሪ ነበረች። ((الاعلام للزرکلی 77/3))
በመጨረሻም ማስተላለፍ የምፈልገው ቢኖር እውቀትን መፈለግ በወንድም ሆነ በሴት ላይ ግዴታ መሆኑን የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ገለፀውልናልና ዒልምን መፈለግ የእህቶቻችን፣ የሚስቶቻችን የአማኝ እህቶቻችን መብት እንደሆነ ማወቅ በኛ በወንዶች ላይ የተገባ ነው። ኢብኑል ሐጅ አልማሊኪ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ ፥
فلو طلبت المرأة حقها في أمر دينها من زوجها ورفعته إلى الحاكم وطالبته بالتعليم لأمر دينها لأن ذلك لها إما بنفسه أو بواسطة إذنه لها في الخروج إلى ذلك لوجب على الحاكم جبره على ذلك كما يجبره على حقوقها الدنيوية إذ أن حقوق الدين آكد وأولى
አንዲት እንስት በእውቀት በኩል ያላትን ሐቅ ከባሏ ከጠየቀች እናም መሪውን (የሙስሊሞች መሪ) በዲኗ ትምህርት ዙሪያ ከጠየቀች ባሏ እንዲያስተመራት አሊያም እውቀትን ፍለጋ ውጪ ወጥታ እንድትማር ፍቃድ ማግኘት መብቷ ነው። በመሆኑም ባሏ በዱኒያዊ ጉዳዮች ላይ ፍላጎቷን እንደሚያሟላላት ሁሉ (እውቀት መፈለግ ላይ ያላትን ፍላጎት እንዲያሟላላት) ግፊት ማድረግ በመሪው ላይ ግዴታ ይሆንበታል። ምክንያቱም እውቀትን የመፈለግ መብት ከምንም ነገር በላይ አስፈላጊ ነውና። [አል መድኸል 1/276]