ይህን ይሆን ‹‹ነባሩ እስልምና›› የሚሉት?
=======================
ነባሩ እየተባለ የሚወራለት ሰርጎ ገቡ መጤው የሱፍያ መንገድ ነው፡፡ ሰሃባዎች የመጀመርያዎቹ 2 ጊዜ ወደ ኢትዬጵያ የተሰደዱት ያልነበሩበትን በአድ አምልኮ (ሽርክ ከአላህ ውጭ ያለን ሙታንን መለመን)፣ ቢድዐን፣ ጭፈራን፣ አደንዛዥ ቅጠሉን ጫት መቃምን ነው፡፡ ሱፍያም ሆነ ሌሎች የጥመት መንገዶች እውነተኛው የመጀመርያው አንድ ብቻ የሆነው የሃቅ መስመር ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እና ሰሃባዎቻቸው ከነበሩበት መንገድ ያለው ተቃርኖ የ7ኛ ሰማይ እና የ7ኛ ምድር ያህል ነው፡፡ ለምሳሌ አገራችን ላይ ታዋቂ ከሆኑት የሱፍያ መንዙማ ባዬች አንዱ ሸይኽ ሰኢድ አርባ እንዲህ ሲል የአላህ መብት ለነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) አሳልፎ ይሰጣል፡፡

‹‹የአርባው ልጅሆ፣ ቆሟል ከደጅሆ፣
ስጡት በእጅሆ ከእዛ ከጉርጅሁ (ከካዝናዎ)››
ስጡት በእጅሆ ከእዛ ከጉርጅሁ (ከካዝናዎ)››
ይህ ያነበባችሁት የሽርክ ስንኝ ለነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) የተገጠመ እና እንደ መንዙማ አገራችን ላይ ይባላል፡፡ ይህንን ያለውም ሸህ ሰኢድ አርባ በመባል ይታወቃል፡፡ ‹‹የአርባው ልጅሆ›› በማለት ግጥሙ ላይ እራሱን የሚጠራው ‹‹ሱፊ›› ኢናሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂኡን፡፡ ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) የአላህ ባርያ እና መልክተኛ ብቻ እና ብቻ ናቸው፡፡ ከአላህ ጋር ሸሪካ አይደሉም፡፡
እስቲ የግጥሙን አስከፊነት እና ሽርክነት እንየው፡፡
1) ‹‹የአርባው ልጅሆ››
ነብዩ ሙሐመድ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) የማንም አባት አይደሉም የመጨረሻው ነብይ እንጂ፡፡ አላህ እንዲህ ይላል
مَّا كَانَ مُحَمَّدٌ أَبَآ أَحَدٍ مِّن رِّجَالِكُمْ وَلَٰكِن رَّسُولَ ٱللَّهِ وَخَاتَمَ ٱلنَّبِيِّۦنَ ۗ وَكَانَ ٱللَّهُ بِكُلِّ شَىْءٍ عَلِيمًا
ሙሐመድ ከወንዶቻችሁ የአንድም ሰው አባት አይደለም፡፡ ግን የአላህ መልክተኛና የነቢዮች መደምደሚያ ነው፡፡ አላህም በነገሩ ሁሉ ዐዋቂ ነው፡፡

2) ‹‹ቆሟል ከደጅሆ››
የሚቆመውም ለአላህ ብቻ ነው፡፡ አላህ እንዲህ ይላል
وَقُومُوا۟ لِلَّهِ قَٰنِتِينَ
ታዛዦች ኾናችሁም ለአላህ ቁሙ፡፡
የሚቆመውም ለአላህ ብቻ ነው፡፡ አላህ እንዲህ ይላል
وَقُومُوا۟ لِلَّهِ قَٰنِتِينَ
ታዛዦች ኾናችሁም ለአላህ ቁሙ፡፡
3) ‹‹ስጡት በእጅሆ ከእዛ ከጉርጅሁ (ከካዝናዎ)››
ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) አይደለም ሊሰጡ እራሳቸው ከአላህ ካዝና፣ ከእዝነቱ፣ ከቱሩፋት ጠባቂ ደሃ ባርያው ነበር፡፡ ባርያዎች በጠቅላላም ከአላህ ፈላጊ ደሃዎች ናቸው፡፡ አላህ እንዲህ ይላል
قُل لَّآ أَقُولُ لَكُمْ عِندِى خَزَآئِنُ ٱللَّهِ وَلَآ أَعْلَمُ ٱلْغَيْبَ وَلَآ أَقُولُ لَكُمْ إِنِّى مَلَكٌ ۖ إِنْ أَتَّبِعُ إِلَّا مَا يُوحَىٰٓ إِلَىَّ ۚ قُلْ هَلْ يَسْتَوِى ٱلْأَعْمَىٰ وَٱلْبَصِيرُ ۚ أَفَلَا تَتَفَكَّرُونَ
«ለእናንተ የአላህ ግምጃ ቤቶች እኔ ዘንድ ናቸው አልልም፡፡ ሩቅንም አላውቅም፡፡ ለእናንተም እኔ መልአክ ነኝ አልልም፡፡ ወደእኔ የሚወርድልኝን እንጅ ሌላን አልከተልም» በላቸው፡፡ «ዕውርና የሚያይ ይስተካከላሉን? አታስተነትኑምን?» በላቸው፡፡

وَلَآ أَقُولُ لَكُمْ عِندِى خَزَآئِنُ ٱللَّهِ وَلَآ أَعْلَمُ ٱلْغَيْبَ وَلَآ أَقُولُ إِنِّى مَلَكٌ وَلَآ أَقُولُ لِلَّذِينَ تَزْدَرِىٓ أَعْيُنُكُمْ لَن يُؤْتِيَهُمُ ٱللَّهُ خَيْرًا ۖ ٱللَّهُ أَعْلَمُ بِمَا فِىٓ أَنفُسِهِمْ ۖ إِنِّىٓ إِذًا لَّمِنَ ٱلظَّٰلِمِينَ
«ለእናንተም እኔ ዘንድ የአላህ ግምጃ ቤቶች አልሉ ሩቅንም ዐውቃለሁ አልላችሁም፡፡ እኔም መልአክ ነኝ አልላችሁም፡፡ ለእነዚያም ዓይኖቻችሁ ለሚያዋርዷቸው አላህ ደግ ነገርን (እምነትን) አይሰጣቸውም አልልም፡፡ አላህ በነፍሶቻቸው ውስጥ ያለውን ነገር አዋቂ ነው፡፡ እኔ ያን ጊዜ ከበደለኞች እሆናለሁና» (አላቸው)፡፡

وَإِن مِّن شَىْءٍ إِلَّا عِندَنَا خَزَآئِنُهُۥ وَمَا نُنَزِّلُهُۥٓ إِلَّا بِقَدَرٍ مَّعْلُومٍ
መካዚኖቹም (መክፈቻቸው) እኛ ዘንድ ያልሆነ ምንም ነገር የለም፡፡ በተወሰነም ልክ እንጂ አናወርደውም፡፡

أَمْ عِندَهُمْ خَزَآئِنُ رَحْمَةِ رَبِّكَ ٱلْعَزِيزِ ٱلْوَهَّابِ
ይልቁንም የአሸናፊውና የለጋሱ ጌታህ የችሮታው መጋዘኖች እነርሱ ዘንድ ናቸውን?

وَلِلَّهِ خَزَآئِنُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ وَلَٰكِنَّ ٱلْمُنَٰفِقِينَ لَا يَفْقَهُونَ
የሰማያትና የምድር ድልቦችም የአላህ ናቸው፡፡ ግን መናፍቃን አያውቁም፡፡

وَٱللَّهُ ٱلْغَنِىُّ وَأَنتُمُ ٱلْفُقَرَآءُ ۚ
አላህም ከበርቴ ነው፡፡ እናንተም ድኾች ናችሁ፡፡
አላህም ከበርቴ ነው፡፡ እናንተም ድኾች ናችሁ፡፡
አላህ ብቻ በሚችለው ጉዳይ ከአላህ ውጭ ያለን ማንንም ይሁን ማን (መላኢካም፣ ነብይም፣ ጂንም፣ ዛፍም…..) የጠየቀ በእርግጥ ሁሉን ቻይ በሆነው አላህ ላይ አጋርቷል፡፡ በአላህ ላይ እያጋራ የሞተ ሰው የእሳት ነው ይሉናል ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም)፡፡ አሁንም ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ ይላሉ ‹‹የአደም ልጅ ሲሞት ስራው ይቋረጣል….›› ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ደግሞ የአደም ልጅ ናቸው፣ እሳቸውም ሞተዋል፡፡ እሳቸውም በህይወት በነበሩ ግዜ ይለምኑ የነበረው፣ ይፈሩ የነበረው፣ ይመኩበት የነበረው ህያው በሆነው በማይሞተው አላህ ብቻ እና ብቻ ነበር፡፡
በአንድነት ስምም ‹‹ሲን እና ሷድ ሰለፊ እና ሱፊ አይለየንም›› እያሉ ለሚያጭበረብሩ ሰዎች አላህን ሊፈሩ ይገባል፡፡ ‹‹ነባሩ እስልምና›› እያሉ አላዋቂዎች የሚጠሩት ሱፍያ ማለት ብዙ ሽርክ፣ ቢድዐ፣ ፊስቆች ያሉበት የጥመት መንገድ ነው፡፡ መጤ ‹‹ወሃቢ›› እያሉ የሚጠሩት የአህለሱና ወልጀመዓ፣ ሰለፍያ ብቸኛው የሃቅ ጎዳና ሰሃባዎች ወደ ሀበሻ ሲሰደዱ ይዘውት የመጡት አንድ አምላክ አላህን በብቸኝነት ማምለክ በእሱም ላይ ማንንም አለማጋራት፣ የነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለምን) መራቅ ቢድዐ የተባለን መራቅ፣ አንድ በሃቅ ላይ የተሰበሰበ ጀመዐ መሆን እንጂ ‹‹በአንድነት›› ስም ሽርክና ቢድዐ የሚሰራውን ሁሉ ‹‹ሲን እና ሷድ ሰለፊና ሱፊ አይለያየንም፣ መውሊድ አይለያየንም፣ መውሊድ ቅርንጫፍ ነው፣ መውሊድ አቂዳ አይደለም›› እያሉ ማጭበርበር አይደለም፡፡
እንዴት ነው ሃቅ እና ባጢል አንድ የሚሆነው? ከሃቅ በኋላ ጥመት እንጂ ምን አለ?
መጤዎቹ፣ ሰርጎ ገቦቹ ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እና ሰሃባዎቻቸው የነበሩበት መንገድ ሰለፍያ፣ አህለሱና ወልጀመዓ ‹‹ወሃቢያ›› እያሉ የሚጠሩት ሳይሆን ኸዋሪጅ፣ ሺዓ፣ ቀደርያ፣ ሙዕተዚላ፣ ማትሩድያ፣ አሽዐርያ፣ ሱፍያ፣ ……. ኢኽዋን፣ ተብሊግ፣ አኽባሽ፣ አልቃኢዳ፣ ዳኢሽና ሌሎችም የጥመት ቡድኖች ናቸው፡፡

ከኋላ የመጣ አይን አወጣ እንደተባለው ሆነ፡፡ ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ኢስላም እንግዳ ሆነ እንደጀመረና ተመልሶ እንግዳ እንደሚሆን ተናግረው ነበር፡፡ ይሀው በአይናችን እያየነው ነበር፡፡
አላህ ሆይ! ውስጥ አዋቂው አንተ ብቻ ነህ፡፡ እኛ ባየነው ለተውሂድ የለፉትን ሸይኽ ሙሐመድ አብድል ወሃብ፣ ኢትዬጵያዊው ኸይኽ ሙሐመድ ወሌ እና ሌሎችም እዘንላቸው፣ ቀብራቸውን አስፋላቸው፣ ቀብራቸውን የጀነት ጨፌ አድርግላቸው፣ ማራቸው፣ ዉድድ አድርጋቸው፣ በህይወት ያለነውንም የሃቋን የነብያት ሁሉ መንገድ ተውሂድን ምራን፣ በዛው መንገድ ላይ ግደለን፡፡