Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ጥያቄ፦ ነቢዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) የተቀበሩት መስጂድ ውስጥ መሆኑን እንደማስረጃነት ለሚያቀርቡት የቀብር አምላኪዎች ምን መልስ እንስጣቸው? ሸይኽ መሐመድ ኢብኑ ሷሊህ አልዑሰይሚን ረሂመሁላህ

ጥያቄ፦ ነቢዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) የተቀበሩት መስጂድ ውስጥ መሆኑን እንደማስረጃነት ለሚያቀርቡት የቀብር አምላኪዎች ምን መልስ እንስጣቸው?
መልስ፦ ለዚህ ጥያቄ በብዙ መልክ መልስ ይሰጣል፦
አንደኛ፦ መስጂዱ በቀብር ላይ አልተገነባም ነበር። የተገነባው ነቢዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) በሕይወት እያሉ ነበር።
ሁለተኛ፦ ነቢዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) መስጂድ ውስጥ አልተቀበሩም። የተቀበሩት በቤታቸው ውስጥ ነበር።
ሦስተኛ፦ የነቢዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ቤቶች የዓኢሻን ቤት ጨምሮ ወደ መስጂዱ እንዲጠቃለል የተደረገው በሰሃቦች ሙሉ ስምምነት አልነበረም። እንዲያውም አብዛኞቹ ሰሃቦች ተቃውሞአቸውን በማሰማት ትተው ከሄዱ በኋላ ነው ቀብራቸው ወደ መስጂዱ እንዲጠቃለል የተደረገው። ይህም የሆነው በ94 አመተ ሂጅራ አካባቢ ነበር። ይህን ጉዳይ ሰሃቦች በአንድ ድምፅ አልተስማሙበትም። ከፊሎቹ ተቃወሙ። ከተቃወሙት ውስጥ ሰዒድ ቢን አልሙሰየብ ይገኝበታል።
አራተኛ፦ ቀብሩ ወደ መስጂድ ከተጠቃለለ በኋላ እንኳ መስጂድ ውስጥ ነው ያለው አይባልም ምክንያቱም ራሱን በቻለ ክፍል ውስጥ ነውና። መስጂድ በርሱ ላይ አልተገነባም። ስለዚህም ይህ ቦታ የተጠበቀና በሶስት ግድግዳዎች የተከለለ ነው። ግድግዳው የተደረገው ከቂብላ አቅጣጫ ዘወር ባለ ማእዘን ላይ ነው። ማለትም ሦስት ማእዘን አለው ማለት ነው። ሰው ሲሰግድ ወደ ቀብሩ ፊቱን እንዳያዞር ማእዘኑ ያለው በስተሰሜን በኩል ነው። በዚህም የቀብር አምላኪዎች ማስረጃ ውድቅ ይሆናል።
❲ሸይኽ መሐመድ ኢብኑ ሷሊህ አልዑሰይሚን ረሂመሁላህ❳