Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ሺዓዎች "ሺዓ" ወይም "ራፊዷ" የሚል ስም ለምን ተሰጣቸው?

ለአላህ ከዚያም ለታሪክ لله ثم للتاريخ


=== ሺዓዎች "ሺዓ" ወይም "ራፊዷ" የሚል ስም ለምን ተሰጣቸው? ===
"ሺዓ" ማለት ከአረብኛ ቋንቋ አንጻር ጉሩፕ፣ ተከታይ፣ ረዳት ማለት ሲሆን ሺዓዎች በተሳሳተ መልኩ የዐሊይ እና የልጁ ሁሰይን (ረዲያሏሁ ዐንሁማ) ረዳቶች ነን ይሉ ስለነበር ይህ ስም መለያቸው ሆኗል ከዛም "ራፊዷ" የሚል ስያሜ ተሰጥቷቸዋል።
'ራፊዷ' ማለት 'እምቢ ባይ' ማለት ሲሆን በዚህ የተሰየሙበት ምክኒያትንና ለመጀመሪያ ግዜም የተሰየሙባት አጋጣሚ እንደ ሚከተለው ነው_ ...
የቀድሞ ሺዓዎች የዐሊይ ልጅ የሆነው የሁሰይን የልጅ ልጅ ዘንድ በመሄድ 'ከአንተ ጋር እንሆን ዘንድ ከአቡበክር እና ከዑመር የጠራሁ ነኝ < የነሱ ተቃዋሚ ነኝ > በል' አሉት እሱም "እነሱ እኮ የቅድመ አያቴ <የነቢዩ > የቅርብ ጓደኞች ናቸው እንዴት እነሱን እተቻለሁ? ይልቁንስ እወዳቸዋለሁ" አላቸው። ይህንንም ሲላቸው ጥለውት ሄዱ። በዚህና መጀመሪያም የአቡበክር አስሲዲቅን እና የዑመርን (ረዲየሏሁ ዐንሁማ ) መሪነት አናምንበትም <አንቀበልም > ይሉና ያስተባብሉ ስለነበር "ራፊዷ" የሚለው ስያሜ ተሰጣቸው:: ይህንንም: <አል መጅሊሲ> የሚባለው ጸሃፊያቸው <አል_ቢሓር> በሚባለው መጽሃፉ ገጽ 68
ላይ ጠቅሷል ይህ በንዲህ እንዳለ: አንዳንድ ዑለሞች ይህ ስያሜ የተሰጣቸው ትክክለኛውን ዲነል ኢስላም (ስለተው) አልቀብልም ስላሉ እንደሆነ ጠቅሷል።
Ustaz Ahmed Adem