"ታውቃለህ ይሄ ዝንብ ካፊር ነው"
ይህ ከታላቁ የግብፅ ዓሊም ከሸይኽ ዶ/ር ሙሐመድ ሰዒድ ረስላን ትምህርት የተቀነጨበ ስለተክፊሪዪች አስገራሚ ድንበር ማለፍ የሚተርክ ነው።
ሸይኽ ረስላን እንዲህ ይላሉ፦ " ሁለት ተክፊሪዮች ነበሩ፤ ዓለሙን በሙሉ አክፍረው ሁለታቸው ብቻ ቀርተዋል። ቁጭ
ብለው ሳሉ ዝንብ መጣችና አንደኛው አፍንጫ አሊያም አይኑ ጣጥግ ላይ አረፈች። አስቸገረችው፤ ያባርራታል ትመለሳለች።
ዝንብ ደግሞ ያባረሩት ጊዜ ይመለሳልና ተመለሰ። በጣም ሲጨናነቅ፣ መጨናነቁም የከበደው ግዜ ለጓደኛው "ታውቃለህ
ይሄ ዝንብ ካፊር ነው" አለው።
ጓደኛውም "አይደለም! እንዴት ካፊር ይሆናል?! በመሰረቱ መች ሙከለፍ(ለሸሪዓ ተገዳጅ) ሆነና?! አእምሮስ መች አለውና! እንዴት ካፊር ይሆናል?!" አለው።
ይሄኛውም መልሶ "ምክንያቱም ይህ ምእመናንን እያስቸገረ ነው፤ ማንኛውም ምእመናንን ፈቅዶ የሚያስቸግርኮ ካፊር ነው" አለው።
ሁለተኛው ግን "አይ እኔ በዚህንኳ አልስማም" ሲለው የመጀመሪያው ይሄኛውንም አከፈረው! ምክንያቱ ደግሞ "ካፊርን
አላከፈረም" ነበርና ነው። የመጀመሪያው ዝንብን አክፍሯል ማንም ዝንብን ያላከፈረ ካፊር መሆኑ ነው። እነርሱ ዘንድ
ወርቃማ በሆነው 'ካፊርን ካፊር ያላደረግ ካፊር ነው' በሚለው የዘመናችንም ሆነ የቀድሞዎቹ ኸዋሪጆች መርሆ መሰረት
..."