Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

አላህ አርሸ በላይ ነው Gtm


ለምን ይሆን እምቢ ያሉት?
ለምን ይሆን እምቢ ያሉት?
በአላህ ላይ ያመፁና የኮሩት፤
ቦታ የለህም የሚሉት?
ሁሉም ቦታ ነውም ያሉት?
አይከብድም ወይ ትርጉማቸው
ከተባሉት መዞራቸው
አርሸ ላይ ነኝ እያላቸው
በቁርአኑ ግልፅ አድርጎ ሲነግራቸው
አንተ አታውቅም አዋቂ ነን ማለታቸው
አርሽ ላይስ አይደለህም ብለው የሞገቱት
እርሱ ያለውን ሰምተው ማፅደቅ ሲገባቸው
ትርጓሜን ማዛባትም ሆነ ስራቸው
አርሽ ብሎ በቁርአኑ እያላቸው
በተዘዋሪ እንኳን ሳይሆን በቀጥታ ነገራቸው
ለምን ይሆን መጥመማቸው?
በጌታቸው በአምልካቸው
ይህ ሁሉ ማጥ ውስጥ መግባታቸው
የቱም እምነት ያላለውን ማለታቸው
በኢስላም ላይ ማመፃቸው
የአላህን ባህሪያቱን አስበውት በትንሿ እውቀታቸው?
ሀሳቦችን አስቀድመው መጓዛቸው
የጌታን ቃል ወደ ኋላ ማለታቸው
ተመለሱ ንስሃ ግቡ እንበላቸው
ግን እነርሱ ሰጥመዋል በምናባቸው
ተስፋ ሳንቆርጥ በዱኣችን እናሰባቸው
መንገዱን እንዲያሳያቸው
ርቀዋል በፍልስፍና በራዕያቸው
ደጉ ጌታ ተው ብሎ ያባናቸው።
እንደዚሁ በጥሜት ላይ እንዳይሄዱ በእምነታቸው
ቅጣቱን አይችሉትምና የካዱት ጌታቸው
© ተንቢሃት